ዩኒቨርሲቲው የሴኔት መተዳደሪያ ደንብ ክለሳ ወርክሾፕ አካሄደ
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን በአስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ እየሠራ ሲሆን ከሥራዎቹ አንዱ የሆነውን የሴኔት መተዳደሪያ ደንብ (Senate Legislation) ክለሳ አከናውኖ ዛሬ ታኅሣሥ 22/2017 ዓ/ም በተከለሰው ረቂቅ ደንብ ላይ የውስጥ ግምገማ አካሂዷል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ተ/ፕሬዝደንት ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማል እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው የሴኔት መተዳደሪያ ደንብ እና ስትራጂክ ዕቅዱን ለመከለስ ያቋቋመው ኮሚቴ የተለያዩ ሰነዶችን በማመሳከርና የሌሎች የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ተቋማትን ተሞክሮ በማጥናት ክለሳውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቋል፡፡ የተከለሰው ደንብና ስትራቴጂክ ዕቅድ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለሚመለከተው አካል ከመላኩ በፊት ማስተካከያዎችን ለማድረግና የጠራ ሥራ ለማቅረብ የሚረዳ ግብአት ለማግኘት ውይይቱ መዘጋጀቱን ተ/ፕሬዝደንቱ ገልጸዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝ አስተዳደር ፕሮጀክት ማኔጀር ዶ/ር ቤታ ፀማቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ መረጃ መሰብሰብ፣ ማጠናቀርና ሌሎችም ሒደቶችን አልፎ ክለሳው በከፍተኛ ትኩረትና ትጋት መሠራቱን ገልጸው ዶክመንቱ ተጠናቆ ለሚመለከተው አካል ከመላኩ በፊት ከመድረኩ የተገኙ ጠቃሚ ግብአቶች የሚካተቱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሴኔት መተዳደሪያ ደንብ ክለሳ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ተስፋዬ ሀብተማርያም የክለሳ ሒደቱን አስመልክቶ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን በክለሳ ሒደቱ የተለያዩ ሰነዶች ቅኝትና የተቋማት ተሞክሮ ዳሰሳ መደረጉን እንዲሁም በኮሚቴ አባላት በክፍፍል የተሠራውን እያንዳንዱን ሥራ በጋራ በማየት የማደራጀትና የአርትኦት ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
የራስ-ገዝ አስተዳደር ስታንዳርድና ፖሊሲ አስተባባሪ አቶ አስጨናቂ ዳዊት የደንቡን ይዘት አስመልክቶ ባቀረቡት ገለጻ የተከለሰው መተዳደሪያ ደንብ በስምንት የተለያዩ ክፍሎች የተከፋፈለ ሲሆን የተቋሙን አወቃቀር፣ የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች አካዳሚክ መመሪያና ደንቦች፣ ምርምር፣ የማኅበረሰብ ጉድኝት፣ ዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር እና የማማከር አገልግሎት የመሳሰሉ ክፍሎችን የያዘ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች ክለሳውን ላከናወነው ኮሚቴ ምስጋና በማቅረብ የዩኒቨርሲቲውን አስተዳደር ቦርድ እና የፕሬዝደንቱ ሥልጣንና ኃላፊነት፣ የትምህርት ፕሮግራሞች፣ የማስመረቂያ ጊዜ፣ የተማሪዎች ቅበላ፣ የመምህራንና ተመራማሪዎች አካዳሚክ ደረጃ እድገት እና የመሳሰሉት ላይ በተለይም ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ጉልህ ለውጥ የተደረገባቸው ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው በረቂቅ ሕገ ደንቡ መሠረት የማስተካከያ ሃሳቦችን ሰጥተዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት