Alibaba‼️
አሊባባ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር ክፍያ መቀበል እንደሚጀምር አስታወቀ‼️
አንጋፋው አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ተቋም የሆነው አሊ ባባ እንደገለፀው ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በአሊ ኤክስፕረስ የበርካታ አገራትን ገንዘብ ጥቅም ላይ ያውላል፡፡
ከእነዚህ አገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ኬንያና ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል፡፡ የክፍያ መፈፀሚያ ገንዘቦችን ማስፋፋት ያስፈለገው ለአፍሪካ ተጠቃሚዎች በስፋት ተደራሽ ለመሆን በማሰብ እንደሆነ የጠቀሰው አሊ ባባ በተጨማሪም በአለም አቀፍ የክሬዲት ካርዶችና የውጭ ምንዛሬ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለማስቀረት እንደሆነ አስረድቷል፡፡
የአፍሪካ አገራትን ገንዘብ በግብይቱ ውስጥ ጥቅም ላይ ማዋሉ በአለም አቀፍ የክፍያ ስርአት የተነሳ ለአፍሪካዊያን ትልቅ ማነቆ የሆነውን ችግር ለመቅረፍ ማቀዱንም አስታውቋል፡፡ በዚህም አዳዲስ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎችን እንደሚያገኝ ተስፋ ሰንቋል፡፡
ለዚህ እንዲረዳው በተጠቀሱት አገራት ከሚገኙ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ጥምረት መፍጠሩን የገለፀው አሊ ባባ ከሚቀጥለው ሳምንት ማለትም የካቲት 17 ጀምሮ ብርን ጨምሮ የተለያዩ ገንዘቦችን በግብይት ስርአቱ ውስጥ እንደሚያካትት አስታውቋል፡፡
====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s