የሰማዩን ምስክር
ጨለማን ሰባሪ_ብርሃን ወጥቶብሻል
ሞትን የሚገድል_ትንሳኤን ወልደሻል
ንጽሕ መሶበ ወርቅ_ ድንግል ተብለሻል
ለከበረው ክብርሽ_ስግደት ይገባሻል።
የሰማዩ ምስክር_ የታየው በራማ
በምድራዊው ገነት_ እነሆ ተሰማ
የመልአኩን በስራት_ኤልሳቤጥ ስትደግመው
በሆዷ ያለው ጽንስ_ ደስታ አዘለለው
መጥምቀ መለኮት_ክብሩ ከፍ ያለ ነው።
ለኛ ስለሰጠች _ የሕይወት እንጀራን
ሁሌም ለዘለአለም_ እንወዳታለን
የምስራቋ ደጃፍ_የወለደች ፀሐይ
የኤልሳዕ ማሰሮ_ የበረከት ሲሳይ።
የፍቅር የሰላም _ የምሕረት መገኛ
የምንመካብሽ _ ነይ ነይ ወደ እኛ
ኖርዶስ ቀሲመታት_ በጎ መዓዛ ነሽ
የአማኑኤል ማደሪያ_ የለም የሚመስልሽ።
ጌታዬ ከሰጠኝ_ እናቴ እልሻለው
የመንገድ ስንቄ ነሽ_ እመካብሻለው
ለጠየኩሽ ሁሉ _ መልስ የምትሰጪኝ
እንዳልነዋወጥ_ በዐለቱ ትከይኝ።
በመከራ ጊዜ _ መሸሸጊያ ሆኖን
የመከራን ባሕር_ በፍቅሩ አሻግሮን
እንደበደላችን_ ሳያጠፋን ጌታ
አቆመን በደጁ_ ሞልቶን በእልልታ።
ከኛ የበረታችሁ _ አስቡን በጸሎት
በስጋ ፈተና _ እንዳይገለን ምቾች
በሄድንበት ሁሉ_ እንዲገጥመን ሰላም
ፍፃሜአችን እንዲያምር_አማልጅን ማርያም።
የተሰቀለውን _በገና አውርዱ
መሰንቆ ክራሩን_ ከበሮ አሰናዱ
መቆሚያ ጽናጽል_ ይታደል ለሁሉም
በያሬድ ውብ ዜማ_በሚያስረሳ ዓለም
ተነሱ እንዘምር_ ለመድኃኒዓለም።
እንዲህ እናምናለን_ እንታመናለን
በተበተንበት በባዕዱ ምድር_ እንመሰክራለን
የሥላሴን ጥበብ_ ትውልድ እንዲረዳ
ይምጣና ይመገብ_ ከእናቱ ጓዳ
ኋላ ለጥያቄ _እነዳይሆን እንግዳ ትጉኃን
በዝማሬው ጣዕም_ተሞልተን ደስታ
በተዋሕዶነቷም _ ነፍሳችን ተጽናንታ
በቃሉ ምስክር _ ቀርቦልን ማዕድ
በወልድ እናት ምልጃ _በሕይወት መንገድ
ከቅድስት ምድራችን _በመጡት
በደጀ ሰላሙ አለን_ ተሰብስበን።
በመረዋ ድምጹ_ በሚስረቀረቀው
ሲሰማ አርነት_ተሰፋን በሚሰብከው
የአባቶችን ምክር_ትዕዛዝ በሚያከብረው
በረጋው አንደበት_ ከቴድሮስ ሰማነው
ኪዳነምሕረት_ በእቅፏ ታኑረው።
ከዕርስታችን ወተን_ ብንኖርም በእሩቅ
መተላለፋችን_ በስሙ እንዲፋቅ
ክብር ሞገስ ሆነን_ ስራው የሚያስደንቅ።
ሀይማኖት ከምግባር_የነፃነት በፍታ
የሚያስተምር ፍቅር_ ጠዋትና ማታ
የወንጌል አርበኛ_ የሚያስር የሚፈታ
ደጀንን ሸለመን_ የሰራዊት ጌታ።
ለዘመኑ ሕመም_ መድኃኒት ያመርታል
የነፍስ ዶክተር ነው _ትውልድ ይፈውሳል
ብሉይን ከሐዲስ _ እያመሳጠረ
ስንቱን ሐሰተኛ_ ከቤት አባረረ።
በጠላት ተከቦ_ ሲደፈር ተራራው
እንደ ተመረጡት_ በእውነት አብበው
ወንጌልን ተጫምቶ_ በብዕር ይሻገራል
በለበሰው ሞገስ_ ሁሉን ያስደምማል
___
h>ttps://t.me/behle_abew
ጨለማን ሰባሪ_ብርሃን ወጥቶብሻል
ሞትን የሚገድል_ትንሳኤን ወልደሻል
ንጽሕ መሶበ ወርቅ_ ድንግል ተብለሻል
ለከበረው ክብርሽ_ስግደት ይገባሻል።
የሰማዩ ምስክር_ የታየው በራማ
በምድራዊው ገነት_ እነሆ ተሰማ
የመልአኩን በስራት_ኤልሳቤጥ ስትደግመው
በሆዷ ያለው ጽንስ_ ደስታ አዘለለው
መጥምቀ መለኮት_ክብሩ ከፍ ያለ ነው።
ለኛ ስለሰጠች _ የሕይወት እንጀራን
ሁሌም ለዘለአለም_ እንወዳታለን
የምስራቋ ደጃፍ_የወለደች ፀሐይ
የኤልሳዕ ማሰሮ_ የበረከት ሲሳይ።
የፍቅር የሰላም _ የምሕረት መገኛ
የምንመካብሽ _ ነይ ነይ ወደ እኛ
ኖርዶስ ቀሲመታት_ በጎ መዓዛ ነሽ
የአማኑኤል ማደሪያ_ የለም የሚመስልሽ።
ጌታዬ ከሰጠኝ_ እናቴ እልሻለው
የመንገድ ስንቄ ነሽ_ እመካብሻለው
ለጠየኩሽ ሁሉ _ መልስ የምትሰጪኝ
እንዳልነዋወጥ_ በዐለቱ ትከይኝ።
በመከራ ጊዜ _ መሸሸጊያ ሆኖን
የመከራን ባሕር_ በፍቅሩ አሻግሮን
እንደበደላችን_ ሳያጠፋን ጌታ
አቆመን በደጁ_ ሞልቶን በእልልታ።
ከኛ የበረታችሁ _ አስቡን በጸሎት
በስጋ ፈተና _ እንዳይገለን ምቾች
በሄድንበት ሁሉ_ እንዲገጥመን ሰላም
ፍፃሜአችን እንዲያምር_አማልጅን ማርያም።
የተሰቀለውን _በገና አውርዱ
መሰንቆ ክራሩን_ ከበሮ አሰናዱ
መቆሚያ ጽናጽል_ ይታደል ለሁሉም
በያሬድ ውብ ዜማ_በሚያስረሳ ዓለም
ተነሱ እንዘምር_ ለመድኃኒዓለም።
እንዲህ እናምናለን_ እንታመናለን
በተበተንበት በባዕዱ ምድር_ እንመሰክራለን
የሥላሴን ጥበብ_ ትውልድ እንዲረዳ
ይምጣና ይመገብ_ ከእናቱ ጓዳ
ኋላ ለጥያቄ _እነዳይሆን እንግዳ ትጉኃን
በዝማሬው ጣዕም_ተሞልተን ደስታ
በተዋሕዶነቷም _ ነፍሳችን ተጽናንታ
በቃሉ ምስክር _ ቀርቦልን ማዕድ
በወልድ እናት ምልጃ _በሕይወት መንገድ
ከቅድስት ምድራችን _በመጡት
በደጀ ሰላሙ አለን_ ተሰብስበን።
በመረዋ ድምጹ_ በሚስረቀረቀው
ሲሰማ አርነት_ተሰፋን በሚሰብከው
የአባቶችን ምክር_ትዕዛዝ በሚያከብረው
በረጋው አንደበት_ ከቴድሮስ ሰማነው
ኪዳነምሕረት_ በእቅፏ ታኑረው።
ከዕርስታችን ወተን_ ብንኖርም በእሩቅ
መተላለፋችን_ በስሙ እንዲፋቅ
ክብር ሞገስ ሆነን_ ስራው የሚያስደንቅ።
ሀይማኖት ከምግባር_የነፃነት በፍታ
የሚያስተምር ፍቅር_ ጠዋትና ማታ
የወንጌል አርበኛ_ የሚያስር የሚፈታ
ደጀንን ሸለመን_ የሰራዊት ጌታ።
ለዘመኑ ሕመም_ መድኃኒት ያመርታል
የነፍስ ዶክተር ነው _ትውልድ ይፈውሳል
ብሉይን ከሐዲስ _ እያመሳጠረ
ስንቱን ሐሰተኛ_ ከቤት አባረረ።
በጠላት ተከቦ_ ሲደፈር ተራራው
እንደ ተመረጡት_ በእውነት አብበው
ወንጌልን ተጫምቶ_ በብዕር ይሻገራል
በለበሰው ሞገስ_ ሁሉን ያስደምማል
___
h>ttps://t.me/behle_abew