ዕውቀት እና የዕውቀት ባለቤቶች ደረጃ
ክፍል - 8
ኡለሞችን ለመቃወም መፍጠን?!
በዚህ ኡመት በሱና ፣ በተውሂድ ፣ በፍትሃዊነት ፣ በአማና ፣ በጽናት የሚታወቁ ኡለሞችን እውነታውን ሳያረጋግጡ መቃወም አደጋው የከፋ ሊሆን ይችላል። ታዲያ እነርሱን ከመቃወም መታቀቡ መልካም የሆነ አካሄድ ነው፡፡ እውቀት ፈላጊዎች ፣ ከታላላቅ ኡለሞች አስተያየት ዘንድ የራሳቸውን አስተያየት መጠርጠር። ነገሮችን ከማረጋገጥ በፊት ለተቃውሞ አለመፍጠን፡፡
ኢማም ሻጢቢያ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል ፡
((በአማናው ፣ በእውነተኛነት ፣ በአህለል ፈድል በዲን እና አላህን በመፍራት ባለቤቶች መንገድ ላይ በመጓዝ የሚታወቅ አሊም ስለወቅታዊ ጉዳዮች ሲጠየቅ መልስ ይሰጣል፡፡ ለእነርሱ ያልተለመዱ ጉዳዮች በመሆናቸው ወይም ከአድማጩ ዘንድ ግንዛቤው በቀላሉ ባለመድረሱ ምክንያት ለተቃውሞ እና ለትችት አለመፍጠን፡፡
አስቸጋሪ ነገር ካቀረበ ፣ ቆም ብሎ ማጤን በላጭ ነው ፣ ከሚፈራው ለመዳንም ፣ ከአላማም ለመድረስ ተገቢውም ይህ ነው፡፡ ))
(“ሙዋፈቃት” ፡ 324)
ታማኝ በሆነ ፣ ሀቅን አጥብቆ በመያዝና በመልካምነቱ የሚታወቅን አሊም በተቃውሞ አለመጋፈጥ ምስጉን ከሆኑ ትዕግስቶች አንዱ ነው፡፡
ከአሊምና ከእውቀት ጋር ትእግስት የሌለው ፣ በዚህም ላይ መልካም ጽናት የሌለው እውቀትን ከአሊሞች በቀላሉ ለማግኘት አይችልም፡፡
ትዕግስት የሌለው እውቀትን ሊያገኝ አይችልም፡፡ ትዕግሰት አጥብቆ የያዘ ወደርሱ የሚገሰግስበትን ነገር በቀላሉ ማሳካት ይችላል፡፡
ኸዲር ከእርሱ ዘንድ ያለውን እውቀት ለማግኘት ለሙሳ ትእግስትን መስፈርት እንዳደረገበት አላህ በሚከተለው ቁርዓናዊ አንቀጽ ነግሮናል፡ -
قَالَ لَهُ مُوسَىٰ هَلْ أَتَّبِعُكَ عَلَىٰ أَن تُعَلِّمَنِ مِمَّا عُلِّمْتَ رُشْدًا قَالَ إِنَّكَ لَن تَسْتَطِيعَ مَعِيَ صَبْرًا
وَكَيْفَ تَصْبِرُ عَلَىٰ مَا لَمْ تُحِطْ بِهِ خُبْرًا
قَالَ سَتَجِدُنِي إِن شَاءَ اللَّهُ صَابِرًا وَلَا أَعْصِي لَكَ أَمْرًا
قَالَ فَإِنِ اتَّبَعْتَنِي فَلَا تَسْأَلْنِي عَن شَيْءٍ حَتَّىٰ أُحْدِثَ لَكَ مِنْهُ ذِكْرًا
ሙሳ ለእርሱ «ከተማርከው ነገር ቀጥተኛን (ዕውቀት) ታስተምረኝ ዘንድ ልከተልህን» አለው፡፡ (ባሪያውም) አለ «አንተ ከእኔ ጋር መታገስን በጭራሽ አትችልም፡፡ «በዕውቀትም በእርሱ ባላዳረስከው ነገር ላይ እንዴት ትታገሳለህ» (ሙሳ) «አላህ የሻ እንደ ኾነ ታጋሽና ላንተ ትዕዛዝን የማልጥስ ኾኜ ታገኘኛለህ» አለው፡፡ «ብትከተለኝም ለአንተ ከእርሱ ማውሳትን እስከምጀምርልህ ድረስ ከምንም ነገር አትጠይቀኝ» አለው፡፡
(ከህፍ 66-70)
ኢብን ሰዕድይ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል ፡ -
ሙሳ ከኸዲር ጋር ባለው ታሪክ የሚገኙ ፋይዳዎች እንደሚከተለው ግልጽ አድርገዋል ፡
((ከነዚህ ፋይዳዎች መካከል ፡ ነገሮች ብይን የሚሰጣቸው በግልጽ በታየው እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ ብይኖች ከገንዘብ ፣ ከደም እና ከሌላም ዱንያዊ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ናቸው፡፡ ሙሳ የመርከቡን መቀደድ ፣ የወጣቱን መገደል አውግዟል፡፡ እነዚህ ነገሮች በውጭ ሲመለከቷቸው (ሊወገዙ የሚገባቸው) መጥፎ ተግባራት ናቸው፡፡
ሙሳ ፣ ኸዲርን ከተጎዳኘባቸው ከእነዚህ ሁኔታዎች ውጭ ነገሮችን በዝምታ ሊያልፋቸው አልመረጠም፡፡
ሙሳ ቸኮለ፡፡ አጠቃላይ በሆነው የነገሮች ባህሪ ለማውገዝ ተሸቀዳደመ፡፡ እርሱም ለማውገዝ ሊሽቀዳደሙበት የማይገባና ትእግስት የሚያስፈልገው ወደሆነው (እርሱ ያልደረሰበት) ተቃራኒ ብይን ፊቱን አላዞረም፡፡))
(‘ተይሲሩ አልከሪሙ አርረህማን’ ፡ 5/69-70)
ኡለሞችን ከማረጋገጥ በፊት በተቃውሞ መጋፈጥ አስፈላጊ እንዳልሆነ ከሚያስረዱ ታላላቅ ማስረጃዎች መካከል በሁደይቢያ ቀን ከቁረይሾች ጋር የስምምነት ሰነድ ከተፈረመ በኋላ ሶሃቦች ከነብዩ ጋር የነበራቸው ታሪክ ነው፡፡
ከስምምነቶች መካከል ፡
1ኛ - በሙስሊሞች እና ቁረይሾች መካከል ለአስር አመታት የጦር ማቆም ስምምነት ማድረግ ፤
2ኛ ፡- ሙስሊሞች ኡምራ ሳያደርጉ ወደ መጡበት ተመልሰው እንዲሄዱ ፣ ከአመት በኋላ ግን መካ ኡምራን መስራት እንደሚችሉ ፣ ኡምራን ሰርተው ካበቁ በኋላ ለሶስት ቀን ብቻ መካ መቆየት እንደሚችሉ
3ኛ ፡ - ከቁረይሾች ወደሙስሊሞች የመጣውን ፣ ሙስሊሞች ለቁረይሾች ሊመልሱ ፣ ከረሱል ወደቁረይሽ የመጣንውን ቁረይሾች ወደሙስሊሞች ላይመልሱ
ይህን ስምምነት ሶሃቦች ተቃወሙ፡፡ አንዳንዶቹ በመቃወም “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህን ትጽፋለህ?!” አሏቸው፡፡ እርሳቸውም “አዎ! ወደነርሱ የሄደውን አላህ አርቆታል፡፡ ከእነርሱ ወደኛ የመጣውን ደግሞ ለእርሱ መውጫንና ፈረጃን ያደርግለታል” አሉ፡፡
ከብርቱ ተቃዋሚዎች መካከል አንዱ ኡመር ኢብን አልኸጧብ ነበር፡፡ የነበረውን ታረክ እንደሚከተለው ይገልጸዋል፡ ((ወደነብዩ መጣሁ ፣ “እውነተኛ ነብይ አይደለህምን?” አልኳቸው፡፡ “አዎ” የሚል ምላሽ ሰጡኝ፡፡ “እኛ በሀቅ ላይ ፣ ጠላቶቻችን ደግሞ በውሸት ላይ አይደሉምን?” አልኳቸው፡፡ “አዎ” አሉኝ፡፡ “ታዲያ ለዲናችን ውርደትን እንዴት እንሰጣለን?” አልኳቸው፡፡ “እኔ የአላህ መልክተኛ ነኝ ፣ እርሱን የምነቅፍ አይደለሁም ፤ እርሱም ረዳቴ ነው” አሉኝ፡፡ “ወደካእባ እንደምንመጣና እንደምንጦውፍ አልነገርኸንምን?” አልኳቸው፡፡ “አዎ ! ታዲያ በዚህ አመት ብየሀለሁ?” አሉኝ፡፡ “አላሉኝም” አልኳቸው፡፡ “አንተ ወደርሱ ትመጣለህ ፣ እርሱንም ትጦውፈዋለህ” አሉኝ፡፡
ወደአቡበክር መጣሁ፡፡ “አቡበክር ሆይ! ይህ ትክክለኛ ነብይ አይደለምን?” አልኩት፡፡ “ነው” አለኝ፡፡ “ታዲያ በዲናችን ውርደትን እንዴት እንሰጣለን?” አልኩት፡፡ “አንተ ሰው! እርሱ የአላህ መልክተኛ ነው፡፡ ጌታውን የሚነቅፍ አይደለም ፣ እርሱም ይረዳዋል ፣ እርካቡን አጥብቀህ ያዝ ወሏሂ እርሱ በሀቅ ላይ ነው” አለኝ፡፡ “እንደምንመጣና ቤቱን እንደምንጦውፍ ከዚህ በፊት አልነገረንምን?” አልኩት፡፡ “አዎ! ታዲያ በዚህ አመት ትፈጽማለህ ብሎሃል?” አለኝ፡፡ “አላለም” አልኩት፡፡ “አንተ ወደርሱ ትመጣለህ ፣ እርሱንም ትጦውፈዋለህ” አለኝ፡፡
(ቡኻሪ ዘግቦታል ፡ 3/182)
በዚህ ሐዲስ የምንገነዘበው ኡመርም ይሁን ሶሃቦቹ ነገሩ ስህተትና በውስጡ መጥፎ ነገር ያለበት መስሏቸው በረሱል ላይ ተቃውሞ አቅርበዋል፡፡ እርሱ ግን ትክክል እና በአጠቃላይ ውስጡ መልካም ነበር፡፡
ኢማም አዙህር - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግሯል ፡
((ከዚህ በፊት ትልቅ ድል ተገኝቶ አያውቅም ልክ እንደርሱ - (እንደ ሁደይቢያው ስምምነት) …))
በወቅቱ የሁደይቢያ ስምምነት ተቃውመው የነበሩ ሰዎች የስምምነቱ ጥቅም በኋላ ግልጽ ሆኖላቸዋል፡፡ ከተቃውሟቸውም ጸጸት አድርገው ተመልሰዋል፡፡ ኡመርም የነፍሱን ስህተት ተገነዘበ፡፡ አላህ ስህተቱን እንዲምረው ተስፋ በማድረግ መልካም ስራዎችንም በብዛት ይሰራ ነበር፡
ኡመር ብን አልኸጧብ የሚከተለውን ተናግሯል ፡
"ما زلت أصوم وأتصدق وأعتق من الذي صنعت كلامي الذي تكلمت به يومئذ – يعني يوم الحديبية – حتى رجوت أن يكون خيرا"