ዕውቀት እና የዕውቀት ባለቤቶች ደረጃ
ክፍል - 9
የሱና ኡለማዎችን ከመተቸት መጠንቀቅ
የሱና ኡለሞችን በመጥፎ ማንሳት ፣ መዝለፍ የጠማማዎችና በስህተት ላይ ያልሉ ሰዎች ጎዳና ነው፡፡ ይህም ፣ የሱና ኡለማዎችን ስንተች የታሰበው አካላቸውን ሳይሆን የምንተቸው ዲኑን እንደሆነ መገንዘብ አለብን፡፡ የምንተቸው የተሸከሙትን ሸሪዓዊ እውቀት ፣ ተውሂድና ሱናን ፤ የምንተቸው ወደርሱ የተጠጉበትን ከአሏህ የወረደ የኢስላም ሐይማኖት መሆኑን መዘንጋት የለብንም።
የሱና ኡለማዎችን መተቸት ሀራም ነው፡፡
ረሱል ﷺ የሚከተለውን ተናግረዋል ፡
"إن دماءكم وأموالكم وأعراضكم عليكم حرام كحرمة يومكم هذا في شهركم هذا ، في بلدكم هذا"
“ደሞቻችሁ ፣ ገንዘቦቻችሁ ፣ ክብሮቻችሁ በእናንተ ላይ ሀራም ነው፡፡ ልክ ይህ ቀናችሁ እርም እንደሆነው ፣ ይህ ወራቸሁ (ዙልሂጃ) እርም እንደሆነው ፣ ይህ አገራችሁ (መካ) እርም እንደሆነው ሁሉ፡፡”
ዲንን መተቸቱ ፣ የዚህን ኡመት ቀደምቶች ፣ እነርሱንም በመልካም የተከተሉትን ጭምር መተቸት በመሆኑ ሀራምነቱ የበረታ ይሆናል፡፡
ሰለፎች ይህን በመገንዘባቸው ሶሃባን የሚተችን አካል ዚንዲቅ (ሙናፊቅ) ይሉት ነበር - ምክንያቱም ሶሃባን መተቸት እስልምናን ወደመተቸት ስለሚያደርስ ፤ የረሱልን ﷺ ክብር የሚቀንስ በመሆኑ፡፡
አቡ ዙርዓ የሚከተለውን ተናግሯል ፡
(ከረሱል ሶሃቦች የአንዱን ክብር ሲያጓድል ከተመለከትህ ይህ ሰው ዚንዲቅ መሆኑን እወቅ፡፡ ምክንያቱም ረሱል ከእኛ ዘንድ ሀቅ ናቸው ፤ ቁርዓን ሀቅ ነው ፤ በእርሱ የመጡበትም ሀቅ ነው፡፡ ይህን ቁርዓንና ሱና ወደኛ ያደረሱት የአላህ መልክተኛ ባልደረቦች ናቸው፡፡ የሚፈልጉት ሸሂዶቻችንን ለመተቸት ነው፡፡ ቁርዓንና ሱናን ለማበላሸት ነው፡፡ ሊትተቹ የሚገባቸው እነርሱው ናቸው፡፡ እነርሱ ዚንዲቆች (ሙናፊቆች) ናቸው፡፡)
(ኸጢብ አልበግዳዲ ፣ ‘አልኪፋየቱ ፊ ኢልሚሪዋየቲ’ ፡ 49)
(ሀፊዝ ብን ሀጀር ፣ ‘አልኢሷባ’ ፡ 1/10)
ኢማም አህመድ የሚከተለውን ተናግረዋል ፡
"إذا رأيت الرجل يغمز حماد بن سلمة فاتهمه على الإسلام ، فإنه كان شديدا على المبتدعة"
( አንድ ሰው ሀም’ማድ ብን ሰለማሀን ሲተች ከተመለከትህ በእስልምናው ጠርጥረው - እርሱ በሙብተዲኦች ላይ ብርቱ ነውና))
(‘ሲየር አእላም አንኑበላ’ ፣ ዘህብይ ፡ 7/450)
የህያ ብን መዒን የሚከተለውን ተናግሯል ፤
"إذا رأيت الرجل يتكلم في حماد بن سلمة وعكرمة مولى ابن عباس فاتهمه على الإسلام"
((አንድ ሰው በሀማድ ብን ሰለማ ፣ በኢብን አባስ መውላ ኢክሪማ ላይ (መጥፎ) ሲናገር ከተመለከትህ ፣ በእስልምናው ላይ ተጠራጠረው))
('ሸርህ ኡሱል ኢእቲቃዲ አህሊ ሱነቲ ወልጀማአቲ' ፡ አልላለካኢይ : 3/514)
በሙስሊም ላይ ግዴታው ተገቢ ያልሆነን ንግግር ከመናገር ምላስን መጠበቅ ነው፡፡ ሲናገር በእውቀትና በማስረጃ ላይ ተንተርሶ መናገር አለበት፡፡
ኡለሞች በግልጽ ስህተት ፈጽመው ከሆነ ሸሪዓዊ መንገድን ተከትሎ እርምት መስጠት ይቻላል፡፡ በግልጽ የፈጸሙት ስህተት ከሌለ ፣ በውስጣቸው ያለውን ወደአላህ ማስጠጋት ነው፡፡
ኡመር ኢብን አልኸጧብ ይህን አስመልክቶ የሚከተለውን ተናግሯል
“ሰዎች በአላህ መልክተኛ ዘመን የሚያዙት በወህይ ነበር፡፡ ወህይ ተቋርጧል፡፡ አሁን የምንይዛችሁ ከተግባራችሁ ለእኛ ግልጽ በሆነው ነው፡፡ መልካምን ግልጽ ላደረገልን እውነት እንለዋለን ፣ እናቀርበዋለን፡፡ በውስጥ ባለው አንዳች መብት የለንም፡፡ ውስጡን አላህ ይመርምረው፡፡ መጥፎ ነገር ግልጽ ያደረገልንን አናምነውም ፣ እውነት አንለውም - ውስጤ መልካም ነው ቢል እንኳ፡፡”
