✅ባሻዬ! የትንሽነትና የዘረኝነት መንፈስ ውሻ ነው። ከሮጥክለት ይከተልሃል። በተለይ የበታችነት መንፈስ (Inferiority complex) አደገኛ ነው። ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ ባልችልም አልበርት አንስታይን "የበታችነት መንፈስ ከተሰማህ ዛፍ ላይ ውጣ" ይላል። እኔ ግን እልሃለሁ እንኳን ዛፍ ላይ ይቅርና የንግድ ባንክ አዲሱ ፎቅ ላይ ብትወጣ የበታችነት ስሜትን ማጥፋት አትችልም።
ባሻዬ! ስለ ትንሽነት ስነ ልቦና በዚች ጨዋታ ላዋዛልህ፣
አህያና ፈረስ ተገናኙና ማውራት ጀመሩ። አህያው ፈረሱን ጠየቀው
"ሥራህ ምንድነው?"
"ስፖርተኛ ነኝ። በፈረስ ግልቢያ፣ በፈረስ ጉግስና የመሰናክል ዝላይ ብዙ ዋንጫዎችና ሜዳሊያዎችን ተሸልሜያለሁ"
አህያው ይሄንን ሲሰማ ከፍተኛ የመንፈስ ቅናት ተሰማው። የተሰማውን የበታችነት ስሜት ለመደበቅ ሲል በቀጣዩ ሣምንት ፈረሱን በቤቱ ምሳ ሊጋብዘው ቀጠረው።
የቀጠሮው ቀን ሲደርስ አህያው ፈረሱን ሊያስደምመው ፈለገና ሁለት የሜዳ አህያ (ዜብራ) ፎቶ ገዛና ቤቱ ግድግዳ ላይ ሰቀለ።
ፈረሱ አህያው ቤት ገባና ዙሪያውን ተመልክቶ ጠየቀው፣
"ቤትህ ያምራል። እነዚያ ሁለት ፎቶዎች ላይ የሚታዩት ዜብራዎች እነማን ናቸው?"
✅"አልነገርኩህም ለካ! እኔም እኮ እንዳንተ ስፖርተኛ ነኝ። ፎቶዎቹ የኔ ናቸው። አንደኛው ባለፈው ሲዝን ለጁቬንቱስ ስጫወት የተነሳሁት ነው። ሁለተኛው አሁን ለኒው ካስትል ስጫወት የተነሳሁት ነው። እንዲያውም ነገ ከሊቨርፑል ጋር የካራባእ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ እሰለፋለሁ
"Tesfaye H/Mariam