ኩሉ ቢዳዓቲን ዶላላ ምን ማለት ነው
አንዳንድ ካለ ዒልም ለተመቻቸው አጀንዳ ብቻ ፈትዋ እንደሚሰጡት ሰዎች ነው?!
የቢድዐው ስለት ከሲራጥ ሲቀጥን
ክፍል አንድ
====================
"እጅግም ስለት ይቀዳል አፎት፤ አጅግም ብልሃት ያደርሳል ከሞት"
ሀገርኛ ብሒል
"እጅግም ጡሃር ንጃስ ያመጣል"
አንድ የወሎ ሸህ
አንዳንድ ሁለት ገፅ ቀርተው ስለ ቢድዐ ሚናገሩ ሰዎች ''ኩሉ ቢድዐቲ ዶሏሏ ..." ....ብሎ የጀሃነም ካታሎጉን መዘርዘር ይቀጥላሉ.....ወንድሜ በዚህ ሀዲስ ላይ የትኛውም ሙስሊም የሶሒነት ጥያቄ አያነሳም...ይኸ የረሱል(ሰዐወ) ንግግር ነው....ይህንን ሀዲስ ግን የሀዲሶች ሁሉ አልፋና ኦሜጋ ስታደርገው ነው ችግር የሚፈጠረው...ምን መሰለህ ችግሩ..."ሁሉም ፈጠራ ጥመት ነው" [ኩሉ ቢድዐቲ ዶሏሏ]ብለህ የጀሃነም ደላላነትህ ላይ ታንቄ እሞታለሁ ስትል...የቢድዐው ስለት የሚያስተርፈው የለም.... ...ከረሱል(ሰዐወ) ህልፈት በኋላ መስጊድ ውስጥ ሰዎች በኡበይ ኢብኑል ከዐብ ኢማምነት ሲሰግዱ ሰይዱና ዑመር(ረ.ዐ) አገኟቸውና "ኒዕመቲል ቢድዐቱ ሀዚሂ"... አሉ...ሰምተሃል! ዑመር ኢብኑል(ረዐ) ኸጣብ፤ ዑመሩል ፋሩቅ... ናቸው ይህንን ያሉት...በግልፅ 'ቢድዐ' ብለው
በነገራችን ላይ 'ቢድዐ' የሚለው ቃል ጥሬ ትርጉም "ፈጠራ" (innovation) ማለት ነው። ከአላህ ሰሞች አንዱ "በዲዕ" ነው፤ መሠል የሌላቸው ነገሮች ፈጣሪ ማለት ነው....ይህንን ጥሬ ትርጉም ይዘን "ኩሉ ቢድዐቲ ዶሏሏ፤ ኩሉ ደሏሏቲ ፊ ናር" ብለን ስንገግም...የቢድዐው ስለት ማንንም አያስተርፍም....በነብዩ የሕይወት ዘመን ቁርዓን በመፅሐፍ መልክ አልተዘጋጀም....በሰይዱና ዑመር(ረ.ዐ) ጎትጓችነት...ሰይድና አቡበከርሲዲቅ (ረ.ዐ) ቢድዐ ሰሩ...ቁርዓኑን በመፅሐፍ መልክ ጠረዙ፤...ሰይዱና ዑስማን ኢብኑ ዐፋን(ረ.ዐ)...ነብዩ ያላደረጉትን የጁምአ የመጀመሪያ አዛን በማስደረግ ቢድዐ ሰሩ...ሰይዱና አሊይ(ረዐ) በየህያ ኢብኑ የዕመር አማካኝነት የቁርአን ነጠብጣብና ተሽኪል(ፈትሃ፣ ኪስራ...)በመጨመር ቢድዐ (ፈጠራ) አሰፋፉ....ወንድሜ በዚህ አያያዝ የቢድዐው ቁልቁለት ማቆሚያው ሩሩሩሩቅ ነው....የመስጅድ ሚናሬት ፣ የመስጅድ ምንጣፍ ፣ማይክራፎን፣ የኢማሙ ሚህራብ ፣በግመል ና በቅሎ ሳይሆን በመኪና መሄድ፣ በእጅ ሳይሆን በማንኪያ መብላት፣ በስንዴ ቂጣ ፈንታ እንጀራ መብላት ፣ ቀሚስ(ጀለቢያ) እንጂ ጂንስ ማድረግ ፣ ሸበጥ ትቶ እስኒከር ማድረግ፣ በሲዋክ ምትክ ኮልጌት መጠቀም፣በሲዲ ሃዲስ ማሳተም....እያልክ ክሩን ስትተረትረው...አዳዲስ ፈጠራ ሁሉ ጥመት፣ ሁሉም ጥመት ደግሞ ወደ እሳት ገቢ ይደረጋልና ጀነት ፆም ማደሯ ነው....
