Postlar filtri


📢 የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የክረምት STEM ሥልጠና በስኬት ተጠናቀቀ

📌 የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የSTEM መርሃ-ግብር ላይ
🎮 Level 0: Robotics for Kids and Python Programming for Kids
🔬 Level 1: Basic Science Courses
⚙️ Level 2: Engineering Courses
🛠 Level 3: STEM Innovation Project እንዲሁም
🚀 "AI and Mathematical Research" STEM Camp የትምህርት የክረምት መርሃ ግብር የስቴም ማዕከሉ ከ673 ተማሪዎች በላይ ተቀብሎ ትምህርታቸውን በተሳካ ሁኔታ ላጠናቀቁ 520 ተማሪዎች ትምህርቱን መጨረሳቹሁን በማስመልከት ቅዳሜ መስከረም 09/2019 ዓ.ም የምስክር ወረቀት በዩንቨርስቲው ተበርክቶላቸዋል። በዕለቱም የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሃም ደበበ እንደገለጹት፣ ዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶቹን በማጠናከር እና ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠን ረገድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አክለውም ተማሪዎች በሥልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በቀጣይ የትምህርት ዘመናቸው ስኬት፣ ለፈጠራ እንዲሁም ለምርምር ሥራዎቻቸው በአግባቡ እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል። እንዲሁም የስቴም ሲነርጂይ “STEM Synergy Ethiopia” ካንትሪ ዳይሬክተር ኢንጂነር አብዮት ላቀው በበኩላቸው፣ ተቋማቸው በስቴም ትምህርት ክህሎት ማሳደግ ላይ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ገልጸው ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር በቀጣይም በተለያዩ የSTEM ትምህርትና ሥልጠና መርሃ ግብሮች ላይ አብረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።


📢 በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የSTEM መርሃ-ግብር ትምህርት ተማሪዎች በሙሉ

📌 የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የSTEM መርሃ-ግብር ላይ
🎮 Level 0: Robotics for Kids and Python Programming for Kids
🔬 Level 1: Basic Science Courses
⚙️ Level 2: Engineering Courses
🛠 Level 3: STEM Innovation Project እንዲሁም
🚀 "AI and Mathematical Research" STEM Camp የትምህርት መርሃ ግብር ላይ ስትማሩ የነበራቹሁ እና ትምህርታቹሁን በአግባቡ የተከታተላቹሁ የትምህርት ውጤት በዚህ ቴሌግራም ላይ የለጠፍን ሲሆን ትምህርቱን መጨረሳቹሁን በማስመልከት ቅዳሜ መስከረም 09/2019 ዓ.ም ከ2፡30 ሰዓት ጀምሮ በ ‘AASTU Old Graduation Hall’ የመዝጊያ ስነ ስረዓት ይካሄዳል። በመሆኑም ትምህርታቹሁን በአግባቡ ያጠናቀቃችሁ ተማሪዎች በዕለቱ በ ‘AASTU Old Graduation Hall’ በመገኘት የምስክር ወረቀታቹሁን በሰዓቱ በመገኘት እንድትውስዱ በአክብሮት እንጠይቃለን።

2k 0 13 1 11

📚 ትምህርት እና የማህበራዊ ሚዲያ

ውድ ተማሪዎች፦


ዛሬ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጥቂት ሰከንዶች የሚፈጅ ቪዲዮ በአንድ ሌሊት በብዙ ሰዎች ዘንድ ታዋቂ ሊያደርግ ይችላል። ይህም ብዙ ወጣቶች "ትምህርት ተምሬ ምን አገኛለሁ?" እንዲሉ እያደረገ ነው።

አንዳንድ * ታዋቂ * ነን የሚሉ ሰዎች ህይወት፣ ስኬት ያለው እዛ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብቻ እንደሆነ በማሳየት የልጆችን አእምሮ፣ የወደፊት ተስፋና ህልም እየገደሉ ነው።

" TikTok " ሆነ ሌላ የማህበራዊ ሚዲያ መጠቀም ወይም ይዘት መፍጠር በራሱ ችግር አይደለም፤ ችግሩ ግን የትምህርት፣ የንባብና የራስን እድገት ጊዜ ሲተካ ነው።

አስተውሉ 👉 ዝና ሊያልፍ ይችላል፤ እውቀትና ችሎታ ግን ማንም ሊነጥቃችሁ የማይችለው ሀብታችሁ ነው።

🎓 ትምህርት ምን ይሰጣል ?

ትምህርት መማር ፈተና ለማለፍ ብቻ አይደለም። ማሰብን ፣ መጠየቅን ፣ ችግር መፍታትን ፣ ትክክለኛውንና ስህተቱን መለየትን ፣ ሚዛናዊ መሆንን፣ ራስን መግዛትን ያስተምራል። የራስ እምነትን ያዳብራል፣ የሥራ እድልን ያሰፋል፣ አንድ ሰው የሚፈልገውን ህይወት ለመገንባት የሚያስፈልገውን እውቀትና ክህሎት ይሰጣል።

ዛሬ የምታሳልፉት ጊዜ ነገ የምትሆኑትን ሰው ይወስናል።

ሰዓታትን በስልክ ወይም በሌላ ስክሪን ላይ ብዙ ሰዓት ማሳለፍ ጊዜያዊ መዝናኛ ቢሰጣችሁም፣ በዚያ የምታጡት የጥናት ጊዜ ግን መልሳችሁ ልታገኙት አትችሉም።

📱 ተማሪዎች ማህበራዊ ሚዲያን ተጠንቀቁ ፤ ተጠቀሙበት እንጂ እሱ እንዳይጠቀምባችሁ!

TikTok ፣ Facebook ፣ Telegram፣ YouTube፣ Instagram፣ X እና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ለመማር ፣ አዳዲስ እውቀቶችን ለማግኘትና ጠቃሚ ክህሎቶችን ለመማር ትልቅ እድል ይሰጣሉ። ነገር ግን ያለገደብ መጠቀም የጥናት ጊዜን ሊወስድ፣ ትኩረትን ሊበትንና የትምህርት ውጤትን ሊጎዳ ይችላል።

⏰ ስለዚህ ለማህበራዊ ሚዲያ የምታጠፉትን ጊዜ ወስኑ። በተለይ የጥናት ሰዓትን ለስልክ አትስጡ። ሌሊት ረጅም ሰዓት ስልክ መጠቀምም እንቅልፍን ስለሚያሳንስ በሚቀጥለው ቀን ትኩረታችሁን ሊጎዳ ይችላል።

🔐 የግል መረጃችሁን ጠብቁ።

የቤት አድራሻ፣ የስልክ ቁጥር፣ የትምህርት ቤት መረጃ፣ የቀጣይ መርሃ ግብር ወይም ሌሎች የግል መረጃዎችን ለማታውቋቸው ሰዎች አትስጡ። በኢንተርኔት ላይ የምትለቁት መረጃ በቀላሉ ሊሰራጭ እንደሚችል አትዘንጉ።

👩‍👩‍👦‍👦 ወላጆች፣ የልጆቻችሁን የዲጂታል ህይወት ተከታተሉ።

ልጆች ስልክ እንዳይጠቀሙ ብቻ መከልከል ሳይሆን፣ ለምን ገደብ እንደሚያስፈልግ ከእነሱ ጋር ተወያዩ። እናተም አርአያ ሁናችሁ አሳዩዋቸው። ጊዜ ስጧቸው። ረጅም ሰዓት ቲክቶክ ወይም ሌላ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባለማሳለፍ የምትመክሯቸውን እውነትም ኑራችሁ አሳዩዋቸው።

- የጥናት፣
- የእንቅልፍ፣
- የቤተሰብ ጊዜ
- የመዝናኛ ጊዜን በአግባቡ እንዲያመጣጥኑ እርዷቸው።

የጥናት ልምድ እንዲያዳብሩ፣ ጊዜያቸውን እንዲያቅዱ እና ለሚፈልጉት ሙያ ቀድመው እንዲዘጋጁ አበረታቷቸው።

የልጆቻችሁን የትምህርት ጉዞ በመከታተል ብቻ ሳይሆን፣ በመምራትና በመደገፍ አብራችሁ ተጓዙ።

ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚያጠፉትን ሰዓት ወደ መጽሐፍ ንባብ፣ ትምህርት ነክ ይዘቶች፣ አዳዲስ ክህሎቶች፣ ስፖርትና ከቤተሰብ ጋር ወደ የሚያሳልፉት ጊዜ ማዞር ይችላሉ።

👍 ውድ ተማሪዎች ፦ በአንድ ትንሽ ስህተት ፤ አልያም ከጊዜና ወቅት ጋር አብሮ የሚያልፈውን የማህበራዊ ሚዲያ ዝናን ሳይሆን ከእናንተ ጋር እስከመጨረሻው የሚቀረውን እውቀት ምረጡ ፤ እውቀት ያኮራል፤ ያስከብራል !

🎉 የ2019 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ለተማሪዎች የእውቀትና የስኬት፣ ለወላጆች ደግሞ የደስታና የኩራት ዓመት እንዲሆን እንመኛለን።

መልካም የትምህርት ዘመን!

