✍
ነገ ስትጠየቅ ድንጋጤው እንዲቀንስልህ;
ዛሬ ተጠያየቅ!!
ፉደይል ኢብኑ ኢያድ አላህ ይዘንለት ከአንዱ ጋ መንገድ ላይ ተገናኝተው እንዲህ ሲል ጠየቀው……
ፉደይል…… "እድሜህ ስንት ነው?"
ሲል
ሰውየው…… "ስልሳ ዓመቴ ነው" አለ።
ፉደይል…… "ስልሳ ዓመት በሙሉ ወደ ጌታህ እየሄድክ ነው አሁን ደግሞ ልትደርስ ተቃርበሀል።"
አለው
ሰውየው…… በመደናገጥ ስሜት
"إنّا لله وإنّا إليه راجعون"
"እኛ የአላህ ነን: ወደሱም ተመላሾች ነን።" አለ
ፉደይል…… "የዚህን ትርጉም ታቃለህን?"
"ይህ ማለት እኮ እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ: መመለሻዬም ወደሱ ነው ማለት ነው።
የአላህ ባሪያ መሆኑና ወደ አላህ እንደ ሚመለስ ያወቀ የሆነ ሰው; አላህ ፊት እንደ ሚቆም ሊያውቅ ይገባዋል።
አላህ ፊት እንደ ሚቆም ያወቀ የሆነ ሰው; አላህ ፊት እንደ ሚጠየቅ ሊያውቅ ይገባዋል።
አላህ ፊት እንደ ሚጠየቅ ያወቀ ሰው ደግሞ ለጥያቄው ምላሽ ማዘጋጀት ይገባዋል።" አለው
ሰውየው…… ከቅድሙ የበለጠ ደነገጠና "እሺ መፍትሔው ምንድን ነው?"
ብሎ ጠየቀው
ፉደይል…… "በጣም ቀላል ነው"
አለው
ሰውየው…… "ምንድን ነው እሱ?"
ሲል ጠየቀ
ፉደይል……
"تُحسِن فيما بقي، يُغفر لك ما مضى، فإنّك إنْ أسأتَ فيما بقي، أُخِذْتَ بما مضى وبما بقي."
"በተቀረህ እድሜ መልካም ስራ ስራበት; ያለፈውን ስህተትህ ትማራለህ።
በተቀረው እድሜህ መጥፎ ከሰራህበት ግን ባሳለፍከውም በተቀረውም ትያዛለህ።"
አለው።
[جامع العلوم والحكم لابن رجب (1 / 383)]
🌙ወንድሜ ሆይ………
አንተስ ከእድሜህ ስንት ነው ያሳለፍከው??
በምን መልኩ ነው ያሳለፍከው??
ወደ ጌታህ እንደምትመለስ፣
ከሱም ፊት እንደ ምትቆምና እንደ ምትጠየቅ ታውቃለህን??
ለጥያቄው ያዘጋጀፀው ምላሽህስ ምን ይመስላል??
ሁላችንም ለነፍስያችን ይህንን ጥያቄ በመጠየቅ ራሳችንን ሂሳብ እናድርግ እና በተዉበትና በኸይር ስራ ለአሄራ እንዘጋጅ!!
https://t.me/abumerymadama