Bahiru Teka dan repost
👉 ሌራ ተረኛዋ የተውሒድ ጮራ አሰራጭ
በምእራብ ስልጤ ዞን የምትገኘው ሌራ ከተማ ተረኛዋ የታደለች የተውሒድ ጮራ አሰራጭ ሆናለች ። የሌራ አል – ኢማሙ አሕመድ መስጂድ የተውሒድና ሱና መሻኢኽና ኡስታዞችን እንዲሁም ዱዓቶችና እንግዶችን ለመቀበል አንፀባራቂ በለበሱ የሱና ኻዲሞች ተውቦና አምሯል ። መስጂዱ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተመሙ መሻኢኾችና ኡስታዞች እንዲሁም ዱዓቶች የተውሒድ ዘር እየተዘራበትና የብርሃኑ ጮራ እየፈነጠቀ ይገኛል ።
ሰው ምን ይለኛልን በማይፈሩ የቁርጥ ቀን ዑለሞችና መሻኢኾች ነጭ ነጩ እንቅጭ እንቅጩ እየተነገረ ነው ። የተውሒድ ሚስጢር እየተገለፀ የሽርክ ቫይረስ ላይ አጥፊ መድሃኒት እየተረጨ ነው ። ሐቅን ደብቆ አንድነት የለም, ሐቅን ደብቆ ስምምነት የለም ሐቁ ይነገራየጠላ ይጠላል የወደደ ይወዳል ። ስለተውሒድ ለተበሩክ ሳይሆን ሽርክን ለማጥፋት ማስተማር ነብያዊ ተልእኮ ነው ። በመሆኑም ሽርክን በጥቅሉ ሳይሆን በዝርዝር እየአንዳንዱ በስሙ ሌራ ላይ እየተነገረ ይገኛል ።
የሌራ ከተማ በተውሒድና ሱና መአዛ ታውዳለች ። መንገዶቿ ፣ መንደሮቿ ፣ ጋራ ሸንተረርዋ ተውሒድ ተውሒድ ይሸታሉ ። ጎዳናዎቿ የሱና አበባ ተነስንሶ ላየ ጤነኛ ልቦና ባልተቤት የደስታ ሲቃ ያሲዛል ።
ለዚህ ታላቅ ፕሮግራም መሳካት የከተማዋ የፖሊስ የፀጥታና የድርጅት ሀላፊዮች የተጣለባቸውን ህዝብን የማገልገል ሀላፊነት በቅንነት መወጣት አላህን ከማመስገን በኃላ ሊመሰገኑ ይገባል ። በቅርቡ አሊቾ ወረዳ ላይ ያየነውና አሁን ምእራብ አዘርነት በርበሬ ሌራ ወረዳ ላይ ያለው ሁኔታ የእነዚህ የሴክተር መ/ቤቶች ያሳዩት ሀላፊነትን በአግባቡ መወጣት የስልጤ ዞንን ገፅታ የሚቀይርና እሰይ የሚያሰኝ ሌሎችም ሊከተሉት የሚገባ የሚደነቅ ተግባር ነው ።
http://t.me/bahruteka