በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘውና በአጭር ጊዜ 53 ቀናት ውስጥ የተገነባው ቅሊንጦ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው ዕለት የመማር ማስተማር ስራ ጀምሯል፡፡
ትምህርት ቤቱ በአዲስ መልክ ከመገንባቱ በፊት 1555 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች በቅሊንጦ ቁጥር 2 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በፈረቃ ሲማሩ የቆዩ ሲሆን የዚህ G+4 የመማሪያ ክፍል ግንባታ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ከፈረቃ ትምህርት እንዲወጡና ለብቻው በተከለለው ቅሊንጦ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርታቸዉን እንዲከታተሉ ያስቻለ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በቅሊንጦ ቁጥር 2 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው G+4 የመማሪያ ክፍል ማስፋፊያ ግንባታም የተጠናቀቀ ሲሆን በዛሬው ዕለት ለመማር ማስተማር ስራዉ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news