(ቡኻሪ ፡ 3/221)
አንዳንድ ጊዜ የሱና ኡለሞችን ተችቶ የሚገኘው ከዚያው ከጎናቸው የማይለይ በእውቀት የተበለጠ ጓደኛቸው ሊሆን ይችላል።
ኢማን አህመድ ይህን አስመልክቶ የሚከተለውን ተናግረዋል ፡
"اعلموا رحمكم الله تعالى أن الرجل من أهل العلم إذا منحه شيئا من العلم ، وحرمه قرناؤه وأشكاله حسدوه ، فرموه بما ليس فيه ، وبئست الخصلة في أهل العلم"
رواه البيهقي في : "المناقب" (2\259)
“እወቁ - አላህ ይዘንላችሁ - ከእውቀት ባለቤት መካከል ለአንድ ግለሰብ (አላህ) ከእውቀት ከለግሰው ፤ የእርሱ ጓደኞች የሆኑት ደግሞ (ከዚያ እውቀት) ካልተሰጡ በእርሱ ላይ ይመቀኙታል፡፡ (ከዚያ በኋላ) እርሱ ንጹህ በሆነበት ነገር ይተቹታል፡፡ በእውቀት ባለቤቶች ውስጥ (እንዲህ አይነቷ) ባህሪ ከፋች!”
ዲን ለማበላሸት በውስጥ ተሰግስገው የተቀመጡ ሙናፊቆችን ፣ የአሊም ምቀኞችንና የሱና ጠላቶችን ኡለሞቹ ጠንቅቀው እንዴት አያውቋቸውም? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ይህ ፣ የእነርሱን መብት የሚቀንስ አይደለም፡፡ በዚህ ኡመት ሙናፊቆች ወይም ዚንዲቆች ይኖራሉ፡፡ ኡለሞች ላያውቋቸው ይችላሉ፡፡ የእነርሱ ባህሪ ከእነርሱ ላይ መሰወሩ እንደነውር ታይቶ ሊተቹበት የሚገባ አይደለም፡፡
ኢማም አዝዘህብይ ይህን አስመልክቶ የሚከተለውን ተናግረዋል፤
((በነብዩ ዘመን - ወደ እርሳቸው እምነት የተጠጉና የእርሳቸው ባልደረባም ነን የሚሉ ጀማአዎች ነበሩ፡፡ ውስጣቸው ግን ንፍቅና ያለባቸው ናቸው፡፡ የአላህ ነብይ ﷺ አያውቋቸውም ነበር፡፡
አላህ ﷻ የሚከተለውን ተናግሯል ፡
وَمِمَّنْ حَوْلَكُم مِّنَ الْأَعْرَابِ مُنَافِقُونَ ۖ وَمِنْ أَهْلِ الْمَدِينَةِ ۖ مَرَدُوا عَلَى النِّفَاقِ لَا تَعْلَمُهُمْ ۖ نَحْنُ نَعْلَمُهُمْ ۚ سَنُعَذِّبُهُم مَّرَّتَيْنِ ثُمَّ يُرَدُّونَ إِلَىٰ عَذَابٍ عَظِيمٍ
"በዙሪያችሁም ካሉት ከዐረብ ዘላኖች መናፍቃን አልሉ፡፡ ከመዲና ሰዎችም በንፍቅና ላይ በማመጽ የዘወተሩ አልሉ፡፡ አታውቃቸውም፡፡ እኛ እናውቃቸዋለን፡፡ ሁለት ጊዜ እንቀጣቸዋለን፡፡ ከዚያም ወደታላቅ ቅጣት ይመለሳሉ፡፡"
(ተውባ ፡ 101)
በመዲና የሰው ልጆች አለቃ የሆኑት ነብዩ ለአመታት ሲኖሩ ከመካከላቸው የሚገኙትን ሙናፊቆች ካላወቁ ፣ ከኢስላም የተራቆቱ ሙናፊቆችን ከእርሳቸው በኋላ ያለው ኡመት አለማወቁ በጣም ተገቢ ነው፡፡))
(ሲየር አእላም አንኑበላእ ፡ 14/343)
ኡለሞችን ማማት ፣ ሌላውን አካል ከማማት ይከብዳል፡፡ ለሱና ኡለሞቻችን ትልቅ ክብር ልንሰጥ ይገባል፡፡
ጧውስ ብን ከይሳን - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል ፡
"من السنة أن يوقر أربعة : العالم ، وذو شيبة ، والسلطان ، والوالد" ذكره البغوي : (13\43)
“ለአራት (ሰዎች) ክብር መስጠት ከሱና ነው ፡ አሊም ፣ የሽበት ባለቤት ፣ ባለስልጣን ፣ ወላጅ”
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة