ለመጀመሪያ ጊዜ ቱርክ እንደሄድኩ እንግዳ ከሆኑብኝ ነገሮች አንዱ እጅግ ንጹህና ውብ ሱፍ የለበሱና ፍጹም ፕሮቶኮላቸውን የጠበቁ ሰዎች መንገድ ላይ የተለያዩ ጥቃቅን እቃዎችን ሲሽጡ መመልከቴ ነበር። በቆይታ የተረዳሁት በርካታ የባንክ ሰራተኞች፥ ሲቪል ሰርቫንቶች፥ መምህራን እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት ቋሚ ሰራ ያላቸው ሰዎች ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት በትርፍ ሰዐታቸው የመንገድ ላይ ሸያጭ ላይ መሰማራት የተለመደ መሆኑን ነበር።እንቅስቃሴ የሚበዛባቸው ጎዳናዎች ላይ በመቆም የባንክ ሰራተኛው ካልሲ፥ መምህሩ ጌጣ ጌጥ፥ የመንግስት ሰራተኛው ውሃ ሊሸጡ ይችላሉ። የዚህ አይነት ትርፍ ሰራ ሀገራችን እምብዛም ስላልተለመደ ለረጅም ጊዜ እንግዳ ይሆንብኝ ነበር።
በሀገራችን ዛሬም ድረስ የተለመደው ማህበራዊ አመለካከት አንድን ሰው ከአንድ ሙያ ጋር ማሰተሳሰር ነው። መምህሩ ከማሰተማር፥ አሊሙ ከማቅራት፥ ዳዒው ከመሰበክ፥ ማህበረሰብ አንቂው ከአክቲቪዝም፥ ምሁሩ እውቀት ከማሰፋፋት ጋር ብቻ ይያያዛሉ። ከዚህ ማዕቀፍ የወጣ ሰራ ሲሰሩ ለብዙዎች እንግዳ ይሆናል፥ አንዳንዱም ተቃውሞውን ያሰማል። ይህ እሳቤ ብዙዎች ከሙያቸው ያለፈ ሌላ ሰራ ላይ በንቃትና በነጻነት እንዳይሳተፉ ማነቆ ሆኗል። ጊዜው፥ እውቀቱ፥ ፍላጎቱና እድሉ እያላቸው የማህበረሰቡን እሳቤ ላለመቃረን ሲሉ ብዙ የሚለወጡበትን እድል ያመክናሉ።
አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ አይደለም የገንዘብ ነጻነት የሚሻ መደበኛ የሚባል ኑሮ ለመኖርም ሁለት፥ ሶሰትና አራት ገቢ የሚያሰገኙ ዘርፎች ላይ መሳተፍ ግድ ይላል።
ለራሰ የሰጠነው ወይም ማህበረሰብ ያሸከመን ደረጃም ሆነ ማዕረግ ከመልፋትና ከመጣርና ከምንታወቅበት ሙያ ውጪ ከመስራት ሊያግደን አይገባም። እንዴት መምህር ሁኜ፥ ባንክ እየሰራሁ፥ ዶክትሬት ጭኜ፥ ዑስታዝና ሽኽ ተብዬ፥ ሲቪል ሰርቫንት ተደርጌ ይሄን እሰራለሁ እያልክ "ብራንድህን" የምትጠብቅበት ዘመን አልፏል። በሀላል መንገድ ለፍቶ አዳሪ ሁን፥ ሌላ ባታተርፍ የአላህን ውዴታ ማግኛ ሰበብ ይሆንሃል።
ኢሰታንቡል የሚገኘው እድሜ ጠገቡና ትልቁ ገበያ Grand Bazaar መግቢያ ላይ እንዲህ የሚል ጹሁፍ ተሰቅሏል:
" ለፍቶ አዳሪ የአላህ ወዳጅ ነው"
©️ኢብራሂም አብዱ