እውቀት እና የእውቀት ባለቤቶች ደረጃ
ክፍል - 21
የእውቀት መክፈቻ ፡ በጥሩ መልኩ ጥያቄን ማቅረብ ፤ በጥሩ ሁኔታ ማድመጥ
ኢብን አልቀይም - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል ፡
"مفتاح العلم : حسن السؤال وحسن الإصغاء"
شمس الدين محمد بن أبي بكر بن أيوب الزرعي الدمشقي المعروف بابن قيم الجوزية (691 - 751)، حادي الأرواح إلى بلاد الأفراح، تحقيق الدكتور السيد الجميلي، الطبعة الأولى 1405هـ، دار الكتاب العربي، 1985م، ص 100.
“የእውቀት መክፈቻው ፡ ጥሩ ጥየቃ ፤ ጥሩ ማድመጥ ነው”
ያላወቁትን መጠየቅ አላህ ﷻ እንዲሁም ረሱል ﷺ በቁርዓንም ይሁን በሐዲስ ያበረታቱት ጉዳይ ነው፡፡
አላህ ﷻ በተከበረው ቁርዓን ፡
فَاسْأَلُوا أَهْلَ الذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
"የማታውቁ ከሆናችሁ የዕውቀት ባለቤቶችን ጠይቁ፡፡"
(ነህል ፡ 43)
ሰዕድይ - ረሂመሁሏህ - ይህን ቁርኣን አስመልክቶ የሚከተለውን ትንታኔ ሰጠዋል ፡
“የዚህ አንቀጽ ጥቅል መልእክት : አሊሞች መወደሳቸው ፤ ከኢልም አይነቶች ትልቁ አላህ ያወረደው ኪታብ መሆኑ ፤ ያላወቀ ሰው በማንኛውም ክስተት ወደነርሱ (ወደ አሊሞች) እንዲመለስ አላህ ማዘዙ ፤ የእውቀት ባለቤቶች ፍትሃዊነት መገለጹ ፤ እነርሱንም ማወደሱ ፤ እነርሱንም እንድንጠይቅ ማዘዙ ፤ በዚህም ጃሂል (ይህ ጉዳይ የማይመለከተው መሆኑ) በውስጡ ያመላክታል፡፡ በወህይውና ባወረደው ህግ ላይ አላህ በእነርሱ ላይ አመኔታ እንደጣለ ፤ ነፍሳቸውን (ከተለያዩ መጥፎ ስነምግባራት) እንዲያጠሩ እና በተሟላ ስነምግባር መዋብ እንዳለባቸው መታዘዛቸውን ይገልጻል፡፡”
ዩሱፍ ከጥያቄ በመነሳት ነበር ለእስር ቤት ጓደኞቹ ዳዕዋ ያደረገላቸው ፤
يَا صَاحِبَيِ السِّجْنِ أَأَرْبَابٌ مُّتَفَرِّقُونَ خَيْرٌ أَمِ اللَّهُ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ
«የእስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! የተለያዩ አምላኮች ይሻላሉን ወይስ አሸናፊው አንዱ አላህ?"
“ዩሱፍ ፡ 39)
ሙሳ ከኸዲር እውቀትን ለማግኘት እና እርሱን ለመጎዳኘት በተለሳለሰ ጥያቄ ነበር የቀረበው :-
قَالَ لَهُ مُوسَىٰ هَلْ أَتَّبِعُكَ عَلَىٰ أَن تُعَلِّمَنِ مِمَّا عُلِّمْتَ رُشْدًا
"ሙሳ ለእርሱ «ከተማርከው ነገር ቀጥተኛን (ዕውቀት) ታስተምረኝ ዘንድ ልከተልህን?» አለው፡፡"
(ከህፍ ፡ 66)
ዲናቸውን ለማስተማር ጅብሪል ወደ ሶሃቦች የመጣው በጥያቄ መልክ ነበር
የአላህ ﷻ መልክተኛ ﷺ የሚከተለውን ተናግረዋል ፡
"إنه جبريل أتاكم يعلمكم دينكم"
“እንሆ እርሱ ጅብሪል ነው ፤ የመጣው ሀይማኖታችሁን ሊያስተምራችሁ ነው፡፡”
አቡ ሁረይራ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል :- አንድ የገጠር ሰው ወደ ረሱል ﷺ መጣ፡፡ “ሚስቴ ጥቁር ልጅ ወልዳለች ፤ ታዲያ ይህን ልቀበል አልቻልኩም?!” በማለት ጠየቃቸው። የአላህ መልክተኛ ﷺ “ለአንተ ግመል አለህን?” አሉት፡፡ “አዎ” አለ፡፡ “ምንድን ነው ከለሯ" አሉት። “ቀይ” አላቸው፡፡ “ቡናማ (ከለር ያለው) በመካከላቸው አለ?" በማለት ጠየቁት። “ቡናማ በመካከላቸው አለ” አለ። "ከየት ያመጣችው ይመስልሃል?” በማለት ጠየቁት። “ምናልባት የዘር ሐረግ ጎትቶት ሊሆን ይችላል” አላቸው። ረሱልም ﷺ "እርሱም (ልጅህ) የዘር ሐረግ ጎትቶት ሊሆን ይችላል” በማለት ምላሽ ሰጡት።
(አልቡኻሪ ፡ 7314)
ሰለፎች ለጥያቄ ትልቅ ቦታ ይሰጡ ነበር ፤ የእውቀት ማግኛ አንገብጋቢ መንገድ እንደሆነም ያረጋግጡ ነበር፡፡
አኢሻ የሚከተለውን ተናግራለች ፡
"نعم النساء نساء الأنصار ، لم يكن يمنعهن الحياء أن يسألن عن الدين ، وأن يتفقهن فيه"
“ከሴቶች መልካሞች የአንሷር ሴቶች ናቸው ፤ ስለዲን ከመጠየቅ ፣ ስለርሱ ከመማር አፍረት አይከለክላቸውም ”
(ሶሂህ ሙስሊም/ 332)
ሱፍያን ብን ኡየይና የሚከተለውን ተናግረዋል ፡
“እውቀት የሚጀምረው : በመልካም ሁኔታ በማዳመጥ ፤ ከዚያም በመገንዘብ ፤ ከዚያም በመሐፈዝ ፤ ከዚያም በመተግበር ፤ ከዚያም (የተማረውን) በማሰራጨት ነው …ባሪያው በእውነተኛ ኒያ አላህ በሚወደው ላይ ወደአላህ ኪታብ ፣ ወደነብዩ ሱና ካዳመጠ አላህ በሚገባ ሁኔታ ያስገነዝበዋል ፤ በልቡ ውስጥ ብርሃን ያደርግለታል፡፡”
(አልቁርጡብይ : አልጃሚኡ ሊአህካሚል ቁርዓን ፡ 14/26)
ሀሰን ብን አልይ ለልጁ የሚከተለውን ምክር መክሮታል
"يا بني ، إذا جالست العلماء فكن على أن تسمع أحرص منك على أن تقول ، وتعلم حسن استماع كما تتعلم حسن الصمت ، ولا تقطع على أحد حديثه وإن طال ، حتى يمسك"
“ልጀ ሆይ! ከኡለማ ጋር ከተቀመጥህ ከመናገርህ ይልቅ ለማዳመጥ በጣም ጉጉትና (ፍላጎት) ይኑርህ ፤ መልካም ዝምታን እንደተማርህ ሁሉ መልካም የሆነ ማድመጥንም ተማር ፤ የአሊሙ ንግግር የፈለገው ቢረዝም እርሱ እስከሚያቆም ድረስ አታቋርጠው።"
አጠያየቃችን ይመር! እውቀት ስንፈልግ ያማረ ዝምታ ይኑረን
ኢብን አልቀይም የሚከተለውን ተናግሯል ፡
((“ለእውቀት ስድስት ደረጃዎች አሉት፡፡
የመጀመሪያው : መልካም ጥያቄ ነው
ሁለተኛው : መልካም ማድመጥ
ሶስተኛው : መልካም ግንዛቤ
አራተኛው ፡ ሂፍዝ
አምስተኛው : (የተማረውን)ማስተማር ነው።
ስድስተኛው : ተግባር ነው ፤ እርሱም የእውቀት ፍሬው ነው፡፡
ከሰለፎች መካከል አንዱ የሚከተለውን ተናግሯል ፡
"إذا جالست العالم ، فكن على أن تسمع أحرص منك على أن تقول"
“ከአሊም ጋር ከተቀመጥህ ከመናገርህ ይልቅ ለማድመጥ ያለህ ፍላጎት ከፍተኛ ይሆን።”
አላህ ﷻ የሚከተለውን ተናግሯል ፡
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَذِكْرَىٰ لِمَن كَانَ لَهُ قَلْبٌ أَوْ أَلْقَى السَّمْعَ وَهُوَ شَهِيدٌ
"በዚህ ውሰጥ ለእርሱ ልብ ላለው ወይም እርሱ (በልቡ) የተጣደ ሆኖ (ወደሚነበብለት) ጆሮውን ለጣለ ሰው ግሳጼ አለበት፡፡"
(ቃፍ ፡ 37) ))
ابن قيم الجوزية، مفتاح دار السعادة ومنشور ولاية العلم والإرادة، مكتبة الرياض الحديثة، 1/ 169.
የሚከተለውን ቁርዓን አስመልክቶ ቁርጡብይ ማብራሪያ ሰጧል :-
۞ إِنَّمَا يَسْتَجِيبُ الَّذِينَ يَسْمَعُونَ ۘ
"ጥሪህን የሚቀበሉት እነዚያ የሚሰሙት ብቻ ናቸው፡፡ "
(አንአም ፡ 36)
"أي سماع إصغاء وتفهم ، وإرادة الحق ، وهم المؤمنون الذين يقبلون ما يسمعون ، فينتفعون به ويعملون" القرطبي الجامع أحكام القرآن 8\367)
“ጀሮ ሰጦ ማዳመጥና መገንዘብ ፤ ሀቅን መፈለግ ነው። ሀቅን የሚቀበሉ ፤ የሰሙትን የሚጠቀሙበትና የሚሰሩበት ሙእሚኖች ናቸው”
ቁርጡብይ አሁንም ወህብ ብን ሙነቢህ የተናገረውን እንደሚከተለው ዘግቧል ፡