📌ቢድዓ የሽርክ ጓደኛ ነው
ሽርክ የጌታን ክብር ከማጓደል ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ሙሽሪኩ ወደደም ጠላም ፣ የጌታን ክብር ማጓደሉ ከእርሱ ጋር የማይላቀቅ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ሙሽሪክ ፍጹም እንደማይማር ተመስጋኝነቱ ፣ ፈጣሪነቱ ፣ ሙሉነቱ የወሰነው ጉዳይ ሆኗል - የሽርክ ባለቤት ዘወትር በአሳማሚ ቅጣት እንደሚቀጣም እንዲሁ፡፡ ከፍጡራኖች ሁሉ በጣም ጠማማ ያደርገዋል፡፡ አንድን ሙሽሪክ አታገኘውም - በማጋራቱ አላህን አልቃለሁ ብሎ ቢሞግትም - የአላህን ክብር የሚቀንስ ቢሆን እንጅ፡፡
በተመሳሳይ አንድን ሙብተዲእ አታገኘውም ፣ የረሱልን ክብር የሚያጓድል ቢሆን እንጅ - በቢድዓው ለረሱል ክብር ሰጥቻለሁ ብሎ ቢሞግትም፡፡ ተጎታች ጃሂል ከሆነ ቢድዓ ከሱና የተሻለች ወይም ከሱና ተቀዳሚ ወይም እርሷ ሱና ናት ብሎ ይሞግታል፡፡ ጮሌ ከሆነ ደግሞ በቢድዓው አላህና ረሱልን ይቀናቀናል፡፡
ከአላህ ፣ ከረሱል እና ከአማኞች ዘንድ ጎደሎዎች ፡ የሽርክ ባለቤቶች እና የቢድዓ ባለቤቶች ናቸው፡፡ በተለይም ፣ ‘የአላህና የረሱል ንግግር ባዶ ቃላት እንጅ ከእውቀት ፣ በእምነት እርግጠኛ ከመሆን የተራቆተ ነው’ በሚል አመለካከት ላይ ዲኑን የመሰረተ አካል ከሆነ፡፡
ልክ እንደዚሁ መመሳሰልን እና ለአላህ የፍጠራንን የመሰለ አካል ሊኖረው ይችላል በሚል ስጋትና ብዥታ ከፈጣሪ ላይ ሙሉ የሆኑትን ባህሪያቶችን ያራቆተ ሰው ፣ አላህ ነፍሱን በገለጸበት የተሟላ ባህሪ ተቃራኒ ጉድለትን አመጣ፡፡
ተፈላጊው አላማ ፡ እነዚህ ሁለት ጭፍራዎች በሀቂቃ የአላህን እና የመልክተኛውን መብት አጓዳዮች ናቸው፡፡ ይልቁንም እነዚህ ሁለት ጭፍራዎች ከሰዎች ሁሉ የአላህንና የረሱልን ክብር በማጓደል ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ የአላህን ክብር ማጓደልን ፣ ለእርሱ ሙሉ ክብር እንደመስጠት አስመስሎ ሰይጣን በእነርሱ ላይ አምታታባቸው፡፡ በዚህ ምክንያት ቢድዓ የሽርክ ጓደኛ እንደሆነ በአላህ ኪታብ ተገልጹዋል፡፡
قُلْ إِنَّمَا حَرَّمَ رَبِّيَ الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ وَالْإِثْمَ وَالْبَغْيَ بِغَيْرِ الْحَقِّ وَأَن تُشْرِكُوا بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا وَأَن تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
“ጌታዬ እርም ያደረገው መጥፎ ስራዎችን ከርሷ የተገለጸውንና የተደበቀውን ሐጢአትንም ያላግባብ መበደልንም ፣ ከርሱ ማስረጃ ያላወረደበትነ (ጣዖት) በአላህ ማጋራታችሁን ፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው” በላቸው፡፡
(አእራፍ፡ 33)
ሐጢያትና ድንበር ማለፍ ጓደኛ ናቸው ፤ ሽርክ እና ቢድዓም ጓደኛ ናቸው፡፡
طب القلوب : - ١٧٩-١٨٠
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة