ዕውቀት እና የዕውቀት ባለቤቶች ደረጃ
ክፍል - 10
እውቀት የሱና መክፈቻ ነው ፤ ጅህልና ደግሞ የቢድዓ መክፈቻ ነው
እውቀትን በመፈለግ የዲን ጉዳዮች ይብራራሉ ፣ ብዠታዎች ይወገዳሉ ፤ ስውር ነገሮች ይገለጻሉ ፤ የራቁ ነገሮች ይቀርባሉ፡፡
የውዱዕን ስርዓት የማታውቅ ከሆነ ሌላ አማራጭ የለህም ኡለሞችን ጠይቀህ መገንዘብ እንጅ፡፡ የሶላትን ፣ የዘካን ዝርዝር ህግጋት ፣ እውቀቷንም እንዲሁ ካላወቅህ ኡለሞችን መጠየቅ እንጅ ሌላ አማራጭ የለህም፡፡
የቁርዓንና የሀዲስ ማስረጃዎቸን ተከታትለህና ከተገነዘብክ ፣ ባወቅኸው ከሰራህ ሱናውን በቀላሉ ትገነዘባለህ፡፡ በዚህም ታላቅና ሰፊ የሆነ ምንዳ ከአሏህ ዘንድ ታገኛለህ፡፡
ሙስሊም አቡሁረይራን ጠቅሰው በቁጥር (2699) ላይ የዘገቡት የረሱል ﷺ ሐዲስ የሚከተለው ነው፡-
"ومن سلك طريقا يلتمس فيه علما سهل الله له طريقا إلى الجنة"
“ዕውቀት ፍለጋ መንገድን የተጓዘ አላህ የጀነትን መንገድ ያመቻችለታል፡፡”
ሸሪዓዊ ዕውቀት ልብ ወለድን ከመከተልና የሸይጧንን መንገድ ከመከተል ይጠብቃል፡፡
ኢብኑል ቃሲም - ረሂመሁሏህ - ማሊክ የሚከተለውን ሲናገሩ ሰምተው አስተላልፈዋል፡-
"إن قوما ابتغوا العبادة ، وأضاعوا العلم ، فخرجوا على أمة محمد صلى الله عليه وسلم بأسيافهم ولو ابتغوا العلم لحجزهم عن ذلك"
“ህዝቦች ሸሪዓዊ ዕውቀትን ጥለው አምልኮትን ብቻ ፈለጉ፡፡ በዚህ ምክንያት በሕዝበ ሙስሊሙ ላይ ሰይፋቸውን መዘዙ፡፡ ዕውቀትን ቀድመው ቢፈልጉ ኖሮ ከዚህ ተግባራቸው ይቆጠቡ ነበር፡፡”
ወህብ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡- ኪታብ አስቀምጨ ሱና ሶላት ለመስገድ ቆምኩ፡፡ “የቆምክለት ጉዳይ ከተውኸው ጉዳይ በላጭ አይደለም፡፡” በማለት ኢማም ማሊክ ወቀሱኝ፡፡
(ሚፍታሁ ዳሩሰዓዳህ፡ 1/ 119-120)
“የተውኸው ጉዳይ” የተባለው ኢልም መሆኑን ልብ በል!
ሙዓዝ ብን ጀበል - ረዲዬሏሁ ዓንሁ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡- “ዒባዳ ነውና በዒልም ላይ አደራ! ለአላህ ብሎ ከተማረው ምንዳን ያገኛል፡፡ በርሱ ያስታወሰ ወደ አላህ ይቃረብበታል፡፡ ለማያውቀው ያሳወቀ ሶደቃ ይሆንለታል፡፡ በርሱ ዙሪያ ጥናት ያደረገ እንደ ጅሀድ ይቆጠርለታል፡፡ መተዋወሱ ደግሞ ተስቢህ ይሆንለታል፡፡”
(ፈታዋ ኢብን ተይምያህ ፡ 4/ 42) (አድ'ደይለምይ፡ 2\41)
ሸይኽ ሷሊህ ብን ዓብዲልዓዚዝ ዓሊ ሸይኽ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“ማንኛውም ሙስሊም ያለዕውቀትና ያለማስረጃ ከመናገር መቆጠብ አለበት፡፡ በተለይም በዓቂዳ፣ በኢማን፣ በተክፊር፣ በሀላልና በሀራም ጉዳይ፡፡ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ ከትክክለኛው ጎዳና ማፈንገጥ አንድ ብሎ የተጀመረው ሙስሊሞችን ያለምንም ማስረጃ በከሃዲነት በመፈረጅ ነው፡፡ ከኸዋሪጆች መካከል ከፊሎቹ ሀላፊነታቸውን አልተወጡም በሚል የሙዕሚኖች አሚር የሆኑትን ኡስማንን መገደል አለባቸው ሲሉ ከፊሎቹ ደግሞ አከፈሯቸው፡፡ ከመካከላቸው ዓልይንና ሌሎችን የሙስሊም መሪዎች ያከፈሩም አሉ፡፡
“ተክፊር” የሚለው ቃል ከእስልምና አፈንግጧል ብሎ በአንድ ሙስሊም ላይ ውሳኔ መስጠት ማለት ነው፡፡ እስልምናው የተረጋገጠለትን ሰው ያለአንዳች ሸሪዓዊ ማስረጃ ከኢስላም ወጧል ብሎ ውሳኔ መስጠት አይቻልም፡፡ አንድ ሙስሊም በርግጠኛነት ወደ ኢስላም እንደገባ ሁሉ ከኢስላም ሲወጣም በርግጠኛነት መሆን አለበት፡፡ ያለአንዳች ዕውቀትና ማስረጃ ታላላቅ ኡለሞችን ከመሬት ተነስቶ ከሃዲ ናቸው ብሎ መፈረጅ በጣም አደጋ ነው፡፡ አንድ ሰው ሐቅን የሚያብራሩ ታላላቅ ኡለሞችን በኩፍር ቢዘልፍ ወይም ቢሳደብ ተሳዳቢው ሐቅ ተናግሯል ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም በነፍሱ ላይ ወሰን በመተላለፉ ከሙስሊም መሪዎችና ከሸሪዓ ዳኞች በኩል እጁን ተይዞ ከፍተኛ ቅጣት ሊቀጣ ይገባዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ከዚህ በፊት በሸይኽ ዓብዱልዓዚዝ ብን ባዝና በሸይኽ ሙሐመድ ብን ሷሊህ አል'ኡሰይሚን በርካታ ጥናቶች ተካሂደዋል፡፡ አሁንም ቢሆን በኛ በኩል ከፍተኛ ጥንቃቄ ካላደረግን በኸዋሪጅ የጥመት አመለካከት መለከፋችን የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡
