በእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም dan repost
ልጅ ሆኜ እናቴ ሽንኩርት ስትከትፍ አብሬያት መሆን እወድ ነበር። አንዳንዴ ታዲያ እኔም እንደሷ ለመላጥ አስቤ ሳላውቀው ሽንኩርቱን ልጬ ልጬ የመጨረሻዋ ላይ ስደርስ፣ ልገልጸው የማልችል የተለየ ደስታ ይሰማኝና ውጤቱን ይዤ ወደናቴ እሮጥ ነበር።
እሷ ግን እንደጥፋት ስለምትቆጥረው ከደረሰችብኝ ትከለክለኝ ነበር፤ እጄን ላመል ጥብስ አድርጋ። እሷ ያስተማረችኝ ትክክለኛው ሙያ ደረቁን የውጭ ሽፋን ልጦ የቀረውን መክተፍ ነው።
አሁን አሁን ከሽንኩርት ይልቅ ሰውን ልጦ እስከውስጡ ማየት የተለየ ደስታንና መደነቅን ይፈጥርብኛል። ሳስበው ሰውም እንደሽንኩርት ሳይሆን አይቀርም።
በተለይ የኛ ሕዝብ ተልጦ ውስጡ ያልታየ ምስጢር ነው፣ ነገር ግን ሁሌም ከላይ ከላዩ ብቻ ተልጦ እየተከተፈ በሕይወት ድስት ውስጥ የሚጨመር።
የፈረንጅ ሽንኩርት ሲልጡት ቀላልና ዐይንንም እንደሚያቃጥለው እንዳበሻው ሽንኩርት አለመሆኑን ሞክሬ አይቼዋለሁ። የተሻለ ወጥ የሚያሰማው ግን ያበሻው ሽንኩርት ነው ይባላል።
ቃሪያውም፣ ሽንኩርቱም፣ ሰዉም ለምን ያበሻው እንደሚያቃጥል አላውቅም። እስከመሀሉ ልጠን መመርመሩ ምናልባት ምስጢሩን ያሳውቀን ይሆን?
ከዶ/ር ምህረት ደበበ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