፪
የቅዱስ ኤፍሬም ድርሳን ስለ ጾም ስለ ጸሎትና ንስሓ
ወዳጆቼ ሆይ ወደ ሲኦል የሚያወርድ ወደ ሰማይም የሚያሳርግ ጾም እንዳለ ዕወቁ፡፡ የኤልዛቤል ጾም የከፋ ነው፡፡ በጾም ናቡቴን ትገድለው ዘንድ አዘዘች፡፡ አክዓብም በላ ጠጣ፡፡ ሰውነቱም ተደሰች፡፡ የድኃውን ርስት በነጠቀ ጊዜም ከክብሩና ከንግሥናው ወደቀ፡፡
ዳግመኛም ጳውሎስን በቤተ መቅደስ ሊገድሉት የፈለጉ የዓርባ ሰዎች ጾም የከፋ ነው፡፡ የእስራኤል ልጆች ጾም የከፋ ነው፡፡ በአፋቸው ጾምን ብለው በምግባራቸው እግዚአብሔርን አስቈጥተውታልና፡፡ ባዕለ ጸጋም እንዲሁ ይጾማል፤ የሚጾመው ግን ስለ እግዚአብሔር ብሎ አይደለም፡፡ ሀብቱ ንብረቱ እንዲበዛለት ነው እንጂ፡፡
የጦብያ ጾምም የተወደደ ሆነ፡፡ በሀገሩ ውስጥ የወደቀውን የችግረኛውን አስከሬን እስኪቀብር ድረስ ማዕድን አልሠራም ነበርና፡፡ የአይሁድ ጾም ግን ክፉ ጥፉ ነው፡፡ በአፋቸው እየጾሙ በልባቸው ክፋትን ያስባሉና፡፡ ልቡናውን ከክፉ ነገር ሁሉ ለሚያነጻ ሰው ግን ጾም ያማረ የተወደደ ነው፡፡
እግዚአብሔር መብልን አይጠላም እያልህ ጾምን የምትጠላ ባዕለ ጸጋ ሆይ እንዳትስት አስቀድሞ የሆነውን በጀሮህ ስማ፤ በልብህም አስተውል፤ የጾምን መንገድ የመብልንም ሥራ መርምር፡፡ አዳም ትዕዛዙን በተላለፈ ጊዜና ከዕፀ በለስ በበላ ጊዜ ምን ያህል ኀዘን እንደ መጣበት፣ ከክብሩም እንደ ተዋረደ፣ በሁሉም ዘንድ የተጠላ እንደሆነ፣ ወደ ተፈጠረባት መሬትም እንደ ተመለሰ፣ ከሕይወት ዛፍም እንደ ራቀ፣ ዕራቊትነቱንም ባየ ጊዜ መራራ ልቅሶን እንዳለቀሰ፣ ስለ ተሰጠው የብርሃን ልብስ ፈንታም የበለስ ቅጠልን እንደ ለበሰ ዕወቅ፡፡
በጾመ ጊዜ ግን ባዕለ ጸጋ ሆነ፡፡ በበላ ጊዜ ደግሞ ችግረኛ ሆነ፡፡ ለራሱም ጥልንና ቂምን አመጣ፡፡ ከዚህም የተነሣ ቃኤል ወንድሙን ገደለ፡፡ በአፉ ከዕፀ በለስ በላ፡፡ ሥጋውም በችግርና በድካም ጠፋ፡፡ በሰው መካከልም ጥልና አመፃ በዛ፡፡ የአዳም መብሉ የሰውን መንገድ የባሕር ውስጥ ጉዞ አስመሰለው፡፡ ጥጋብ ግን ብዙ ክፉ ሥራ አለባትና፡፡ በጾም ግን ኃጢአት ይሠረያል፡፡ ሰው በአንዱ አፉ ክፉና በጎ ይናገራል፡፡ መራራና ጣፋጭ ውኃ የሚፈስበት ምንጭ ምንኛ የከፋ ነው!
መራራና ጣፋጭ ውኃ የሚመነጭበትን ምንጭ ለሚመስለው ለቃየል ወዮለት፡፡ ወንድሙን ና! ወደ ምድረ በዳ እንውጣ ብሎታልና፡፡ አቤልም በየዋህነት ተከተለው፡፡ ከዚህም በኋላ ቃኤል አቤልን ገደለው፡፡ ቃኤል ሆይወንድምህን ስለምን ገደልኽው? አንተስ ይሁዳ ጌታህን ስለምን ሸጥኸው? ልብህ በአመፃ ተሞልቶ ሳለ በአፍህ ‹‹መምህር ሆይ ቸር ዋልህን?›› ብለኸዋልና፡፡
ይቀጥላል
(ቅዱስ ኤፍሬም ድርሳን በእንተ ጾም ወጸሎት ወንስሓ ➛ በድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት መጽሐፍ ገጽ 189-199 በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ)