በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


እንኳን ወደበእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም በደህና መጡ!
═══════ ══ ═══════

➛በዚ ቻናል ላይ ድንቅ ድንቅ ስራዎች ይቀረባሉ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


​​ዘመም ይላል እንጂ!

እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት
እንደሰው ጭካኔ፤ እንደ ልቡ ፍሬ
ታምር ነው መትረፍሽ ፤ ታምር ነው መኖሬ።

.
የበጎ ሰው ሀሳብ ፤ ሲካድ እለት በለት ጉድጓድ ተምሶለት ሰብእና ሲቀበር፤ በዚህ ምድር መኖር ፤ አያስመኝም ነበር።
.
ምድሩ ሳር ቅጠሉ፤ በስጋት ተሞልቶ
የማለዳው ሰማይ፤ እንዳንቀልባ ቀልቶ
ታረደ
ነደደ

ከዘብጥያ ወጥቶ ዘብጥያ ወረደ የሚል ዜና ብቻ አየሩን ሲሞላው ሰው በገዛ ጥላው
በርግጎ ሲሸበር
በዚህ ምድር መኖር፤ አያስመኝም ነበር።
.
አዎ!
ለጊዜውም ቢሆን፤ ግፍ ያደነዝዛል

በደል ያስተክዛል ጊዜም ጠብን ሽሮ፤ ወደ ፊት ይጓዛል በልብ ሰሌዳ ላይ ፤ ቂም ይደበዝዛል በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ፤ ሚስቱን ያስረግዛል።
ይቅርታና ምህረት
ፍቅርና ህብረት
ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው ፤ ቢሆን የሞት
ሽረት ዳገት ይወጣሉ ፤ በንጥፍጣፊ አቅም የመኖር ፍላጎት ዘመም ይላል እንጂ፤ ተገርስሶ አይወድቅም።

➛ከበእውቀቱ ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


➛➛➛ያበደ ምሽት➛➛➛
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➮ እጅግ በጣም ገራሚ ወግ ናት አድምጧት!

ከበእውቀቱ ስዩም

➮አጣፍጦና አሳምሮ ያቀረበው እራሱ በእውቀቱ ስዩም ነው
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


➛➛➛ዘፈን እና ዘፋኞች➛➛➛
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➮ እጅግ በጣም ጣፋጫ ወግ ናት አድምጧት!

ከበእውቀቱ ስዩም

➮አጣፍጦና አሳምሮ ያቀረበው እራሱ በእውቀቱ ስዩም ነው
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም dan repost
​​የጥቅምት መስክ ነኝ !!

ሰው ለሰው ይፈርዳል
ልብን ዘልቆ ሳያይ
ላልቃሽ እያዘነ

በፈካ ገፅ ውስጥ ያደፈጠን ስቃይ
-ማነው የመዘነ?
የይስሙላም ይሁን፣ከልብ ያለቀሰ
አያጣም አይዞህ ባይ

ካንጀት ይሁን ካንገት ፣ እንባ ላፈሰሰ
አይጠፋም ከምንገድ ፣መሀረብ አቀባይ
ይብላኝ ላሳሳች ፊት፣አፅናኝ ለማይጋብዝ
አንዳንድ ሀዘን አለ

ከላይ ተሰውሮ ፣ ልብ የሚበዘብዝ
የጥቅምት ብሩህ መስክ፣ አደይ የለበሰ
ስንቱን ጉድ አዝሎታል፣ስሩ ከተማሰ!!

የጥቅምት መስክ ነኝ ፣አደይ ያደመቀው
ፈገግታ ቢውጠው፣ዘበት ቢደብቀው
የኔን ብቻ ህመም፣እኔው ነኝ የማውቀው።


➲ ከበእውቀቱ ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@bewketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም dan repost
​​በምድር ላይ ለአንተ ካንተ የባሰ ጠላት ያለ እንዳይመሰልህ። ራስህን ካላሸነፍክ አሸናፊ መሆን አትችልም። አንዳንድ ጊዜ የምታደርገው ነገር ራስህን እያወደመ ካንተ በተቃራኒ ሆኖ ያሰቃየሃል። አንዳንድ ጊዜ ራስህን ራስህ በገነባኽው
እስር ቤት ታሳሪ ታደርገዋለህ። ከዛም ጠባቂው አንተ ተጠባቂውም አንተ ትሆናለህ። አንድ አንድ ጊዜ
የሚያበሽቅህ፣ የሚያስፈራራ፣ የሚያሸማቅቅህ ድምጽ ከራስህ ወደራስ
ይወረወራል። አትችልም፣ አታደርግም፣ ፈሪ ነህ ፣ ተስጦ የለህም እያለህ ከሰው ሁሉ የበታች ያደርግሃል።
ይህን
በውስጥህ ያለውን ሃይል ለማሸነፍ ለራስህ በራስህ ውስጥ ጠበቃ ቁምለት። ከራስህ ጋር ታገል። ራስህን ከራስህ ጋር
አስማማው እና አለም ሁሉ ከአንተ ጋር
ለመስማማት አጁን ይዘረጋል።
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


​​꧁​​❷⓿❶7 ~~❷⓿❶7꧂

②⓪①7🌻እንኳን አደረሳቹ 🌻

አዲሱ ዓመት የሰላም፤ የጤና፤ የፍቅርና፤ የብልፀግና እንዲሁም የእንድነትናየማስተዋል ፤የመቻቻል፤ችግራችንን፤ በጋር የምንቀርፍበት፤ ብሩህ ፤ተስፍ ፤የምንስንቅበት፤ ዓመት ያድርግልን።

ከበእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም አዘጋጅ ክፍል!
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
✦2017✦
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ይቀላቀላሉ! ➢➢➢

@bewketuseyum~ @bewketuseyum
➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟




​​በእያንዳንዱ የምንጓዝበት መንገድ ፈጣሪ አለ ስንቆም ስንተኛ ስንነሳ ሁሉንም እንቅስቃሴያችንን የሚቆጣጠርልን እርሱ ነው ታድያ ለምንድነው የምንፈራው? ለምንድነው ብቻዬን ነኝ የምንለው ለምንድነው ደጋፊ ያጣን እንደሆንን የምናስበው ?

በምታደርገው ነገር በሙሉ ማንም ሰው ባይደግፍህ ነገርግን ፈጣሪ ከጎንህ እንደሆነ ካመንክ ከሁሉ በላይ የሆነው ካንተ ጋር ነውና በፍፁም አትፍራ ! ✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም dan repost
​​ልጅ ሆኜ እናቴ ሽንኩርት ስትከትፍ አብሬያት መሆን እወድ ነበር። አንዳንዴ ታዲያ እኔም እንደሷ ለመላጥ አስቤ ሳላውቀው ሽንኩርቱን ልጬ ልጬ የመጨረሻዋ ላይ ስደርስ፣ ልገልጸው የማልችል የተለየ ደስታ ይሰማኝና ውጤቱን ይዤ ወደናቴ እሮጥ ነበር።

እሷ ግን እንደጥፋት ስለምትቆጥረው ከደረሰችብኝ ትከለክለኝ ነበር፤ እጄን ላመል ጥብስ አድርጋ። እሷ ያስተማረችኝ ትክክለኛው ሙያ ደረቁን የውጭ ሽፋን ልጦ የቀረውን መክተፍ ነው።

አሁን አሁን ከሽንኩርት ይልቅ ሰውን ልጦ እስከውስጡ ማየት የተለየ ደስታንና መደነቅን ይፈጥርብኛል። ሳስበው ሰውም እንደሽንኩርት ሳይሆን አይቀርም።

በተለይ የኛ ሕዝብ ተልጦ ውስጡ ያልታየ ምስጢር ነው፣ ነገር ግን ሁሌም ከላይ ከላዩ ብቻ ተልጦ እየተከተፈ በሕይወት ድስት ውስጥ የሚጨመር።

የፈረንጅ ሽንኩርት ሲልጡት ቀላልና ዐይንንም እንደሚያቃጥለው እንዳበሻው ሽንኩርት አለመሆኑን ሞክሬ አይቼዋለሁ። የተሻለ ወጥ የሚያሰማው ግን ያበሻው ሽንኩርት ነው ይባላል።

ቃሪያውም፣ ሽንኩርቱም፣ ሰዉም ለምን ያበሻው እንደሚያቃጥል አላውቅም። እስከመሀሉ ልጠን መመርመሩ ምናልባት ምስጢሩን ያሳውቀን ይሆን?

ከዶ/ር ምህረት ደበበ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም dan repost
ቴሌግራም ልክ እንደ ቲክቶክ ብዙዎችን ባለሀብት እያደረገ ነው 🤩

ቴሌግራም የቲክቶክን ፈለግ በመከተል አዲስ Telegram Stars የተሰኘ Gift Coin አምጥቷል።

ቴሌግራምም ይህንን ነገር ለማስተዋወቅ Major በተሰኘ Airdrop መሰል ነገር መጥቷል ይህም ሰው invite በማድረግ በቀላሉ የቴሌግራም Star Coin መስራት እንድችሉ ያደርጋል።

1 ሰው invite ስታደርጉ 15 star ታገኛላቹ ⭐️⭐️

ስራውን ለመጀመር ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን ስታርት በሉት 👇🏻👇🏻

https://t.me/major/start?startapp=709140036

https://t.me/major/start?startapp=709140036


ወንድ በራሱ መንገድ.pdf
1.2Mb
✦ወንድ በራሱ መንገድ ✦በpdf ✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟➳➳➳ ይቀላቀላሉ! ➢➢➢
@Daniel_bewketu ~ @Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟


በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም dan repost
​​ድምጽ አልባ ፊደላት

ፀጉሩን አንጨብሮ ፂሙን አጎፍሮ
ጥግ ተቀምጦ ለሚታየኝ ወጣት
ሂድና ታዘዘው ስጠው አንድ ድራፍት

ቅዳለት ደብል ጂን ሃሳቡን ይርሳበት
በፂሙ መጎፈር በፀጉሩ መንጨብረር
ቁጥር ፈታ በሚል በግንባሩ መስመር

ይታየኛል ቋንቃ ይታየኛል ነገር
እዛም ከጨለማው ብቸኝነት ውጧት
ሲጋራዋን ይዛ ለቆመችው ወጣት
ሂድና ታዘዛት የሚጠጣ ስጣት

ምጋ በተፋችው በጭሶቹ መሃል
ሴትነት ሲበደል እህትነት ሲጣል
እናትነት ሲጎድል
ይታየኛል ቋንቃ ይታየኛል ፊደል።


ከኤፍሬም ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@bewketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም dan repost
​​ወይ እንጀራ ወይ ሞት

ታሪክ ፀሀፊዎች “ዘመነ መሳፍንት “ ብለው በሚጠሩት ፤ እኔ ደሞ “ ዘመነ የጁ “ በምለው ዘመን ውስጥ አንዲት አረሆ የሚከተለውን ግጥም አንጎራጉራ ነበር፤
"እሄዳለሁ ሜጫ እሄዳለሁ ዳሞት
ሳላገኝ አልቀርም ወይ እንጀራ ወይ ሞት "
በነገራችን ላይ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ባላገሮችንና ጌቶችን በፈጠራ በማዝናናት
የሚተዳደሩ የግጥምና የዜማ ባለፀጋ ሴቶች ና አረሆ ተብለው ይጠሩ ነበር::

ያኔ ካንዱ አውራጃ ወደ አንዱ አውራጃ
የሚኬደው በባዶ እግር፤ ግፋ ቢልም በበቅሎ ነው ! ሲመሽ በሸማ ድንኩዋን ስር ወይም ዛፍ ስር ይታደራል ! አባይን መሻገርማ አይጣል ነበር ፤ ካዞ ብታመልጥ ሽፍታ አይምርህም ! አቶ ሀዲስ አለማየሁ እንዳሉት አባይ “ ብዙ ሞቶች ተሰብስበው የሚገኙበት ቦታ” ነበር፤

