ከዩኒቨርስቲ እንደወጣሁ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን system development division ውስጥ ለአንድ አመት ከስምንት ወር ሰርቻለሁ።
ያኔ ታድያ java ላይ እንሰራ ስለነበር የቤቱ ሲኒዬር ደቨሎፐርና መካሪያችን ተስፋዬ ሰይፉ ይባላል። ተስፍሽ የተወሰነ ነገር ካሳዬኝ በኋላ አንድ ስራ እንድሰራ ይጠይቀኛል። የገባኝ መስሎኝ ነበር ግን ተወዛገብኩና ድጋሚ ጠይቄው አሳየኝ።
ከዛ ስደናበር አይቶኛል መሰለኝ ድጋሚ እንዳልጠይቀው ብቻ ሳይሆን እንዳልሰንፍ በሩን ሊዘጋብኝ ፈልጓል። እና ምን አለኝ መሰላችሁ😅
"ይሄን መስራት ካልቻልክ አስክሬን እየጎተትን ነው ማለት ነው" አለኝ። ህይወት ያለው አስክሬን አለ ማለቱ እኮ ነው 😅
(ወይኔ በላቸው፣ መሳፈሪያ ማጣት አትሉም )
ደግነቱ ሰራሁት መሰለኝ። እና ምን ልላችሁ ነው ሁሉንም ነገር አትጠይቁ google ማድረግ ይለመድ።