ሰበር ዜና!
የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በምዕራብ በለሳ ወራህላ ከተማ ዙሪያ ልዩ ቦታው ፈንጣ ሀዋሪያት ከሚባል ዛሬ መጋቢት 1/2017 ዓ/ም ከጥዋቱ አራት ስዓት ጀምሮ የብልፀግናን ጥምር ወንበር አስጠባቂ ሀይል ማለትም መከላከያ፣ አድማ በታኝ እና ሚኒሻን በተለመደው የውጊያ ምት ቁም ስቅሉን አያበሉት ለእነሱ ቀኑ ወር ያህል እረዝሞባቸው መውጫ ቀዳዳ አሳጥቷቸው ውሏል።
ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በለሳን ሙሉ ለሙሉ ከአገዛዙ ለማፅዳት ዘመቻ ከጀመረበት የካቲት 20 ጀምሮ ገጠሮችን ሙሉ ለሙሉ አስለቅቀን አርባያ ከተማ እና ከመኪና መንገድ ብቻ ተወስኖ እንዲቀመጥ አድርገናል ሲል የክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ፋኖ ታድሎ ደሴ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ተናግሯል።
የአገዛዙ ሀይል በማንኛውም ስአትና ሁኔታ ፣ ቀንም ሆነ ለሊት ከጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የሚገጥመነን እርምጃ አናውቅም በማለት እንቅስቃሴአቸውን ሁሉ በዙ 23 የታጀበ ቢያደርጉም ከጀግኖች ምት እና ሞት መዳን አልቻሉም ማንም እንደ ማያድናቸውም እያሳየናቸው እንገኛለን፣ በዛሬው ውጊያ ጠላት ዳግመኛ ከፍተኛ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት በሽንፈትና በውርደት ተመልሷል ብሏል።
ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ሰሞኑን በበለሳ ከመከላከያ፣ከአድማ ብተና፣ እንዲሁም የተለያየ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ከአገዛዙ በግፍ የተባረሩ በርካታ አዲስ ሀይሎች ወደ ክፍለ ጦራችን እየተቀላቀሉ ጉልበት እየሆኑን እንዲሁም ለአማራ ህዝብ ተጨማሪ ጥንካሬ በመሆን ከነባሩ ሀይል ጋር በቅንጅት እየተዋጉ ይገኛሉ።
የበለሳ ህዝብ ከጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ጎን በመሆን የብልፅግናን ስርዓት ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ቆርጦ ተነስቶ አብሮ ተሰልፎ የህይወት ዋጋ እየከፈለ ይገኛል። መንግስትን ጎትተን ቤተ መንግስት አስገብተነው ዋጋችን እረስቶ አመድ አፋሽ አድርጎን በለሳን በማንኛውም ልማት ወደ ኋላ አስቀርቶን የሚኖረውን ስርዓት ከዚህ በላይ እንዲቀጥል አንፈቅድለትም በማለት ከፋኖ ጋር እየታገሉ ያሉ አርሶ አደሮች እና ልጆቻቸው ቁጥር እጅግ ብዙ ናቸው። የደጃች ዳኛው ተሰማ ልጆች እንደ አያቶቻቸው የህልውና ፣ የነፃነት እና የፍትህ ተጋድሎ እያደረጉ ዳግመኛ ታሪክ እየሰሩ ይገኛሉ።
ጠላት በአሁኑ ስአት ሀይሉን ተራራ ላይ እንደ ዝንጀሮ መንጋ ሰብስቦ በሞርተር እና ዲሽቃ ነብሱን ለማትረፍ እየጣረ በከፍተኛ የድረሱልን ጥሪ እየጮኸ ይገኛል።
ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ጥቁር አስፓልትና ከተማ ዙሪያ የማይለቀውን የአንባገነኑን ስርዓት እግር በእግር እየተከታተለ እግሩን እያሳጠረለት፣ ቁጥሩን እየቀነሰለት፣ ሞራሉን እየሰበረው እንደሚገኝ ፋኖ ታድሎ ደሴ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።
ከጎንደር ሰማይ ሰር ውጊያ እና ግዳጅ ላይ የሚገኘው ክፍለ ጦራችን በቅርቡ የጥይት ድምፃችን አባይ ማዶ አራት ኪሎ ጥግ ለማድረግ ድርሻችን እና ግዴታችን እየተወጣን እንገኛለን ሲል የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግ/ሀላፊ አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።
© ኢትዮ 251 ሚዲያ