በዚያ ላይ በየቦታው መሳፍንቱ ጎራ ለይተው በየቦታው ይከሳከሳሉ ፤ በግርግር መሀል በራሪ ጥይት መሞት መደፈርና መጠለፍ ሊያጋጥም ይችላል!
የጠቀስኩት ግጥም ዝምብሎ የድሮ ግጥም አይደለም! ዛሬም የብዙሀኑን የኢትዮጵያዊ ህይወት የሚገልፅ ይመስለኛል ! “ሜጫንና ዳሞትን “ በሌሎች ቦታዎች ተክቶ ማንበብ ብቻ ነው እሚጠበቅብን ! ከጥቂት አመታት በፊት በሰደት ወጥቶ መሞትን ስናስብ መጀመርያ ወደ አእምሮአችን የሚመጣው አረብ አገር ወይም ደቡብ አፍሪካ ነበር ፤ ብዙ ሰው ወቅቱን ያልጠበቀ ሞት ሸሽቶ ነበር ወደ አሜሪካ የሚሰደደው ሞት አሜሪካ ውስጥ ለመጥፋት የተቃረበ ብርቅየ አውሬ ሆኖ ቆይቷል ፤ ዘንድሮ ይሄ ቀርቷል ! ከሁለት ቀናት በፊት ባንድ ቀን ብቻ ዘጠኝ መቶ ሰባ አንድ ሰዎች እንደ ጥቢ ቅጠል ረግፈዋል! አሜሪካ እንጀራ አምሮት ለመጣ ስደተኛ ሞትን በሰፌድ ማቅረብ ጀምራለች::

ይህ ብቻ አይደለም ! አሜሪካኖች ምርጫ ላይ ናቸው! የትራምፕ ደጋፊዎች እንደ ጌታቸው መጋጣነታቸውን -ወይም ባዲስባ አራዳ አማርኛ " ሰገጤነታቸውን " መደበቅ እሚችሉ አይደሉም ! ሰውየውም ሽንፈቴን በፀጋ አልቀበልም ብሏል ! ደጋፊዎች ጎራ ለይተው ሊላመጡ
ይችላሉ! እዚህ አገር ድብድቡ ከተጀመረ እንደ ሸገር በድንጊያ ወይም እንደ
ፍልስጤም በወንጭፍ አይደለም! ሁሉም " ነጣ ዘለግ ያለ ስናይፐር ታጣቂ" ነው!
አሁን ሳስበው መሞቴ ካልቀረ እዛው ባገር በቀል ዱላ መሞት ይሻለኝ ነበር፤
ደግነቱ በሜክስኮ ድንበር ግንብ ታጥሮ አለማለቁ ጠቀመኝ! የፈራሁት ከደረሰ፤ በቅርቡ “ የበውቄ ኩብለላ-ከማንኩሳ እከጉዋታማላ “ የሚል ማስታወሻ ጠብቁ፤

➮ በእውቀቱ ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@bewketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


➛➛ይድረስ ላብሮ አደጌ➛➛

●●◦ግጥም በጃዝ◦●●

✰አቅራቢ፦አበባው መላኩ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


የዘር ማጥፋት ዳርዳርታ ስም ማጥፋት ነው።
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━

እጅግ በጣም ገራሚ እና አስተማር ወግ ናት አድምጧት!

➮ ከበእውቀቱ ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@bewketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


ባሻ ደምሴ በምርጫ ለምን ተሸነፉ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
እጅግ በጣም ገራሚ እና አስተማር ወግ ናት አድምጧት!

