በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም dan repost
ወይ እንጀራ ወይ ሞት
ታሪክ ፀሀፊዎች “ዘመነ መሳፍንት “ ብለው በሚጠሩት ፤ እኔ ደሞ “ ዘመነ የጁ “ በምለው ዘመን ውስጥ አንዲት አረሆ የሚከተለውን ግጥም አንጎራጉራ ነበር፤
"እሄዳለሁ ሜጫ እሄዳለሁ ዳሞት
ሳላገኝ አልቀርም ወይ እንጀራ ወይ ሞት "
በነገራችን ላይ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ባላገሮችንና ጌቶችን በፈጠራ በማዝናናት የሚተዳደሩ የግጥምና የዜማ ባለፀጋ ሴቶች ና አረሆ ተብለው ይጠሩ ነበር::
ያኔ ካንዱ አውራጃ ወደ አንዱ አውራጃ የሚኬደው በባዶ እግር፤ ግፋ ቢልም በበቅሎ ነው ! ሲመሽ በሸማ ድንኩዋን ስር ወይም ዛፍ ስር ይታደራል ! አባይን መሻገርማ አይጣል ነበር ፤ ካዞ ብታመልጥ ሽፍታ አይምርህም ! አቶ ሀዲስ አለማየሁ እንዳሉት አባይ “ ብዙ ሞቶች ተሰብስበው የሚገኙበት ቦታ” ነበር፤
በዚያ ላይ በየቦታው መሳፍንቱ ጎራ ለይተው በየቦታው ይከሳከሳሉ ፤ በግርግር መሀል በራሪ ጥይት መሞት መደፈርና መጠለፍ ሊያጋጥም ይችላል!
የጠቀስኩት ግጥም ዝምብሎ የድሮ ግጥም አይደለም! ዛሬም የብዙሀኑን የኢትዮጵያዊ ህይወት የሚገልፅ ይመስለኛል ! “ሜጫንና ዳሞትን “ በሌሎች ቦታዎች ተክቶ ማንበብ ብቻ ነው እሚጠበቅብን ! ከጥቂት አመታት በፊት በሰደት ወጥቶ መሞትን ስናስብ መጀመርያ ወደ አእምሮአችን የሚመጣው አረብ አገር ወይም ደቡብ አፍሪካ ነበር ፤ ብዙ ሰው ወቅቱን ያልጠበቀ ሞት ሸሽቶ ነበር ወደ አሜሪካ የሚሰደደው ሞት አሜሪካ ውስጥ ለመጥፋት የተቃረበ ብርቅየ አውሬ ሆኖ ቆይቷል ፤ ዘንድሮ ይሄ ቀርቷል ! ከሁለት ቀናት በፊት ባንድ ቀን ብቻ ዘጠኝ መቶ ሰባ አንድ ሰዎች እንደ ጥቢ ቅጠል ረግፈዋል! አሜሪካ እንጀራ አምሮት ለመጣ ስደተኛ ሞትን በሰፌድ ማቅረብ ጀምራለች::
ይህ ብቻ አይደለም ! አሜሪካኖች ምርጫ ላይ ናቸው! የትራምፕ ደጋፊዎች እንደ ጌታቸው መጋጣነታቸውን -ወይም ባዲስባ አራዳ አማርኛ " ሰገጤነታቸውን " መደበቅ እሚችሉ አይደሉም ! ሰውየውም ሽንፈቴን በፀጋ አልቀበልም ብሏል ! ደጋፊዎች ጎራ ለይተው ሊላመጡ
ይችላሉ! እዚህ አገር ድብድቡ ከተጀመረ እንደ ሸገር በድንጊያ ወይም እንደ ፍልስጤም በወንጭፍ አይደለም! ሁሉም " ነጣ ዘለግ ያለ ስናይፐር ታጣቂ" ነው!
አሁን ሳስበው መሞቴ ካልቀረ እዛው ባገር በቀል ዱላ መሞት ይሻለኝ ነበር፤ ደግነቱ በሜክስኮ ድንበር ግንብ ታጥሮ አለማለቁ ጠቀመኝ! የፈራሁት ከደረሰ፤ በቅርቡ “ የበውቄ ኩብለላ-ከማንኩሳ እከጉዋታማላ “ የሚል ማስታወሻ ጠብቁ፤
➮ በእውቀቱ ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@bewketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