የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ህግ እንዲወጣ ጠየቀ‼️
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍን አጠቃቀም የሚገራ ህግ መውጣት አለበት ሲሉ ጠየቁ ።
አባላቱ " ማህበራዊ ሚዲያው የአገርን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳረፈ በመሆኑ ዘርፉን መቆጣጠር የሚያስችል ህግ ማውጣት ያስፈልጋል " ብለዋል።
የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ይህን ያሉት ተሻሽሎ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበው የመገናኛ ብዙኃን ረቂቅ አዋጅ ላይ በተደረገ የውይይት መድረክ ነው ።
የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የህግ ክፍል ሀላፊ ወ/ሪት ቆንጂት ታምራት በበኩላቸው " ማህበራዊ ሚዲያን የሚገዛ ህግን በመገናኛ ብዙኃን ረቂቅ አዋጅ ላይ ማካተት የሚዲያውን የገዘፈ ጉዳይ ማሳነስ ስለሚሆን በቀጣይ ራሱን የቻለ ህግ መውጣት ይኖርበታል " ብለዋል ።
የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስም " ቀጣዩ ማህበራዊ ሚዲያን የተመለከተ ህግ ማውጣት ነው " ሲሉ ተናግረዋል ።
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇⬇️⬇️
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s