➮ ከበእውቀቱ ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━


​​ሁሉም ነገር የሚፈጠረው ሁለት ጊዜ ነው፣ በመጀመሪያ በሃሳብ መልክ፣ ከዚያም በገሃዱ ዓለም፡፡ ዛሬ በሃሳብ፣ በንግግርም ሆነ በተግባር የሚዘራው ዘር የነገውን እውነታ እንደሚፈጥርበት የማያስተውል ግለሰብም ሆነ ሕብረተሰብ ጥበብ እንደጎደለው ማሰብ አያስቸግርም፡፡ ይህንን የመዝራትና የማጨድ ሕግ ያልተገነዘበና ስርአት የሌለው ሕብረተሰብ በውጤቱ ለአመለካከቱና ለራሱ የሚገባውንና የሚመጥነውን አለም ይፈጥራል፡፡ ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢](https://t.me/joinchat/AAAAAFek7uctS1ofuUIvWQ)
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@brwketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


​​የጨረቃዋን ውበት የሚሻ ጨለማውን አይሸሽም፣ ጽጌረዳዋን ብሎ የሄደ እሾሁን ፈርቶ አይመለስም
ፍቅርን ከልቡ የሚፈልግ ሰው ከራሱ አይደበቅም ፣እራሱን ፈጽሞ አይሸሽም


የምንፈራው ነገር ብዙ ጊዜ የምንመኘውና የሚበጀንን ነገር ነው። ሰዎች ከእውነተኛ ፍላጎታችን የመሸሽ ባህሪ አለን። በምክንያቶች እራሳችንን እያታለንን፤ ሊነቃ የሚታገለውን ድብቅ ምኞታችንን መልሰን እናስተኛዋለን።

ፍርሃታችንን ብንከታተለው..ጥበባችንንም እዛው ማግኘታችን አይቀም። ለዚህም ነው ልትገባበት የምትፈራው ዋሻ ውስጥ ነው ሀብትህን የምታገኘው የሚባለው። ውብ ነገሮችን ለማግኘት ሰው ፍርሃቱን አልፎ መሄድ አለበት፤ በምንፈግልጋቸው ነገሮችና በእኛ መካከል የቆመው ትልቁ ግድግዳ ካለማውቅ የሚመነጨው ፍርሃት ነው:: ጨለማውን የደፈረ ጨረቃን፤ እሾሁን ያልፈራ ጽጌረዳዋን፤ እራሱን ያወቀ ፍቅርን ማግኘቱ አይቀርም::

ፍርሃታችንን....እንከተለው ፤ የፍርሃት ዱካ እውነትኛ ምኞታችንን ያሳይን ይሆናል። ያንቀላፋውን ምኞት የሚቀሰቅሰውም ይኸው ለፍርሃት የምንሰጠው ምላሽ ብቻ ነው። ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@brwketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


​​✦✗ይህ እውነት የገባኝ ቀን✗✦
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ስለማያገባኝ ሰው ማውራት አቆምኩኝ፣ በማያገባኝ ስፍራ መገኘት ተውኩኝ፣ ምንም ለውጥ በማያመጣ ነገር ላይ መከራከርን ጣልኩት፣ ምንም ተጽእኖ ከማላመጣለት ሰው ጋር መነታረክን ተወት አደረኩኝ፣ ድምዳሜ ላይ ስደርስ ምንም ፋይዳ የማያመጣልኝን ጉዳይ ማሰላሰል እርግፍ አደረኩኝ . . . በአጭሩ የማደርገው ነገር ሁሉ ከዋናው የህይወቴ ዓላማና እሴት ጋር የመጣጣሙን ጉዳይ ማሰብ መኖር ጀመርኩኝ ፡፡━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@brwketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


​​ከሐዘን በኋላ ደስታ እንጂ ምን አለ!
ማጣትን ማግኘት እንጂ ሌላ ምን ይከተለዋል! ምሽቱስ እየነጋ አይደል የሚሄደው?? ከጨለማ በኋላ ብርሃን እንጂ ምን ይመጣል
፡፡ የጨለመው ይበራል ፣ የጠፋዉም ይገኛል ። ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @bewketuseyum
@brwketuseyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.