📌 የዱዓችን ተቀባይነት ማጣት ምክንያቱ ምን ይሆን?
ﻣﺮ ﺇﺑﺮﺍﻫﻴﻢ ﺑﻦ ﺃﺩﻫﻢ ﺭﺣﻤﻪ ﺍللّٰه تعالى ﺑﺴﻮﻕ ﺍﻟﺒﺼﺮﺓ ؛ ﻓﺎﺟﺘﻤﻊ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺇﻟﻴﻪ، ﻭﻗﺎﻟﻮﺍ: ﻳﺎ ﺃﺑﺎ ﺇﺳﺤﺎﻕ: ﻣﺎ ﻟﻨﺎ ﻧﺪﻋﻮﺍ ﻓﻼ ﻳُﺴﺘﺠﺎﺏ ﻟﻨﺎ؟
ኢብራሒም ኢብኑ አድሀም (رحمه الله) በበስራ ገበያ ሲያልፉ ሰዎች ተሰብስበው ወደሳቸው ከበቧቸውና እንዲህ አሏቸው፦ ያ አባ ኢስሃቅ ዱዓእ አድርገን ዱዓችን ለምን ምላሽ አጣ?
ﻗﺎﻝ: لإﻥ ﻗﻠﻮﺑﻜﻢ ﻣﺎﺗﺖ ﺑﻌﺸﺮﺓ ﺃﺷﻴﺎﺀ!.
እሳቸውም፦ ቀልባችሁ (ልባችሁ) በአስር ነገሮች ሞታለች አሏቸው።
ﻗﺎﻟﻮﺍ: ﻭﻣﺎ ﻫﻲ؟ ﻗﺎﻝ:
እነሱም፦ ምን ምንድ ናቸው? ብለው ጠየቋቸው።
እሳቸውም፦
✅ﺃﻧﻜﻢ ﻋﺮﻓﺘﻢ ﺍللّٰه؛ ﻓﻠﻢ ﺗﺆﺩّﻭﺍ ﺣﻘّﻪ.
አንደኛ፡ አላህን አውቃቹት።ሐቁን አልተወጣችሁም።
✅ﺯﻋﻤﺘﻢ ﺃﻧﻜﻢ ﺗﺤﺒّﻮﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠّٰﻪ (ﷺ) ﺛﻢ ﺗﺮﻛﺘﻢ ﺳﻨّﺘﻪ.
ሁለተኛ፡ ነቢዩን (ﷺ) እንወዳለን ብላችሁ ሞገታችሁ፤ ከዚያም ሱናውን ተዋችሁ።
✅ﻗﺮﺃﺗﻢ ﺍﻟﻘﺮﺁﻥ، ﻭﻟﻢ ﺗﻌﻤﻠﻮﺍ ﺑﻪ.
ሶስተኛ፡ ቁርኣንን አነበባችሁት አልሰራችበትም።
✅ﺃﻛﻠﺘﻢ ﻧﻌﻤﺔ الله، ﻭﻟﻢ ﺗﺆﺩّﻭﺍ ﺷﻜﺮﻫﺎ.
አራተኛ፡ የአላህን ፀጋ በልታችሁ ምስጋናውን አልተወጣችሁም።
✅ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥّ ﺍﻟﺸﻴﻄﺎﻥ ﻋﺪﻭّﻛﻢ، ﻭﻭﺍﻓﻘﺘﻤﻮﻩ.
አምስተኛ፡ ሸይጣን ጠላታችነው ብላችሁ ከሱ ጋር ገጠማቹ።
✅ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﺠﻨّﺔ ﺣﻖ، ﻓﻠﻢ ﺗﻌﻤﻠﻮﺍ ﻟﻬﺎ.
ስድስተኛ፡ ጀነት ሐቅ ናት ብላችሁ ለርሷ የሚሆን ስራ አልሰራችሁም።
✅ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﻨّﺎﺭ ﺣﻖ، ﻭﻟﻢ ﺗﻬﺮﺑﻮﺍ ﻣﻨﻬﺎ.
ሰባተኛ፡ የጀሀነም እሳት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሷ የሚዳርጋችሁት ስራ አልተዋቹም።
✅ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﻤﻮﺕ ﺣﻖ، ﻓﻠﻢ ﺗﺴﺘﻌﺪّﻭﺍ ﻟﻪ.
ስምንተኛ፡ ሞት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሱ አልተሰናዳችሁም።
✅ﺍﻧﺘﺒﻬﺘﻢ ﻣﻦ ﺍﻟﻨﻮﻡ، ﻭﺍﺷﺘﻐﻠﺘﻢ ﺑﻌﻴﻮﺏ ﺍﻟﻨﺎﺱ، ﻭﺗﺮﻛﺘﻢ ﻋﻴﻮﺑﻜﻢ.
ዘጠነኛ፡ ከእንቅልፋቹ ነቅታቹ፤ የራሳችሁን ነውር ትታችሁ በሰዎች ነውር ተጠመዳችሁ።
✅ﺩﻓﻨﺘﻢ ﻣﻮﺗﺎﻛﻢ، ﻭﻟﻢ ﺗﻌﺘﺒﺮﻭﺍ ﺑﻬﻢ
አስር፡ ሙታናችሁን ቀብራችሁ በነሱ አልተገሰፃችሁም።
📙 ጃሚዑል በያን ዓልዒልም ወፈድሊህ፡ 2/12
ጆይን፦
https://t.me/ATWHIDCOM