ለይለቱል ቀድር‼️
==========
ክፍል:-①
#ሼር_አድርጉት
ለይለቱ-ልቀድር ማለት ምን ማለት ነው?
«ለይለተል ቀድር ማለት በአጭሩ የመወሰኛይቱ ሌሊት ማለት ነው፣ ይች ለሊት ትልቅ ቀድር ወይም ደረጃ ያላት ለሊት ናት በተጨማሪም ፍጡራንን የሚመለከቱ የአመቱ ውሳኔዎች የሚተላለፍባት ለሊት ናት።||
የለይለቱል-ቀድር ደረጃዎች:-
①) ቁርኣን የወረደባት ለሊት ነች፡፡
አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፡-
إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرٌِ
እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡
📚ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (1)
②) በርሷ ላይ የተፈፀመ ዒባዳ ከሌሎች ለሊቶች በተለየና ምንዳው የበለጠ ነው።
አምላካችን አላህ እንዲህ ይላል፡-
لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٌٍ
መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡
📚ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (3)
③) በርሷ ውስጥ መላእክት ኸይርን ይዘው ወደ ምድር ይወርዳሉ፡፡
አምላካችን አላህ እንዲህ ይላል፡-
تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٌٍ
በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡
📚ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (4)
④) ለሊቷ ዒባዳህ የሚበዛባት፣ ሰላም የሚሰፍንባት ለሊት ናት፡፡
አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፡-
سَلَامٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرٌِ
እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡
📚ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (5)
⑤) የተባረከች ለሊት ናት።
አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፡-
إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَةٍ ۚ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينٌَ
እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡
📚ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አድዱኻን (3)
⑥) በዚች ለሊት አላህ በአመቱ ውስጥ ያሉ የፍጡራኑን የእድሜ እና የሲሳይ ልኬታዎችን ይፅፋል፡፡
አላህም እንዲህ ብሏል፡-
فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٌٍ
በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡
📚ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አድዱኻን (4)
⑦) በዚያች ለሊት ምድር ላይ የሚኖሩት የመላእክት ብዛት ከጠጠሮች ብዛት የበዛ ነው፡፡
⑨) ለተጠቀመባትና አጅሩን ከአላህ ላሰበ ሰው ከወንጀል መማርያ ለሊት
ነች፡፡
ነብዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
«ለይለተልቀድር አምኖ እና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል»፡፡
📚ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
✔️ስለዚህ ይህቺን ወሳኝና እጅግ የላቀ ዋጋ ያላት ለሊት ለማገኘት የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ሌሎችንም ልናበረታታ ይገባል፡፡
ኢብኑልቀይም (ረሒመሁላህ) ይችን ንግግር ተናገሩ:-
«ለይለተልቀድር በአመት ውስጥ የምትገኝ አንዲት ቀን ብትሆን እርሷን
ለማገኘት ስል አመቱን ሁሉ እቆም ነበር፡፡ #በረመዳን አስር ለሊቶች ውስጥ ከሆነችማ ምን ነካህ? እንዴት እዘናጋለሁ?!» አሉ።
✔️ለይለቱልቀድር የምትገኘው በየትኛው ጊዜ ነው?
ለይለተልቀድር የምትገኘው በረመዳን ብቻ ነው፣ ከረመዳንም ደግሞ በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ነው፡፡ ይህንንም የሚያስረዳን ነብዩ (ሰለላሁ
ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸው ነው፡-
«ይቺን ለሊት እየፈለግኩ የመጀመሪያውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ፣ ከዚያም መካከለኛውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ፣ ከዚያም (የሆነ አካል) መጥቶኝ "እሷ በርግጥም
የመጨረሻው አስር ላይ ናት" ተባለኝ» ማለታቸው ነው፡፡
*
ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፡-
«በሱ (በረመዳን) ውስጥ ከአንድ ሺ ወር የምትበልጥ ለሊት አለች፣ የርሷን ኸይር
የተነፈገ በእርግጥም "ትልቅ ነገር" ተነፍጓል»፡፡
📚አስ-ሶሒሕ
♣️
✔️ ስለዚህ ወንድሞችና እህቶች ይቺ ታላቅ ለሊት እንዳታልፈን የምንችለውን ሁሉ ልንጥር ይገባል፡፡
ፁሁፍ ሲንዛዛ አልወድም እንዳላበዛባችሁ
ክፍል:-② ይቀጥላል
④) ለይለቱል ቀድርና ምልክቶቹ?
⑤) ለይለተልቀድር በአይን ትታያለች?
⑥) የዚያች ምሽት ተወዳጅ ዱዓእ ምንድነው?
ሌላም ሰው እንዲቀላቀለን ሊንኩን ሳታጠፉ ሼር አድርጉት‼️
#join.
@back_to_alllah