እንኳን ደህና ቀሩ
[Red-8]
ዘጠና ዘጠኙን፡ አልጋዬ ስር ትቼ
አንዳንድ የምናፍቅ፡ ከጠፉት ሉኮቼ
ሥጭር ላቆሰሉኝ፡ ሙቼ ለፃፍኳቸው
አንድ ቀን አግኝቼ፡ ዳግም ላነባቸው፡
ወደ ወደቁበት ፡ ሀገርና ቅዬ
ያተጫነብኝን፡ ብዕሬን ፈንቅዬ፡
መጣለሁ ያልኩኝ፡ ከሞት ተነስቼ
እኔም ክርስቶስ ነኝ፡ ለጠፉት ግጥሞቼ።
ቢሆንም ቢሆንም፡
አዳማ ፍራንኮ፡ ከእርጎ ቤቱ በቀኝ
ይመጣል እያለች፡ የምትጠብቀኝ
ያቺ ወረቀት ግን ፡ ግጥም የፃፍኩባት
እንኳን ጠፍታኝ ቀረች፡ እንኳን ቀረሁባት።
ያቺ ኮብላይ ግጥሜ፡
መነሀሪያ አጠገብ፡ ቅጥቅጡ እስኪሞላ
ፍቅሩን በመጠበቅ፡ ለፈረሰ ገላ
ለማይረካ ናፍቆት፡ ለማይቆረጥ ጥም
ሻንጣዬን አዝዬ፡ በውሃ ጥም ዝዬ፡ የደረስኳት ግጥም
ሲበቃኝ ከኪሴ፡ አጥፌ ያኖርኳት
እንኳን የወደቀች፡ እንኳንም የጣልኳት።
አንዴ በፃፈው ልክ፡ እየተሰፈረ፡
ላንዴ ባፈለቀው፡ ጥቅስ እየታሰረ
ስንቱ ፈጣሪ ነው፡ ባለበት የቀረ?
ፍጡር ተነቦ ነው ፡ አምላኩ ሚከበር ፡
ፍጡር ተነቦ ነው፡ አምላኩ ሚቀበር
እንኳንም ወደቀች...
ብትኖር እሷን ብዬ፡ እዚያው እቀር ነበር።
አፈር ልሆን ሄድኩኝ፡ እሷን ከአፈር ጥዬ
በዝናብ ርሳ፡ በጣይ ተቃጥዬ
ያስተዋወቀንን፡ መልካችንን ትተን
ተላልፈን ይሆናል፡ ይሄኔ ተያይተን።
በተፃፃፍንበት፡ በነበር መች ቆየን?
በየደረስንበት፡ እንዳዲስ ተቃኘን
እሷ በሷ ሆዬ፡ እኔ በትዝታ
ከንግዲህ በኋላ፡ ባገኛትም እንኳ ፡ ከጣልኩበት ቦታ
አትሆነኝም ሎሌ ፡ አልሆናትም ጌታ።
እሷም ብቻ አይደለች፡ ያኮራችኝ ጠፍታ...
ከሶስት ቁጥር ቶታል ፡ በታቦት ማደሪያ
ለፀሀይ ዩኒፎርም ፡ ጋርደን ሰደርያ
ሲመሽ ከገብርኤል፡ እስከ አቦ ማዞሪያ
መንገዳችን እንጂ፡ ወሬያችን ሳይበቃን
መካኒሳን አልፈን ፡ ሳርቤት በቫቲካን
ለሚያረማምዱኝ፡ ለወክ አጣጮቼ
የታጠፈች ግጥሜን፡ ከኬሴ አውጥቼ
ቆም ሄድ እያልን፡ የመንገድ ባውዛው፡ በየደመቀበት
ያነበብኩላቸው ፡ የላመች ወረቀት...
ያቺ የዋህ ግጥም፡ «አንድም ሰው እንዳይሞት!» የሚል መዝጊያ ያላት
እንኳን የትም ጠፋች፡ እንኳን የትም ጣልኳት!
« አንድም ሰው እንዳይሞት? »
አረ ባክሽ?... እውነት?
የልጅነት ግጥሜ፡ ስሚኝ ተረት ተረት...
