ትላንት ሊቨርፑል ዋንጫ ሲያሳካ ከምንም በላይ ደስ የሚለው የቡድን ስራቸው ነበር። ሊቨርፑል በአውሮፓ አስገራሚ ደጋፊ ካላቸው ቡድኖች ምርጡ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከነሱ በተሻላ አንሳ ብትሉኝ ምናልባት የቦርሽያ ዶርትመንድ ደጋፊዎች ናቸው።
በጣም የወደድኩትን አንድ ነገር ላካፍላችሁ። የርገን ክሎፕ ባለፈው አመት በድንገት ክለቡን እንደሚለቅ ሲያሳውቅ ለክለቡም ለደጋፊውም አስደንጋጭ ነበር። ክሎፕ ከሰላሳ አመት በላይ ከዋንጫ ርቆ የነበረን ቡድን እንደገና ወደ ገናናነቱ መልሶ የአውሮፓ ሻምፒዮን እስከመሆን አድርሶት ነበር።
የማንቸስተር ሲቲ አይነኬ ተፎካካሪነት 2 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን አሳጣው እንጅ በአንድ አመት ሲቲ በ98 ነጥብ ዋንጫ ሲያነሳ በ97 ነጥብ ሁለተኛ ሆኖ ጨርሷል። (2018/19)። በተመሳሳይ 2021/22 በተመሳሳይ በአንድ ነጥብ ልዩነት ዋንጫውን አጥቷል።
የሆነ ሆኖ በቆይታው የሻምፒዮንስ ሊግና የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ማሳካት ችሏል።
ባለፈው አመት ግን ደከመው መሰለኝ በቃኝ አለ። የሊጉ የመጨረሻ ቀን ከሲቲ ዋንጫ ማንሳት በላይ የክሎፕ ሽኝት ትልቅ ትኩረትን ሳበ። ክሎፕም በፕሮግራሙ ላይ ተተኪውን አሰልጣኝ ስሙን እየጠራ ደጋፊዎቹን በሱ መሪነት እንድዘምሩለት አደረጋቸው። "Arne slot Lalala" አሉ። አስቡት አሰልጣኙ ገና ክለቡን አልተረከበም።
ክለቡም ደጋፊውም ያልጠበቀውን አቀባበል አደረጉለት፣ እሱም ገና በመጀመሪያ አመቱ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ አሽነፈላቸው። ዋንጫውን ትላንት ሲያሳኩ አርነ ስሎት የክሎፕን ውለታ አልረሳም። እሱም በተራው ትላንት "Jurgen klop Lalala " ብሎ አዘመረለት።
አስቡት እንድህ አይነት መሪዎች ቢኖሩን
#YWNA
#leadership
#liverpool
#premierleague2025
#PremierLeague