ከነጃሺ ኢስላማዊ ማህበር ( ከአ/አ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር ) የተላለፈ መልዕክት
ህልውናችን በትግላችን ይፀናል !!
ሚያዝያ 23/2011 በተቀመረ ሴራ የሰለፊ/ወሃቢ ቡድን መጅሊስ ውስጥ መግባቱ የታወቃል። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ብዙ ሁከት በየመሳጂዱ አስተናግደዋል። አዲስ አበባ መጅሊስን እንዲመራ በተቀዳሚ ሙፍቲ ደብዳቤ የተሾመው ሱልጣን አማን አዲስ አበባ መጅሊስን ከረገጠበት ቀን አንስቶ ነባሩ ሙስሊም ማህበረሰብ ለዘመናት ደምና አጥንት ከፍሎ የገነባቸው ከ60 በላይ መሳጂዶችን በመንጠቅ ለተደራጁ የወሃቢያ ቦዘኔዎች ለማስከብ በሚፅፋቸው ደብዳቤዎች በየመስጂዱ ብዙ ሁከቶች ተከስተዋል። ይህን ያስተዋለው ፌደራል መጅሊስ ባለፈው ሳምንት አቶ ሱልጣን አማን እና ሌሎች ሁከት ፈጣሪ የወሃቢያ አመራሮች ከሹመት መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ፃፈላቸው።
ሰኔ 18/2014 ከጠዋቱ 12 ሰአት ከሥራ ሰአት ውጭ አቶ ሱልጣን አማን እና ግብረ አበሮቹ ፌደራል መጅሊስ ከሹመታቸው እንዲነሱ የፃፈው ደብዳቤ ተግበራዊ ሊሆንብን ነው ሳንቀደም እንቅደም ብለው የመጅሊሱን ቋሚ ዘበኞች በመደብደብ እና ወደ ፎቁ የሚያስወጣውን በር በመስበር የውንብድና ተግባር ፈፅመው ጥበቃዎቹን አባርረው ከ20 በላይ ቦዘኔዎችን ለጥበቃ በሚል ሽፋን መጅሊሱ ጊቢ ውስጥ ውለው እንዲያድሩ መቀለብ ጀመረ። የአዲስ አበባ መጅሊስ ምክትል ፕሬዝደንት ሸህ ዓሊ እና የቦርድ ፀሀፊው ቶፊቅ ወደ ቢሮ ሊገቡ ሲል አቶ ሱልጣን ያደራጃቸው ወንበዴዎች እንዳይገቡ ከለከሉ። ይህ ሁሉ ሲሆን በአካባቢው ያለው የጸጥታ አካል ሙሉ መረጃው እያለው እርምጃ እንዲወስድም እየተጠየቀ ዝምታን መረጠ።
ትላንት ሰኔ 23/2014 ሸህ ዓሊ ወደ ቢሮ ለመግባት ለምን ተከለከሉ ብለው የተቆጡ ኢማሞችና ወጣቶች ሸህ ዓሊን አጅበው ወደ ቢሮ ለማስገባት አዲስ አበባ መጅሊስ ጊቢ ውስጥ ቢገኙም አቶ ሱልጣን ያደራጃቸው ወንበዴዎች ድንጋይ መወርወር እና ሚስማር ባለው ዱላ ጥቃት ማድረስ ጀመሩ ሁከት ተፈጠረ በመሀል ቦዘኔዎቹ ወደ ፎቅ በመውጣት ወደታች ድንጋይ ሲወረውሩ የቢሮ መስታወት ተሰበረ። ሁከት ቀስቃስሽ ድንጋይ ወርዋሪ ጥቃት አድራሽ መስታወት ሰባሪዎቹ የአቶ ሱልጣን ቦዘኔዎች ናቸው።
ከትላንት እስከዚህ ሰአት ድረስ ያለ ወንጀላቸው ታስረው ጣቢያ የሚገኙ ከ150 በላይ የሚሆኑ ሙስሊሞች እስካሁን ይፈታሉ በማለት ከፖሊስ መምሪያው የተለያዩ መሬት ያልረገጡ ሃሳቦችን እየሰማን በትእግስት እየጠበቅን የቆየን ቢሆንም ዛሬ ከረፋዱ ጀምሮ እስከ 8 ሰአት ድረስ ከ5 በላይ የሚሆኑ ዑለማኦች የጣቢያው ኃላፊን ቢያናግሩትም ኢማሞቹን እንጂ ወጣቶቹን አልለቅም፣ ወጣቶቹን ከለቀቅኩ ወሃብዮቹ ይጮሁብኛል ስማችንን ያጠፉታል ፍርድ ቤት ቀርበው ፍርድ ቤት በዋስ ይልቀቃቸው የሚል ደረቅ ምላሽ እንደሰጠ ለማወቅ ተችሏል። ከፍትህ ይልቅ የወሃቢያ ጩኸትና ስም ማጥፋት የሚፈራበት ፍትህ አልባ ወቅት ላይ ደርሰናል። እንደ ሀገር እጅግ ያሳዝናል።
በመሆኑም ለ1400 አመታት ደምና አጥንት ተከፍሎበት የቆየውን ነባሩን እስልምና ለማስቀጠል ሲሉ የታሰሩ ከ150 በላይ የሚሆኑ ወንድሞቻችን ታስረው እኛ በነፃነት ቤታችን ቁጭ ብለን ዝም እንደማንል የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ሊያውቁት ይገባል። ከገጠር እስከ ከተማ ጫፍ ድረስ ያለው ህዝባችን የታሰሩ ወንድሞቻችንን ጉዳይ በትኩረት እየተከታተለው እና ምን እናግዝ እዘዙን ከእናንተ ጋር ነን እያለ ፍፁም የነቃ ዝግጁነት ላይ ይገኛል።
መንግስት ያለ ወንጀላቸው የታሰሩ ልጆቻችንን በአስቸኳይ እንዲፈታቸው እንጠይቃለን። የወሃቢያ ጩኸት ተፈርቶ ልጆቻችን በእስር እንዲማቅቁ ፈፅሞ አንፈቅድ