ለእውነታው እራሳችንን ማዘጋጀት ከመጥፎ ነገሮች መጠንቀቅ እርስ በርሳችን መመካከርና የነብያት ወራሽ ከሆኑት ኡለሞች ላይ ምላሳችንን መሰብሰብ አለብን፡፡”
ከዲንህ ጉዳዮች ከዘነጋህ ፣ ያለእውቀት ከሰራህ በዱንያም በአኼራም ግልጽ ኪሳራ እንጅ ሌላ አያጋጥምህም፡፡
ኸዋሪጆች የሙስሊሞችን ደም የተፈቀደ ያደረጉት በጅህልና እንደሆነ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ነግረውናል፡፡ ግልጽ የሆኑ አንቀጾችን በመተው አሻሚ የሆኑ አንቀጾችን በመከተላቸው ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀዋል፡፡
ረሱል ﷺ የእነርሱን ባህሪ ሲገልጹ ፡
"يقرؤون القرآن ، لا يجاوز حناجرهم ، يقتلون أهل الإسلام ، ويدعون أهل الاوثان ، يمرقون من الإسلام كما يمرق السهم من الرمية"
“ቁርኣን ይቀራሉ ፣ ከጉሮሯቸው አያልፍም ፣ የኢስላም ባለቤቶችን ይገድላሉ ፣ የጣኦት ባለቤቶችን ይተዋሉ ፣ ከኢስላም ይወጣሉ ቀስት ከተወረወረበት ቦታ (ቀዶት) እንደሚወጣ (ይወጣሉ)፡፡”
በዚህ ምክንያት ከመረጃዎች ያለእውቀት አሻሚ የሆኑ አንቀጾችን የሚከተሉ አካላትን ነብዩ አስጠንቅቀዋል፡፡
ረሱል ﷺ የሚከተለውን ቁርዓን ከቀሩ በኋላ ለአኢሻ የሚከተለውን ሐዲስ ነግረዋታል፡
هُوَ الَّذِي أَنزَلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ مِنْهُ آيَاتٌ مُّحْكَمَاتٌ هُنَّ أُمُّ الْكِتَابِ وَأُخَرُ مُتَشَابِهَاتٌ ۖ فَأَمَّا الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمْ زَيْغٌ فَيَتَّبِعُونَ مَا تَشَابَهَ مِنْهُ ابْتِغَاءَ الْفِتْنَةِ وَابْتِغَاءَ تَأْوِيلِهِ ۗ
"እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሐፉን ያወረደ ነው፡፡ ከእርሱ (ከመጽሐፉ) ግልጽ የኾኑ አንቀጾች አልሉ፡፡ እነሱ የመጽሐፉ መሠረቶች ናቸው፡፡ ሌሎችም ተመሳሳዮች አልሉ፡፡ እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን ለመፈለግና ትችቱን ለመፈለግ ከርሱ የተመሳሰለውን ይከታተላሉ፡፡"
(አል'ኢምራን ፡ 7)
"فإذا رأيت الذين يتبعون ما تشابه منه فأولئك الذين سمى الله فاحذرهم"
“ከእርሱ ተመሳሳይ የሆነውን የሚከተሉትን ከተመለከትህ እነዚያ እነርሱ አላህ የጠራቸው ናቸው ተጠንቀቋቸው፡፡”
ኡመር የሚከተለውን ተናግሯል ፡
"سيأتي ناس يجادلونكم بشبهات القرآن ، فخذوهم بالسنن ، فإن أصحاب السنن أعلم بكتاب الله عز وجل" أخرجه الآجري في "الشريعة" : ص : 52
“ለወደፊት በቁርዓን ሹቡሃ የሚከራከሯችሁ ሰዎች ይመጣሉ ፣ በሱና ያዟቸው ፣ የሱና ባለቤቶች በአላሀ ቁርዓን አዋቂዎች ናቸውና፡፡”
በማህይምነታቸው ምክንያት የቢድዓ ባለቤቶች የቁርዓንን ተመሳሳይ አንቀጾችን ይከተላሉ፡፡ የሀቅ ባለቤቶች ደግሞ ሱናን ለመከተላቸው በተመሳሳይ አንቀጾች ውስጥ ገብተው አይዘባርቁም፡፡ ይልቁንም ተመሳሳዩን ግልጽ ወደሆነው አንቀጽ ይመልሱታል፡፡
በርካታ ጠማማ የሆኑ ቡድኖች የጥመት መነሻቸው ከእወቀት መራቃቸው ነው፡፡ በአላህ ቁርዓን እና በነብዩ ﷺ ሱና የዲን ግንዛቤ ማግኘትን በመተዋቸው ነው፡፡