ዓባይ ባንክ ከሲቲ ኤክስፕረስ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
..............................
ዓባይ ባንክ ከሲቲ ኤክስፕረስ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅት ጋር የሐዋላ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱን ወ/ሮ ጽጌ አያሌው የዓባይ ባንክ የዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት ዋና መኮንን እና አቶ ሰዒድ አሕመድ የሲቲ ኤክስፕረስ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡
በፊርማው ሥነ - ሥርዓት ላይ ወ/ሮ ጽጌ አያሌው በሰጡት አስተያየት ስምምነቱ በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቀላሉ እና ህጋዊ በሆነ መንገድ ገንዘብ ለመላክ የሚያስችላቸውን አማራጭ ለማስፋት እና የውጭ ምንዛሬ ፍሰቱን በማጠናከር በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አስተዋፅኦ ለማበርከት ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡
አቶ ሰኢድ አሕመድ በበኩላቸው በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፈጣን እና አስተማማኝ የሐዋላ የባንክ አገልግሎት ሥርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል የደንበኞችን እርካታ ለመጨመር እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡
ሲቲ ኤክስፕረስ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅት በዋናነት በጅቡቲ እና ሶማሊያ አገራት በመሥራት ላይ የሚገኝ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅት ነው፡፡
ዓባይ ባንክ ከሞጆ፣ ኢትዮዳሽ፣ ዌስተርን ዩኔን፣ ቲዩንስ፣ መኒግራም፣ ድሃብሺል፣ ትራንስ ፋስት፣ ሪያ፣ ዩ-ረሚት፣ ዎርልድ ረሚት፣ ሺፍት እና ሪሚትሊ ከተባሉ ዓለምአቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ጋር በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!