የዩኒቨርሲቲው የታዳሽ ኃይል ምርምር ማእከል አድቫንስድ ሶላር ሥልጠና ሰጠ
የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የታዳሽ ኃይል ምርምር ማእከል ከሳይ ሶላር ማኅበርና ስዊዘርላንድ ከሚገኘው ‹‹University Of Applied Sciences & Arts (SUPSI)›› ጋር በመተባባር ከጥር 26-የካቲት 6/2017 ዓ.ም አድቫንስድ ሶላር ሥልጠና ሰጥቷል ፡፡
የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ የዩኒቨርሲቲው የታዳሽ ኃይል ምርምር ማእከል የመንግሥት ትኩረት የሆነውን ታዳሽ ኃይል ላይ ያሉ አቅሞችን በመጠቀም እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ማእከሉ ከተለያዩ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር በአርባ ምንጭ ዙሪያ፣ ምዕራብ አባያ፣ ቁጫ፣ ጨንቻና ገረሴ ወረዳዎች 250 አባወራዎችን የባዮጋዝ ተጠቃሚ ማድረጉን የተናገሩት ዶ/ር ተክሉ የፀሐይ ታዳሽ ኃይልን ለመጠቀም የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን በጋሞና ጎፋ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች ላሉ 15 ት/ቤቶች እና 23 ጤና ጣቢያዎች መትከል ተችሏል ብለዋል፡፡
የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉነህ ለማ ማእከሉ ገጠራማ በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ጤና ጣቢያዎች የታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከመሥራቱ በተጨማሪ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎችን እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ታዳሽ ኃይል ምርምር ማእከል ዳይሬክተር ዶ/ር ያሊሾ ግርማ እንደገለጹት በሥልጠናው የዩኒቨርሲቲውና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መምህራን፣ የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎችና የሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ሠራተኞችን ጨምሮ 55 ሠልጣኞች ተሳትፈዋል፡፡ ሠልጣኞች ከሥልጠናው በኋላ በወረዳዎች የሚገኙ የሶላር ፕሮጀክቶችን የሚያስተባብሩ ሲሆን ሥልጠናው መምህራን በሶላር ምርምር ዘርፍ ያላቸውን አቅም እንዲያሳድጉ የሚረዳ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
ከአሠልጣኞች መካከል የዩኒቨርሲቲው ኤሌክትሪካልና ኮምፕዩተር ምኅንድስና ፋከልቲ መምህርና ተመራማሪ ሳሙኤል ከፍአለ ‹‹Additional Components›› እና ‹‹Rules & Regulation›› በሚሉ ይዘቶች ላይ ሥልጠና መስጠታቸውን ገልጸው ይህም ባለሙያዎች የተቀመጡ ደረጃዎችን (Standards) ጠብቀው እንዲሠሩ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡ አንድ ባለሙያ በሶላር ቁሶች መረጣና የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ገመድ መረጣ ዙሪያ የወጡ ሀገር አቀፍ ሕጎችን ዐውቆ መሥራት እንዳለበት መ/ር ሳሙኤል ጠቁመዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የፓወር ኢንጂነሪንግ የ2ኛ ዲግሪ ተማሪ ደሳለኝ ቆለጭ በራሳችን አቅም ፕሮጀክቶችን ቀርጸን የምንሠራበትን ዕውቀት ከሥልጠናው አግኝተናል ብሏል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት