✍በኢብራሂም አ.ሰ ጊዜ አለምን ያስተዳድር የነበረው አመፀኛ ንጉስ ማን ይባላል??
@aymi22
መልስ👍መ// ነምሩድ✅
ታሪኩ በጣም ረጅም ቢሆንም ቀንጨብ አድርገን👇
ከሀድዎች የሚያመልኩትን ጣኦት ኢብራሁም ዐ.ሰ በሰባበሩት ጊዜ...
ጣዖት ተገዢዎች #ለነምሩድ ሁኔታውን ተረኩለት። ነምሩድ #ኢብራሒምን አስጠራቸው። በደንባቸው መሠረት ማንኛውም ሰው ወደ #ነምሩድ ሲገባ ሱጁድ ይወርዳል። #ኢብራሒም (ዐ ሰ) ሲገቡ ሱጁድ አልወረዱም ነበር።
#ነምሩድ_ኢብራሒምን ለምን እንዳልሰገዱ ሲጠይቃቸው #ኢብራሒም እንዲህ በማለት መለሱለት፦
#ኢብራሒም፦ አንተንም እኔንም ለፈጠረ አምላክ እንጅ አልሰግድም…!"
#ነምሩድ፦ ጌታህ ማነው?_
#ኢብራሒም፦ የእኔ ጌታ ያ ሕይወት ሰጪ እና ሐይወት ነሺ የሆነው (አምላክ) ነው። "
#ነምሩድ፦ እኔም ህያው አደርጋለሁ፣ እገድላለሁም!"_
ሁለት ሰዎችን ከእስር ቤት አስመጣ እና አንዱን ገድሎ አንዱን በነፃ አሰናበተው። ቀጥሎ እንዲህ አለ፦
"አየህ! እኔም ይህንን ማድረግ እችላለሁ" አለ።
#ነምሩድ ያልገባው ነገር ቢኖር ሕይወት የአምላክ እስትንፋስ፣ ሞት ደግሞ የሩህ ከአካል መለየት መሆኑን ነው። እዚህ ላይ ኢብራሒም እንዲህ አሉ፦
"የእኔ ጌታ ፀሐይን በምስራቅ በኩል ያወጣታል፣ አንተ አቅሙ ካለህ በምዕራብ እንድትወጣ አድርጋት!" አሉት።
ቁርአን ይህንን ክስተት በሚከተለው መልኩ ይገልፀዋል፦
أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِي حَاجَّ إِبْرَاهِيمَ فِي رَبِّهِ أَنْ آتَاهُ اللَّهُ الْمُلْكَ إِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّيَ الَّذِي يُحْيِي وَيُمِيتُ قَالَ أَنَا أُحْيِي وَأُمِيتُ ۖ قَالَ إِبْرَاهِيمُ فَإِنَّ اللَّهَ يَأْتِي بِالشَّمْسِ مِنَ الْمَشْرِقِ فَأْتِ بِهَا مِنَ الْمَغْرِبِ فَبُهِتَ الَّذِي كَفَرَ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ
ወደዚያ አላህ ንግሥናን ስለሰጠው ኢብራሂምን በጌታው ነገር ወደ ተከራከረው ሰው አላየህምን ኢብራሂም «ጌታዬ ያ ሕያው የሚያደርግና የሚገድል ነው» ባለ ጊዜ «እኔ ሕያው አደርጋለሁ እገድላለሁም» አለ፡፡ ኢብራሂም፡- «አላህ ፀሐይን ከምሥራቅ በኩል ያመጣል (አንተ) ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው፡፡ ያም የካደው ሰው ዋለለ፤ (መልስ አጣ) አላህም በዳዮች ሕዝቦችን አይመራም፡፡
📚አል-በቀራህ - 258📚
የቁርአን ሙፈሲሩ አል በይዷዊ ስለ ነምሩድ ሲናገሩ፦
ቂልነቱ የጀመረው መለኮታዊነትን ለራሱ ለማድረግ ሲሞክር ነው» ይላሉ። አላህ (ሱ ወ) አብዝቶ በሰጠው የገንዘብ እና የሹምነት ፀጋ በማመስገን ፋንታ ተቃራኒውን አደረገ። አስተባበለ። የአላህን ህልውና ካደ።~~~~~~~
~~~~~
~~~~ኢብራሒም አ.ሰ ስደት ከወጡ በኋላ በግብዝነታቸው እና በትዕቢተኛነታቸው እምነትን ባልተቀበሉ ሰዎች ላይ የትንኙ መንጋ እንደ አቧራ ነበር የወረደባቸው። ትንኞቹ የጣዖታውያኑን ደም መምጠጥ ጀመሩ። ሰዎቹም በያሉበት ደርቀው ቀሩ። አንዷ ትንኝ #በነምሩድ_አፍንጫ ውስጥ ገብታ ጭንቅላቱ ውስጥ ድረስ ዘለቀች። #ነምሩድ የሚሰማውን ህመም ለማስታገስ ያለማቋረጥ ጭንቅላቱን ይደበድብ ነበር። በመጨረሻም ጭንቅላቱ ተሰንጥቆ ለህልፈት በቃ።
ቁርአን ክስተቱን በዚህ መልኩ ይገልፅልናል፦
وَأَرَادُوا بِهِ كَيْدًا فَجَعَلْنَاهُمُ الْأَخْسَرِينَ
በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ በጣም ከሳሪዎችም አደረግናቸው፡፡
📚ሱረቱ አል-አንቢያ 70📚