ለማለት ብቻ ነው
በፎከረው አፌ በተነሳው ልቤ
ከግንባሬ ወለል በሚታየው ላቤ
በድፍረት ታጅቦ ተንቀልቃይ ሀሳቤ
ደግሜ ሰልሼ ማልኩኝ በማተቤ
ድጋሚ ላልደግመው ላልጠራው በስሙ
በእንቅልፍ በህልም አለም ህልምን ላያልሙ
የተቸሩኝ ጆሮች ስለሱ ላይሰሙ
ማልኩኝ በአምላክ ስም
ካጠገቡ ላልደርስ በከናፍሮቼ ዳግም ጉንጩን ላልስም
ዛትኩኝ በንግግር በልሳኔ አለም
ቃላትን ጨረስኩኝ እንዳልነበር ሁሉም
ከተቀመጥኩበት ይህንን በሙሉ ዝቼ ካለሁበት
ከዛ ሳልነሳ ቦታ ባለሁበት
ይናፍቀኝ ጀመር ስለሱ ማሰቤን አልኩኝ የሙጥኝት
የዛተው አንደበት ፉከራው በሞላ ተረሳ በድንገት
ልቤ ምትት አለች በናፍቆት አጀባ በመናፈቅ ጥማት
ዛቻው መች ወረደ ከጉሮሮ መሬት
መች ደረሰ ከዛ ልቤ ካለችበት
አጥራ በፍቅሩ የራሷኑ ድንበር
አልነካ ብላ ተከልላ ነበር
ምንም ላይበግራት ዛቻ ና ፉከራ
አሁን ግን እጅ ሰታለች መውጣት አቅቷት ይሄንን ተራራ
#ሼር
@amharic_quotes2
በፎከረው አፌ በተነሳው ልቤ
ከግንባሬ ወለል በሚታየው ላቤ
በድፍረት ታጅቦ ተንቀልቃይ ሀሳቤ
ደግሜ ሰልሼ ማልኩኝ በማተቤ
ድጋሚ ላልደግመው ላልጠራው በስሙ
በእንቅልፍ በህልም አለም ህልምን ላያልሙ
የተቸሩኝ ጆሮች ስለሱ ላይሰሙ
ማልኩኝ በአምላክ ስም
ካጠገቡ ላልደርስ በከናፍሮቼ ዳግም ጉንጩን ላልስም
ዛትኩኝ በንግግር በልሳኔ አለም
ቃላትን ጨረስኩኝ እንዳልነበር ሁሉም
ከተቀመጥኩበት ይህንን በሙሉ ዝቼ ካለሁበት
ከዛ ሳልነሳ ቦታ ባለሁበት
ይናፍቀኝ ጀመር ስለሱ ማሰቤን አልኩኝ የሙጥኝት
የዛተው አንደበት ፉከራው በሞላ ተረሳ በድንገት
ልቤ ምትት አለች በናፍቆት አጀባ በመናፈቅ ጥማት
ዛቻው መች ወረደ ከጉሮሮ መሬት
መች ደረሰ ከዛ ልቤ ካለችበት
አጥራ በፍቅሩ የራሷኑ ድንበር
አልነካ ብላ ተከልላ ነበር
ምንም ላይበግራት ዛቻ ና ፉከራ
አሁን ግን እጅ ሰታለች መውጣት አቅቷት ይሄንን ተራራ
#ሼር
@amharic_quotes2