እና ምን ተሻለ?
*****
ወንድሜ(ለምን ግን እህቴ አላልኩም?)....የአረብኛን ትርጉም ማወቅ ማለት ቁርአንና ሀዲስ ማወቅ ማለት አይደለም ለዚህ ነው ከተፍሲር በፊት ነህው (የቋንቋ ህግጋትና ሰዋሰው) ተማር የሚባለው። የቁርአንና የሀዲስ መልዕክት ና የገለፃ አይነት ፣ስልትና ክብደት(ዐምና ኻስ፣ ናሲኽና መንሱኽ ፣ ሙጥለቅና ሙቀየድ) በወጉ ገብቶህ እንጂ እንደወረደ ነፃ ትርጉም ተጠቅመህ የምትተነትን ከሆነ አተናተንህ እርስ በእርሱ እየተጋጨ ዘላለም ስትወዛገብ ትኖራለህ...
ለምሳሌ 'ኩሉ' የሚለውን ቃል ስትተረጉም ቀጥታ ትርጉም ማለትም ኩሉ=ሁሉም(All) ብለን ስንቀጥል...ሱረቱል ዩኑስ ላይ [10፥47] ... ሲል ...ነገ የውመል ቂያማ መልዕክተኛ አልተላከልንም ብለው የሚከራከሩትን የት ታደርጋቸዋለህ?...ሱረቱ ፋጢር[35፥22] ......ሲል ኩሉ=ሁሉም(All) ከሆነ የመርዛማዎቹንም ሥጋ ይጨምራል ማለት ነው?....ሱረቱል አህቃፍ[46፥25] ለአድ ህዝቦች የተላከችውን ነፋስ.........ሲል ኩሉ=ሁሉም ከሆነ ቤቶቻቸውስ?ተራሮቹስ (ይግረምህ ሲል አለፍ ብሎ አዛው ላይ ...ከመኖሪያዎቻቸውም በስተቀር ምንም የማይታዩ ኾኑ ይላል).....ሌላም አብነት ልጨምርልህ....አቡ ሙሳ አል አሽዓሪይ ባወሩትና ቲርሚዚይ በዘገቡት ሀዲስ ረሱል (ሰዐወ) [ ﻛﻞ ﻋﻴﻦ ﺯﺍﻧﻴﺔ ] ... ሲሉ ኩሉ=ሁሉም (All) ካልክ ...የነብያት ዓይንስ?
መቼም ከሪያዱ ሷሊሂን አዘጋጅ፥ ኢማም አን ነወዊህ እበልጣለሁ አትለኝም።ኢማም አን-ነወዊይ ሰሒሕ ሙስሊምን የተነተኑበት መፅሐፋቸው ውስጥ (በጥራዝ 6፤ ገፅ 154) እንዲህ አሉ፦ ነብያችን(ሰዐወ) ﻭﻛﻞ ﺑﺪﻋﺔ ﺿﻼﻟﺔ ያሉት ﻋﺎﻡ ﻣﺨﺼﻮﺹ ‹ጠቅላይ ውስን›› ነው። ማለትም ጥሬ ቃሉ ጠቅላይ ሲሆን ትርጉሙ ግን ውስን ነው (በሆነ ነገር የተወሰነ ነው)...Universal thing mentioned in the sense of specific...ወይንም ኩሉ=አብዛኛው (most) ማለት ነው።
አንድ ሀዲስ ላይ ካልተቸነከርኩ ብለህ ነው እንጂ ይሄም አለ.......
ክፍል ሁለት ይቀጥላል....
©FUAD YASIN
©ABDURAHIMAN
@Ab_Mustefa