💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 120 💙💙
▶️፩. "ወደ አራስና ሳትነጻ በደሟ ወዳለች ሴት መሄድ" እንደ ኀጢአት በብሉይ ኪዳን ተቆጥሯል (2ኛ መቃ.9፥21)። አንዲት ሴት ስትወለድ ማን ያርሳታል ወይስ ራሷ እንድትሠራው ነው? በሐዲስ ኪዳንስ ያለው እንዴት ነው?
✔️መልስ፦ ወደ አራስና ሳትነጻ በደሟ ወዳለች ሴት መሔድ አይገባም ብሎ የገለጸው ከዚህ በአራስነቷ ወይም በወር አበባዋ ጊዜ ከሴት ጋር ግንኙነት አይገባም ማለት ነው እንጂ እንኳን ማርያም ማረችሽ ለማለት አራስን ለመጠየቅ መሔድ አይገባም ማለት አይደለም። በእርግጥ በብሉይ ኪዳን አራስ ቤተ መቅደስ እስከምትገባና ሌላም ሴት በወር አበባዋ ወቅት ሳለች እንደ ርኵስት ትታይ ነበር። እና እርሷን ሰላም ማለትና መንካትም ያረክስ ነበር። በሐዲስ ኪዳን ግን ሰላምታም አይከለከልም። መስቀል መሳለምም ትችላለች። ቤተክርስቲያን ውስጥ መግባትና መቁረብ ብቻ አይፈቀድላትም።
▶️፪. እግዚአብሔር እስራኤላውያን ሲበድሉ የአሕዛብን ነገሥታት አስነሥቶ ያስማርካቸዋል። መልሶ ደግሞ የአሕዛብን ነገሥታት በዚያ ድርጊታቸው ይኮንናቸዋል ይሄ ነገር እንዴት ይታያል?
✔️መልስ፦ ማንኛውም ሰው በደለኛ ከሆነ በበደሉ ይቀጣል። አንድ ጻድቅ ሲያጠፋ እግዚአብሔር በኃጥእ እጅ ሊጥለው ይችላል። ይህም ተጸጽቶ ንስሓ እንዲገባ ነው። ኃጥእ ራሱ ግን ባደረገው በደል ይቀጣል። ለምሳሌ ይሁዳ ጌታን በሠላሳ ብር የሸጠው ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ነው። ንጹሕ ሰውን አሳልፎ መሸጥ ኃጢአት መሆኑን ይሁዳም ያውቅ ነበር። ብሩ በልጦበት እስከ መካድ ደረሰ። አሁን በዚህ ጊዜ ተሰቅሎ ዓለምን ማዳን የጌታም ፈቃዱ ስለሆነ የይሁዳን ክፋት እርሱ ለሌሎች መዳኛ አድርጎ ለውጦታል። ይሁዳ ግን ክፋትን ስለሠራ ተጠያቂ ሆኖ በበደሉ ተቀጥቶበታል። የአሕዛብ ነገሥታት እስራኤላውያንን እየማረኩ ሲበድሏቸው ኖረዋል። አሕዛብ ክፋትን ስላደረጉ በክፋታቸው ይቀጣሉ። እስራኤላውያንም በክፋታቸው ይቀጣሉ። ክፋት ሆኖ የማያስቀጣ ነገር እንደሌለ ሁሉ መልካም ሥራ ሆኖ የሚያስጎዳም የለምና።
▶️፫. አንደኛ መቃብያን ላይ ያለው መቃቢስ ታሪኩ አልተገለጸም ነበር። ሁለተኛ መቃብያን ላይ ነው የተገለጸው። እንደዚህ ከሆነ ለምን ከሁለተኛ መቃብያን አልጀመረም? አንደኛና ሁለተኛ መቃብያንስ ልዩነቱ ምንድን ነው? ታሪኩ ስለተመሳሰለብኝ ነው ።
✔️መልስ፦ ምንም እንኳ ታሪካቸው ተቀራራቢ ቢሆንም ሁለቱም መጻሕፍት የተጻፉት ስለተለያዩ ሰዎች ነው። አንደኛ መቃብያን የተጻፈው ስለመቃቢስ ዘብንያምና ስለ ልጆቹ ሲሆን ሁለተኛ መቃብያን የተጻፈው ደግሞ ስለ መቃቢስ ዘሞዓብ ነውና።
▶️፬. "ክሣደ ልቡናውን በማጽናትና ራሱን በማኩራት ፈጣሪው ለፈጠረው ለአዳም መስገድን እምቢ እንዳለ" ይላል (2ኛ መቃ.9፥3)። ይሄ ንባብ ምን ለማለት ነው?
✔️መልስ፦ ቅዱሳን መላእክት አዳም በእግዚአብሔር አርዓያና መልክ የተፈጠረ መሆኑን ሲሰሙ እግዚአብሔር በባሕርይው ስለማይታይ አምሳሉን አዳምን ለማየት ይጓጉ ነበር። እናም ቅዱሳን መላእክት አዳምን አይተው ሲያከብሩትና ደስ ሲሰኙ ሰይጣን ግን ክፉ ቅንዐትን ቀንቷል። የዲያብሎስን አለመደሰትና አለማክበር አለመስገድ ብሎ ገልጾታል።
▶️፭. "አሳዝነውታልና ክፉ ሥራ የሠሩ ሰዎችንም አስነሥቶ ፈርዶ ወደ ገሃነም ይወስዳቸዋል" ይላል (2ኛ መቃ.9፥16)። መቼም ፍርድ ሲባል የመጨረሻው ቀን (ምጽአት) ነው። መምህር እዚህጋ አንድ ነገር ግልጽ ቢያደርጉልኝ። ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞቶ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ከዲያቢሎስ አገዛዝ (ባርነት) ነጻ አወጣ። አንዳንድ መመህራን "ሲኦል ተመዘበረች ባዶ ቀረች" ይላሉ። ከሲዖል ያወጣቸው በስሙ (በእግዚአብሔር አምላክነት) አምነው የሞቱትን የአዳም ልጆች ብቻ ነው ወይስ በአምላክነቱ ሳያምኑ የሞቱትን አሕዛብንም ጭምር ነው? ለዘለዓለም ወደ ገሃነም የሚገቡ ሲኦል ውስጥ የቀሩ ነፍሳት ነበሩ?
✔️መልስ፦ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ከዚያ በፊት የነበሩ ሕዝብና አሕዛብን በጠቅላላው የአዳም ልጆችን አድኗል። መድኃኔዓለም መባሉ አንዱ በዚህ ነው። ስለዚህ ከዚያ በፊት አምነው የሞቱትም ሳያምኑ የሞቱትም ከሲኦል ወጥተው ወደ ገነት ገብተዋል። እንጂ ያን ጊዜ ሲኦል የቀሩ ነፍሳት አልነበሩም። በመቅድመ ወንጌል ወኀደጎሙ ለእኩያን የሚለውን ሲያትት አጋንንትን በሲኦል እንደተዋቸው ይናገራል። የሰው ልጆች ግን ሁላቸውም ወጥተዋል። ከስቅለት በኋላ ያለን ሰዎች ደግሞ አምነን በመጠመቅና መልካም ሥራን በመሥራት ወደ ገነት እንድንገባ ነጻ ፈቃድ ተሰጥቶናል። ነጻ ፈቃዳችንን ለበጎ እንጠቀምበት። ከስቅለት በኋላ ግን ክፋት ሠርቶ ሲኦል የሚገባ ሰው በኋላ ዘመን ወደ ዘለዓለማዊ ገሃነም እንደሚገባ ተገልጿል (ማቴ.25)።
▶️፮. መቃብያን ማለት ምን ማለት ነው? የመጽሐፈ መቃብያን ጸሓፊስ ማን ነው?
✔️መልስ፦ መቃብያን ማለት የመቃቢስ ዘሮች ማለት ነው። የእነርሱን ታሪክ ስለሚናገር የመጽሐፉ ስም በእነርሱ መቃብያን ተብሏል። የመጽሐፈ መቃብያን ጸሓፊ ከዚሁ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማን እንደሆነ አልተገለጸም። በሌላ የታሪክ መጽሐፍ ካለ ከዚያ ይፈልጉት። ያስጻፈው መንፈስ ቅዱስ ለመሆኑ ግን መጻሕፍት አምላካውያት ከሚባሉት በመመደቡ ታውቋል (ፍት.ነገ.2)።
▶️፯. በለዓም ንጉሡ ባላቅ እስራኤልን እንዲረግምለት ብዙ እጅ መንሻ ቢያቀርብለትም የእግዚአብሔርን ቃል በማክበር ጥያቄውን እንዳልተቀበለ ተገልጿል (2ኛ መቃ.10፥12)። ብዙ ጊዜ ትምህርት ሲሰጥ ግን በለዓም በበጎ ጎን ሲነሣ አልሰማም። በአሉታዊ ሁኔታ በበለዓም መንገድም ሄደዋልና ተብሎም ሌላ ስፍራ ላይ ተጠቅሷል እንጂ። ይህ ሀሳብ እንዴት ይታረቃል?
✔️መልስ፦ በለዓም ጠንቋይ ነው። እስራኤላውያን ሊረግም ሲሄድ እንኳ እግዚአብሔር አፉን ከፍቶ ፊቱን ጸፍቶ ነው አልረግምም ያሰኘው። ፈርቶና ተገዶ ነው እንጂ የእግዚአብሔርን ቃል አክብሮና በእግዚአብሔር አምኖ አልነበረም አልራገምም ያለ። ክፉና ተንኮለኛ ሰው እንደነበረ የሚያሳየን ባይራገም እንኳ ክፉ ምክር መክሮ እስራኤላውያን እንዲጎዱ በማድረጉ ነው።
© በትረ ማርያም አበባው
✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።