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ/ም

#TikvahEthiopiaFamily❤️

@tikvahethiopia


STEM Students CA Result.pdf
213.1Kb
📢 በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የSTEM መርሃ-ግብር ትምህርት ተማሪዎች በሙሉ

📌 የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የSTEM መርሃ-ግብር ላይ
🎮 Level 1: Robotics for Kids and Python Programming for Kids
🔬 Level 1: Basic Science Courses
⚙️ Level 2: Engineering Courses
🛠 Level 3: STEM Innovation Project እንዲሁም
🚀 "AI and Mathematical Research" STEM Camp የትምህርት መርሃ ግብር ላይ ስትማሩ የነበራቹሁ እና ትምህርታቹሁን በአግባቡ የተከታተላቹሁ የትምህርት ውጤት በዚህ ቴሌግራም ላይ የለጠፍን ሲሆን ትምህርቱን መጨረሳቹሁን በማስመልከት ቅዳሜ መስከረም 09/2019 ዓ.ም ከ2፡30 ሰዓት ጀምሮ በ ‘AASTU Old Graduation Hall’ የመዝጊያ ስነ ስረዓት ይካሄዳል። በመሆኑም ትምህርታቹሁን በአግባቡ ያጠናቀቃችሁ ተማሪዎች በዕለቱ በ ‘AASTU Old Graduation Hall’ በመገኘት የምስክር ወረቀታቹሁን በሰዓቱ በመገኘት እንድትውስዱ በአክብሮት እንጠይቃለን።

3.7k 0 64 18 24

Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
Taking STEM Knowledge Beyond Borders
Liya Aschalew is currently studying Cloud Computing and Networking at Montgomery College in the United States. As a member of the SEGA Janihun cohort, she continues to build on the knowledge and skills she gained through the AASTU University STEM Program. Reflecting on her experience, Liya describes how the AASTU STEM course strengthened her interest and abilities in technology, robotics, and programming. The practical knowledge, creativity, and problem-solving skills she developed continue to support her academic and professional journey.
Now residing in the United States, Liya shares her passion for technology by teaching children robotics and programming. She applies the knowledge gained through AASTU to inspire young learners and encourage their interest in STEM.
https://youtube.com/watch?si=8z91A75on5jvM-PW&v=9IUf_bExZsw


Liya Aschalew, discusses her experience with the AASTU university STEM course. Ms. Aschalew, a member of the Sega, Janihun cohort, is currently residing in the United States where she instructs children in robotics and programming. She has applied the knowledge acquired through the AASTU program to her professional endeavors, effectively disseminating the impact of the course internationally.


AASTU_OFFICIAL dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የ2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪ
Call for Registration of 2019 E.C. Freshman Students


📢 በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስቴም (STEM) ማዕከል “AI and Mathematical Research” STEM Camp ስልጠና መስጠት ተጀመረ።

📌 በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስቴም (STEM) ማዕከል ከነሃሴ 25/2018 ዓ.ም (31 August 2026) እስከ ነሃሴ 29/2018 ዓ.ም (04 August 2026) ድረስ የተዘጋጀው የ “AI and Mathematical Research” STEM Camp መርሃ ግብር ዛሬ ነሃሴ 25/2018 ዓ.ም መስጠት ተጀመረ። በዚህ የትምህርት መረሃ ግብር ለስልጠና የተመለመሉ ሰልጣኞች ከዚህ በፊት በማዕከሉ በሌቨል 2 ወይም 3 የተማሩ ወይም የፓይተን ትምህርት ወስደው ከነበሩ ተማሪዎች ውስጥ የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን እንዲሁም የ12ኛ ማጠቃልያ ፈተና የተፈተኑትን ተማሪዎች 40 ተማሪዎች ናቸው።

📆 በተጨማሪም ማዕከሉ አዘጋጅቶት የነበረው የ5 ሳምንታት የስቴም የትምህርት መረሃ ግብር ከ650 ተማሪዎች በላይ አሳትፎ የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡም በማዕከሉ ለተሰጡት ለሁሉም የክረምት ስልጥናዎች የመዝጊያ መረሃ ግብር የሚኖር መሆኑ በአክብሮት እንገልጻለን።




ASTU ተማሪ📚 dan repost
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ የመግቢያ ፈተና ምዝገባ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገባችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን የመግቢያ ፈተና በኦንላይን በመስጠት ለ2019 ዓ.ም መቀበል ይፈልጋሉ፡፡

የትምህርች ዘርፎች
በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች

ለትምህርት መስኮች ዝርዝር 👇
https://www.facebook.com/share/p/19EMVmakWg/ or
https://www.facebook.com/share/p/18zZo4rxUj/

የምዝገባ ጊዜ
ከነሐሴ 25 እስከ ጳጉሜን 03/2018 ዓ.ም ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ

የምዝገባ ቦታ
የምዝገባ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች በኦንላይን https://stuoexam.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et / www.astu.edu.et በመጠቀም መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቀን የምዝገባው ጊዜ ካበቃ በኋላ ይገለጻል ተብሏል።

ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ
በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ።

በቂ አመላካቾች የሌሉባቸው የፈተና ጣቢያዎች በቅርበት ወደሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሊታጠፉ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

🔔 አመልካቾች የመግቢያ ፈተና በሚሰጥባቸው የትምህርት አይነቶች ማለትም (ከ9-12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብ እና እንግሊዝኛ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ ዩኒቨርሲቲዎቹ መክረዋል።

አመልካቾች ለፈተና ስትቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት፣ የፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

@astu_temari


To Be Post.pdf
100.2Kb
📢 በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስቴም (STEM) ማዕከል “AI and Mathematical Research” STEM Camp ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

⏰ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስቴም (STEM) ማዕከል ከነሃሴ 25/2018 ዓ.ም (31 August 2026) እስከ ነሃሴ 29/2018 ዓ.ም (04 August 2026) ድረስ  “AI and Mathematical Research” STEM Camp ለ30 ተማሪዎች ያዘጋጀ እና ተማሪዎችም ሲመዘገቡ መቆየታቸው ይታወቃል። ስለሆነ መስፈርቱን የሚያማሉ የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን እንዲሁም የ12ኛ ማጠቃልያ ፈተና የተፈተኑትን ብቻ የተቀበልን ሲሆን ከተመዝጋቢው ቁጥር ብዛት አንጻር ሌላ ተመሳሳይ ፕሮግራም በቅርቡ ስናዘጋጅ የቀሩ ተማሪዎችን የምናስተናግድ ይሆናል።

📆 በዚህኛው ዙር የተቀበልናቸው የተማሪውች ስም ዝርዝር በዚህ ቴሌግራም ላይ ያያያዝን ሲሆን ትምህርቱ የሚጀምረው ሰኞ ነሃሴ 25/2018 ዓ.ም ስለሆነ በዕለቱ ጠዋት 3፡00 ሠዓት ላይ በዩንቨርስቲው ግቢ ህንጻ ቁጥር 72 እንድትገኙ በአክብሮት እናሳስባለን።


The hackathon event , Open Source in Energy Access Symposium for AASTU STEM students, is open to participants from Kigali, Rwanda.   Hackathon participants can initially attend remotely, with finalists being given the opportunity to present during the October conference from 26-27, 2026.  Kindly help disseminate the announcement within the STEM Center specially for Level three students .


🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ  ስቴም (STEM) ማዕከል “AI and Mathematical Research” STEM Camp ያዘጋጀ ስለሆነ ለመማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስቴም (STEM) ማዕከል ከነሃሴ 25/2018 ዓ.ም (31 August 2026) እስከ ነሃሴ 29/2018 ዓ.ም (04 August 2026) ድረስ  “AI and Mathematical Research” STEM Camp ለ30 ተማሪዎች ያዘጋጀ ስለሆነ መማር ፍላጎት ያላቹህ ከዚህ በፊት አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ  ስቴም (STEM) ማዕከል በሌቨል 2 የተማራቹሁ ወይም የፓይተን ትምህርት ስለመማራቹሁ መረጃ ያላቹሁ ተማሪዎች  እንዲሁም ዘንድሮ የ12ኛ ማጠቃልያ ፈተና የተፈተናቹሁ ተማሪዎችን ጨምሮ  
✅ 2018 ዓ.ም የትምህርት ቤታቹህ ሪፖርት ካርድ (ውጤት)
✅ የትምህርት  ቤት መታወቂያ ኮፒ 
✅ ከዚህ በፊት አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ  ስቴም (STEM) ማዕከል በለቨል 2 እና በላይ የተማራቹሁ ወይም የፓይተን ትምህርት ስለመማራቹሁ የሚገልጽ ማስረጃቹሁን በአንድ ላይ ፋይል (📌 Merged    PDF File) በማድረግ  በዚህ (https://forms.gle/jFGMahtNH3TtC2P56) ጎግል ቅጽ ላይ በመሙላት እንድትመዘገቡ    በአክብሮት እንጠይቃለን። 
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔

4.8k 0 66 13 14











LEVEL 3 Advanced project የምትሰሩ ተማሪዎች ነገ እሮብ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ስቴም እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡


ለLEVEL 3 ተማሪዎች በሙሉ
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
LEVEL 3 Group 1 የምትመጡበት ቀን እሮብ ሲሆን÷
LEVEL 3 Group 2 ደግሞ ቅዳሜ መሆኑን እናሳውቃለን
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.