«"እኔ ብቻ ትክክል ነኝ" የማለት አባዜ!"»
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈
በሁሉም መልኩ ተበዳይና ሐቅ ላይ ነኝ የሚል ግለሰብ እጅግ የበረከተ ነው። ነገሩ ግን እንደሚሞግተው በፍፁም አይሆንም። እንደውም ይህ ግለሰብ በአንድ በኩል ሐቅ ሊኖረውና በከፊል ደግሞ በደልና ባጢል ሊኖርበት ይችላል። ባላንጣው ዘንድ ደግሞ ሐቅና ፍትህ ሊኖር ይችላል። አንድን ነገር መውደድህ እውርና ዲዳ ያደርጋል። የሰው ልጅ ነፍሱን በመውደድ ላይ የተፈጠረ ነው። የነፍሱን መልካሟን እንጂ ሌላን አይመለከትም። ተቃራኒውን ይጠላል። የተቃራኒውን መጥፎ ነገር እንጂ አይመለከትም። እንደውም ራስ ወዳድነቱ በርትቶበት የነፍሱን ክፋት እንደ መልካም መመልከት ይጀምራል። ልክ አሏህ እንዳለው፦
{أفمن زين له سوء عمله فرآه حسناً}
سورة فاطر
"መጥፎ ስራው የተሸለመለትና መልካም አድርጎ ያየው ሰው (አላህ እንዳቀናው ሰው ነውን?)"
በዚህም ባላንጣው ላይ ያለው ጥሩ ጎን መጥፎ እስኪመስለው ድረስ ጥላቻው ይበረታል። ለዚህም ሲባል እንዲህ ተብሏል "በጥላቻ ዓይናቸው ተመለከቱት እንጂ በመልካም ዓይን ቢመለከቱ ኖሮ የጠሉትን ነገር ባወደሱ ነበር!"
☞ኢብኑል ቀይዪም
https://t.me/abdurezaq27