ዮኒፎርም አውልቀው፡ ከአብሮ አደግ ርቀው
በዓለም ስቃይ ልክ፡ ልብን አተልቀው
ከምኞት ደመና፡ በግፍ ወንጭፍ ወርደው
በወክ ካካለሉት ፡ካደጉበት ሰፈር፡ ተነቅለው ተሰደው
ተቃጥለው ከፃፉት ፡ በሀቅ በፍትሕ ጥም
«አንድም ሰው እንዳይተርፍ!» ይማፀናል ግጥም።
እንኳን ጠፋታ ቀረች፡ ግጥሜ እንደልጅነት
ዓለሙን ሳታውቀው ፡ የተፃፈች ጀነት
በምኞት ቡርሿ፡ ሲዖል ለማቆንጀት
ስትጣጣር ያኔ፡ እንኳን ነቃሁባት፡
እንኳን የትም ጣልኳት፡ ይቺ ተረት ተረት...
የወተት ግጥሞቼ፡ እየተነቀሉ፡ ሲበቅል የስጋው
ለነከሰኝ ሁሉ፡ ሰው ብዬ ስጠጋው
እንኳንስ ልታገል፡ ስለት እንዳይወጋው...
ሞት አንሷል ብዬ ነው፡ አሁን የምሰጋው።
ምን ያቺ ብቻ...?
እየደረሳቸው፡ የመሰወር እጣ
ከሀይስኩል መድረክ፡ ፑሽኪን እስክመጣ
ከአዳማ ክበብ፡ ከግቢ እስክወጣ
ከጦቢያ በጃዝ ፡ከፒክኒክ በረንዳ
ጆሮ እየጠመድኩኝ፡ በስንኝ ልነዳ
ከኪሴ እየሳብኩኝ፡ መመለስ ዘንግቼ
የትም የጣልኳቸው ፡ ባይተዋር ግጥሞቼ
ያጡትን ለማግኘት፡ ጠፍቶ ከመመኘት
ተነፋፍቆ ኖሮ፡ ተጣባብቆ መቅረት
ከሚባል መንትያ ፡ቀንበር ነፃ ይውጡ
ከእንግዲህ ግጥሞቼ ፡ ወደኔ እንዳይመጡ...
'ጠፍተን ያልተገኘን፡ ልጆችም ነን' ቢሉ
እንድውጣጣባቸው፡ ለተደለደሉ
ሆኜ ለተውኳቸው፡ ሆኜ ላለፍኳቸው፡ አልቀው ለተጣሉ
ላለፉት እኔዎች፡ መቃብሮች ናቸው፡ የፃፍኳቸው ሁሉ።
[Red-8]
ዘጠና ዘጠኙን፡ አልጋዬ ስር ትቼ
አንዳንድ የምናፍቅ፡ ከጠፉት ሉኮቼ
ሥጭር ላቆሰሉኝ፡ ሙቼ ለፃፍኳቸው
አንድ ቀን አግኝቼ፡ ዳግም ላነባቸው፡
ወደ ወደቁበት ፡ ሀገርና ቅዬ
ያተጫነብኝን፡ ብዕሬን ፈንቅዬ፡
መጣለሁ ያልኩኝ፡ ከሞት ተነስቼ
እኔም ክርስቶስ ነኝ፡ ለጠፉት ግጥሞቼ።
ቢሆንም ቢሆንም፡
አዳማ ፍራንኮ፡ ከእርጎ ቤቱ በቀኝ
ይመጣል እያለች፡ የምትጠብቀኝ
ያቺ ወረቀት ግን ፡ ግጥም የፃፍኩባት
እንኳን ጠፍታኝ ቀረች፡ እንኳን ቀረሁባት።
ያቺ ኮብላይ ግጥሜ፡
መነሀሪያ አጠገብ፡ ቅጥቅጡ እስኪሞላ
ፍቅሩን በመጠበቅ፡ ለፈረሰ ገላ
ለማይረካ ናፍቆት፡ ለማይቆረጥ ጥም
ሻንጣዬን አዝዬ፡ በውሃ ጥም ዝዬ፡ የደረስኳት ግጥም
ሲበቃኝ ከኪሴ፡ አጥፌ ያኖርኳት
እንኳን የወደቀች፡ እንኳንም የጣልኳት።
አንዴ በፃፈው ልክ፡ እየተሰፈረ፡
ላንዴ ባፈለቀው፡ ጥቅስ እየታሰረ
ስንቱ ፈጣሪ ነው፡ ባለበት የቀረ?
ፍጡር ተነቦ ነው ፡ አምላኩ ሚከበር ፡
ፍጡር ተነቦ ነው፡ አምላኩ ሚቀበር
እንኳንም ወደቀች...
