የዕጩ ዶ/ር ፈለቅ ሳቢር የ3ኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፍ ተገመገመ
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሂሳብ ት/ክፍል በ ‹‹Numerical Analysis›› ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ፈለቅ ሳቢር የመመረቂያ ጽሑፍ ታኅሣሥ 22/2017 ዓ.ም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል፡፡
ዕጩ ዶ/ር ፈለቅ ሳቢር የመጀመሪያ ዲግሪውን ከኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የ2ኛ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሂሳብ ትምህርት ያገኘ ሲሆን 3ኛ ዲግሪውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲከታተል ቆይቶ የመመረቂያ ጽሑፉን ‹‹Graded Mesh Methods for Two Parameters Singularly Perturbed Second Order Boundary Value Problems›› በሚል ርዕስ አከናውኗል፡፡
የዕጩ ዶ/ር ፈለቅ ሳቢር ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ የሚመረቅ ይሆናል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት