• ህፃናት ልጆቻችሁን በተለይ ሴቶችን ልታስተምሯቸው የሚገቡ ነጥቦች፡ (ለሌሎች ወላጆችም # Share አድርጉ)
፡
ህፃናት ሴቶች ብቻ ሳይሆን ወንዶችም እየተደፈሩ ያለበት አስቀያሚ የአኺሩ ዘመን የመጨረሻው ግዜ ላይ ነን። እንደ ቀልድ ችላ የምትሏቸው ልታስጠነቅቋቸው የሚገቡ ነጥቦችን ልብ በሉ፡
፡
1: ሴት ህፃናት ልጆቻችሁን የማንም ታፋ ላይ እንዳይቀመጡ ተቆጧቸው (አጎትም ይሁን የማንኛውም ዘመድ ታፋ ላይ እንዳይቀመጡ አስጠንቅቋቸው
፡
2: ልጆቻችሁ 2 ዓመት ከሞላቸው ቡኃላ ልብሳችሁን በነሱ ፊት አትቀይሩ
፡
3: በሰፈር በጎረቤት ወይም በዘመድ ማንም ሰው ልጆቻችሁን
# ባሌ ወይም # ሚስቴ ወይም የእገሌ ባል የእገሌ ሚስት እያለ እንዳይቀልድ አድርጉ
፡
4: ልጆቻችሁ ለጨዋታ ሲወጡ ከማን ጋር እንደሚጫወቱ በሚገባ እወቁ እድሚያቸው ትንሽ ከፍ ያሉ ጎረምሶችና ኮረዶች ወደ ወሲብ የሚገፋፉ ጨዋታዎችን ከትምህርት ቤት ለምደው ስለሚመጡ ምን እንደሚያጫውቷቸው ማወቅ አለባችሁ
፡
5: ለጉርምስና የደረሱ ልጆቻችሁን ስለ ወሲብ ምንነት በትክክለኛው መንገድ አስተምሯቸው። እናንተ በትክክለኛው መንገድ ካላስተማራችኋቸው ማህበረሰቡ በተሳሳተ መንገድ ያስተምራቸዋል
፡
6: የሚመለከቷቸውን የካርቶን ፊልሞች ይዘት አስቀድማችሁ ተመልከቱ። በተለይ አሁን ላይ የሚሰሩ የአኒሜሽን ፊልሞች ለአዋቂዎች የሚሰሩ (የወሲብ ቃላትን ልቅ የሆኑ ንግግሮችን በግልፅ የሚያስተላልፉ) ናቸው
፡
7: ዕድሚያቸው ከ3 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆችን የመፀዳጃ አካላታቸውን ራሳቸው እንዲያጥቡ ካካም ሲሉ ራሳቸው እንዲጠርጉ አስተምሯቸው። ከእነሱ ውጭ ማንም የቅርብ ሰው ይሄንን እንዳያደርግ አስጠንቅቋቸው ይሄ እናንተንም ይጨምራል በደንብ አስተምራችኋቸው በራሳቸው እንዲጠናቀቁ አስተምሯቸው
፡
8: በቤት ውስጥ የሚከፈቱ ሙዚቃዎች፣ ፊልሞችና ድራማዎችን ይዘት በጥንቃቄ አስተውሉ። ስለፍቅር እና ስለተቃራኒ ፆታዎች በግልፅ የሚወራባቸውን ፕሮግራሞች በፍፁም አትክፈቱ። በተለይ በአሁን ሰዓት የሚወጡ ዘፈኖች፣ ድራማዎችና ፊልሞች በጠቅላላ ያለ ጥናት የሚወጡ ልጆችን የሚያበላሹ ናቸው በተለይ የአማርኛ ፊልሞች መንገድ ከሳቱ ቆይተዋል።
፡
9: ልጆቻችሁ በቤተሰባችሁ በብዛት ስለሚመጡ የቅርብ ሰዎች የሚነግሯችሁን ሳትንቁ አዳምጧቸው።
፡
10: የማንንም ሞባይል ለጌም እንዳይጠይቁ አድርጓቸው። ነውር እንደሆነ አስተምሯቸው።
፡
11: ያለ ዕድሚያቸው በፍፁም ስልክ አትስጧቸው። ከተጫወቱም በእናንተ በወላጆቻቸው ስልክ ብቻ እንዲጠቀሙ አድርጉ።
፡
12: የሚጫወቷቸውን የቪዲዮ ጌሞችም በደንብ አስተውሉ እንደ አኒሜሽን ፊልሞች በካርቶን የተሰሩ ልቅ ለህፃናት የማይሆኑ ጌሞችን በኮምፒውተርም በስልክም በታብሌትም እንዳይጠቀሙ አጥፉባቸው። እንደነ ቫይሲቲ ያሉ ጌሞችን የኢትዮጵያ ህፃናት በስፋት ይጫወታሉ ይሄ መሆን የለበትም።
፡
13: በስልኮቻችሁ ከትዳር አጋራችሁ ጋር የተነሳችኋቸውን የግል ፎቶዎች ልጆቻችሁ በፍፁም ማየት የለባቸውም።
፡
14: ሴቶች ልጆች ራሳቸውን የሚያጋልጡ ልብሶች ቤት ውስጥም ቢሆን እንዳያስለምዱ ማስተማር ከተቻለ ከልጅነታቸው ሂጃብንም እንግዳ ሲመጣ እንዲለብሱ ማስተማር
፡
፡
ከነዚህ ውጭ ሌሎች ችላ የምትሏቸውን ነገሮች ትኩረት ሰጥታችሁ ልጆቻችሁን በሚገባ እና በስርዓት ማሳደግ ኃላፊነታችሁ በመሆኑ ለሰከንድም መዘናጋት የለባችሁም።
፡
፡
በተረፈው ዱዓ አድርጉላቸው።
፡
©አይስክሬሙ እንዳጠናቀረው
©ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa