ከፈትዋ ማህደር
ጥያቄ፡- ሸሪዓን የሚጥስ ኃጢያተኛ ሰው ሙስሊሞችን ኢማም ሆኖ ማሰገድ ይችላል?
መልስ፡- አብዝሃኞቹ የአህሉ ሱና ዑለሞች ኃጢያተኛ (ዓሲ) የኢማምነት መስፈርቶችን እስካሟላ ድረስ ኢማም ሆኖ ማሰገድ እንደሚችል ይስማማሉ። ነገርግን ኢማምነቱን ይጠሉበታል። ሰዎችን መልካም ሰው ቢያሰግድ ተመራጭ ነው።
የአውሮፓው የፈትዋና የምርምር ማዕከል (المجلس الأوربي للبحوث والإفتاء/European Council for Fatwa and Research) የሰጠው ፈትዋ እንዲህ ይላል፡-
ሶላቱ ለራሱ የበቃው ሰው ሌሎች ሰዎችንም ኢማም ሆኖ ማሰገድ ይፈቀድለታል። ኢማምነት ላይ የተሻለውን ስርዐት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግር ገልጾታል። እንዲህ ይላሉ፡-
يؤم القوم أقرؤهم لكتاب الله ، فإن كانوا في القراءة سواء فأعلمهم بالسنة، فإن كانوا في السنة سواء فأقدمهم هجرة، فإن كانوا في الهجرة سواء فأقدمهم سنًا، ولا يؤمن الرجلُ الرجلَ في سلطانه، ولا يقعد في بيته على تكرمته إلا بإذنه
“ሰዎችን የአላህን መፅሐፍ ይበልጥ ያነበቡት ያሰግዷቸው። በቂርኣት እኩል ከሆኑ ሱናን ይበልጥ ያወቀው ሰው ያሰግዳቸው። ሱናም ላይ እኩል ከሆኑ ቀድሞ የተሰደደው ያሰግድ። ሂጅራ ላይ እኩል ከሆኑ እድሜው ከፍ ያለው ያሰግድ። ሰውየው ሰውየውን በስልጣኑ ቦታ ላይ አይምራው። በቤቱ ውስጥም እርሱ በሚከበርበት ቦታ ላይ ያለፍቃዱ አይቀመጥ።”
ኃጢያተኛነት የሶላትን ተቀባይነት አያሳጣም። ማንኛውንም መልካምም ሆነ ጠማማ ሙስሊም ተከትሎ መስገድ መቻሉ ከአህሉ ሱና እምነት ውስጥ ይጠቀሳል።
አንዳንዴ ደግሞ ኢማሞች ይፈፅሟቸዋል የሚባሉት ስህተቶች ልዩነት የሚፈቀድባቸው ዑለሞች የተለያዩባቸው ሃሳቦች (ኢጅቲሃዳት) እንጂ ኃጢያቶች አይደሉም። በኢስላም ውስጥ ቁርጥ ተደርገው የተቀመጡ ልዩነት የሌለባቸው ነገሮች አይደሉም።
ለምሳሌ የሱብሂ ሰላት ላይ የቁኑት ዱዓ ማድረግ/አለማድረግ፣ ልብሱ ከቁርጭምጭሚት በታች የወረደ ሰውን ተከትሎ መስገድ፣ ጺሙን የሚላጭን ሰው ተከትሎ መስገድ እና መሰል ዓሊሞች የተለያየ አቋም የያዙባቸው እና ፈትዋዎች የተለያዩባቸው ነገሮች ናቸው ብዙ ጊዜ ኢመሞች ይሰሯቸዋል ተብለው የሚጠቀሱ ስህተቶቸች። እንዲህ ዓይነት ጉዳዮች ላይ ተቃራኒ ሃሳብ ያላቸውን ሰዎች መንቀፍ እና ማብጠልጠል አይቻልም። መገሰፅ እና መምከር ግን ይቻላል። ምናልባት በጉዳዩ ላይ ሰውየው ዘንድ የተሻለ ዕውቀት ልታገኝ ትችላለህ። ስለዚህ በእነዚህ መሰል ጉዳዮች ዙርያ ተቃራኒ የሆነ ሃሳብ ያለውን ሰው መንቀፍ አይቻልም ስንል በዋናነት ደግሞ እርሱን ተከትሎ መስገድ ይበቃል ማለት ይቻላል።
አላሁ አዕለም!
https://t.me/alanisquranacademy