የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዲግሪ መርሀ- ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ጀመረ
የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዲግሪ መርሀ- ግብር ጅማሮ ማብሰሪያ እና ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምስጋና መርሀ-ግብር በዛሬው እለት ማለትም የካቲት 29/2017ዓ.ም በኦሎምፒክ ሆቴል ተካሂዷል።
ኮሌጁ በአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሥር ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት አርባ ስድስት ዓመታት መካከለኛ የጤና ባለሙያዎችን ሲያፈራ የቆየ አንጋፋ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሲሆን ፣የጤና ትምህርት መስኮች በማስተማር በርካታ ባለሙያዎችን አፍርቷል።
በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዲግሪ መርሀ-ግብር ለማስተማር እውቅና አግኝቶ ተማሪዎችን ማስተማር ጀምሯል።
በዛሬው እለት በተደረገውም የዲግሪ መርሀ-ግብር ማብሰሪያ እና የምስጋና ፕሮግራም ኮሌጁ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ላደረገው አስተዋጽኦ እውቅና ሰጥቶታል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ተልዕኮውን እንዲወጣ በሰው ኋይል ስልጠናና በተለያዩ ድጋፎች በአጋርነት ሲሰራ ቆይቷል።
ኮሌጁ በዲግሪ መርሀ- ግብር ማስተማር በመጀመሩ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ደስታቸውን ገልፀዋል። በቀጣይም ኮሌጁ በጤናው ዘርፍ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት በሚያደርገው ጥረት ዩኒቨርሲቲው በትብብር የሚሰራ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news