ብትኖር እሷን ብዬ፡ እዚያው እቀር ነበር።
አፈር ልሆን ሄድኩኝ፡ እሷን ከአፈር ጥዬ
በዝናብ ርሳ፡ በጣይ ተቃጥዬ
ያስተዋወቀንን፡ መልካችንን ትተን
ተላልፈን ይሆናል፡ ይሄኔ ተያይተን።
በተፃፃፍንበት፡ በነበር መች ቆየን?
በየደረስንበት፡ እንዳዲስ ተቃኘን
እሷ በሷ ሆዬ፡ እኔ በትዝታ
ከንግዲህ በኋላ፡ ባገኛትም እንኳ ፡ ከጣልኩበት ቦታ
አትሆነኝም ሎሌ ፡ አልሆናትም ጌታ።
እሷም ብቻ አይደለች፡ ያኮራችኝ ጠፍታ...
ከሶስት ቁጥር ቶታል ፡ በታቦት ማደሪያ
ለፀሀይ ዩኒፎርም ፡ ጋርደን ሰደርያ
ሲመሽ ከገብርኤል፡ እስከ አቦ ማዞሪያ
መንገዳችን እንጂ፡ ወሬያችን ሳይበቃን
መካኒሳን አልፈን ፡ ሳርቤት በቫቲካን
ለሚያረማምዱኝ፡ ለወክ አጣጮቼ
የታጠፈች ግጥሜን፡ ከኬሴ አውጥቼ
ቆም ሄድ እያልን፡ የመንገድ ባውዛው፡ በየደመቀበት
ያነበብኩላቸው ፡ የላመች ወረቀት...
ያቺ የዋህ ግጥም፡ «አንድም ሰው እንዳይሞት!» የሚል መዝጊያ ያላት
እንኳን የትም ጠፋች፡ እንኳን የትም ጣልኳት!
« አንድም ሰው እንዳይሞት? »
አረ ባክሽ?... እውነት?
የልጅነት ግጥሜ፡ ስሚኝ ተረት ተረት...
ዮኒፎርም አውልቀው፡ ከአብሮ አደግ ርቀው
በዓለም ስቃይ ልክ፡ ልብን አተልቀው
ከምኞት ደመና፡ በግፍ ወንጭፍ ወርደው
በወክ ካካለሉት ፡ካደጉበት ሰፈር፡ ተነቅለው ተሰደው
ተቃጥለው ከፃፉት ፡ በሀቅ በፍትሕ ጥም
«አንድም ሰው እንዳይተርፍ!» ይማፀናል ግጥም።
እንኳን ጠፋታ ቀረች፡ ግጥሜ እንደልጅነት
ዓለሙን ሳታውቀው ፡ የተፃፈች ጀነት
በምኞት ቡርሿ፡ ሲዖል ለማቆንጀት
ስትጣጣር ያኔ፡ እንኳን ነቃሁባት፡
እንኳን የትም ጣልኳት፡ ይቺ ተረት ተረት...
የወተት ግጥሞቼ፡ እየተነቀሉ፡ ሲበቅል የስጋው
ለነከሰኝ ሁሉ፡ ሰው ብዬ ስጠጋው
እንኳንስ ልታገል፡ ስለት እንዳይወጋው...
ሞት አንሷል ብዬ ነው፡ አሁን የምሰጋው።
ምን ያቺ ብቻ...?
እየደረሳቸው፡ የመሰወር እጣ
ከሀይስኩል መድረክ፡ ፑሽኪን እስክመጣ
ከአዳማ ክበብ፡ ከግቢ እስክወጣ
ከጦቢያ በጃዝ ፡ከፒክኒክ በረንዳ
ጆሮ እየጠመድኩኝ፡ በስንኝ ልነዳ
ከኪሴ እየሳብኩኝ፡ መመለስ ዘንግቼ
የትም የጣልኳቸው ፡ ባይተዋር ግጥሞቼ
ያጡትን ለማግኘት፡ ጠፍቶ ከመመኘት
ተነፋፍቆ ኖሮ፡ ተጣባብቆ መቅረት
ከሚባል መንትያ ፡ቀንበር ነፃ ይውጡ
ከእንግዲህ ግጥሞቼ ፡ ወደኔ እንዳይመጡ...
'ጠፍተን ያልተገኘን፡ ልጆችም ነን' ቢሉ
እንድውጣጣባቸው፡ ለተደለደሉ
ሆኜ ለተውኳቸው፡ ሆኜ ላለፍኳቸው፡ አልቀው ለተጣሉ
ላለፉት እኔዎች፡ መቃብሮች ናቸው፡ የፃፍኳቸው ሁሉ።