Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚይ ረሒመሁላ፞ህ በስድብ፣ በማንቋሸሽ እና በመቅጠፍ ክብራቸውን ያጎደፈ ሰው ሲገጥማቸው እንዲህ ይሉ ነበር:–
"የላቀው አላህ በኔ ሰበብ አንድንም ሰው እሳት እንዳያስገባ እማፀነዋለሁ።"
ክብራቸውን ያጎደፈ ሰው ይቅርታቸውን ፈልጎ ወደሳቸው ሊመጣ እንደሆነ ሲነገራቸውም "ይቅርታ ለመጠየቅ መምጣት አያስፈልግም። እኔ ሁሉንም ሰው ይቅር ብያለሁ" ይሉ ነበር። አብረዋቸው ለሚሆኑ ሰዎችም ይህንን እንዲያደርሱ ይጠይቁ ነበር።
[ሸርሑል ኡሱሊ ሠላሣህ: 17–18]
~
እኛስ? ታሪኩን ያመጣሁት እንድንማርበት ነው። እስኪ እራሳችንን እንታዘብ። በደል የፈፀመብን፣ ክብራችንን ያጎደፈን ሰው ሳይጠይቀን ይቅር ማለቱ ቀርቶ ከልቡ እየለመነንስ ይቅር እንላለን ወይ? ለብዙዎቻችን ይሄ ከባድ ነው። የአፀፋ ዘመቻ ውስጥ የሚገባው ብዙ ነው። ጉዳዩ ከደዕዋ ወይም ከዱዓት ጋር ሲያያዝ ደግሞ ኸይሩም ሸሩም ለሌሎችም ይተርፋል።
(ٱلَّذِینَ یُنفِقُونَ فِی ٱلسَّرَّاۤءِ وَٱلضَّرَّاۤءِ وَٱلۡكَـٰظِمِینَ ٱلۡغَیۡظَ وَٱلۡعَافِینَ عَنِ ٱلنَّاسِۗ وَٱللَّهُ یُحِبُّ ٱلۡمُحۡسِنِینَ)
"ለእነዚያ በድሎትም ሆነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለሆኑት (ተደግሳለች)፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡"
[ኣሉ ዒምራን: 134]
(وَلَا یَأۡتَلِ أُو۟لُوا۟ ٱلۡفَضۡلِ مِنكُمۡ وَٱلسَّعَةِ أَن یُؤۡتُوۤا۟ أُو۟لِی ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡمَسَـٰكِینَ وَٱلۡمُهَـٰجِرِینَ فِی سَبِیلِ ٱللَّهِۖ وَلۡیَعۡفُوا۟ وَلۡیَصۡفَحُوۤا۟ۗ أَلَا تُحِبُّونَ أَن یَغۡفِرَ ٱللَّهُ لَكُمۡۚ وَٱللَّهُ غَفُورࣱ رَّحِیمٌ)
"ከእናንተም የችሮታና የክብረት ባለቤቶች የሆኑት ለቅርብ ዘመዶችና ለድሆች በአላህም መንገድ ለተሰደዱ ሰዎች ላይሰጡ አይማሉ፡፡ ይቅርታም ያድርጉ፡፡ (ጥፋተኞቹን) ይለፉም፡፡ አላህ ለእናንተ ሊምር አትወዱምን? አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡" [አነሕል: 22]
~~~
https://t.me/IbnuMunewor