ከ"ሜሎሪና" መጽሐፍ የተወሰዱ ሀሳቦች
📕 ‹‹ትልቁ ብቸኝነት ሰውን ማጣት ሳይኾን ራስን ማጣት ነው። በምድር ላይ ራሱን እንዳጣ ሰው ብቸኛ የለም። ራስን ማጣት፥ በኛ ውስጥ ያሉ ችሎታዎቻችንን አቅማችንንና ስሜቶቻችንን ማጣት ነው፡፡ እራሱን ያጣ ሰው በዙሪያው እልፍ ሰዎች ቢሰበስብ እሱ ግን ዘወትር ብቸኛ ነው።››
📕‹‹...ትዝታ ለብዙ ሰው የዕድሜ ዘመን እስር ቤት ነው። ብዙ ሠዎችም ወደፊት መራመድ እየፈለጉ አስሮ የሚይዛቸው በገዛ አዕምሮአቸው ውስጥ ያስቀመጡት የትናንት ታዝታቸው ነው።››
📕‹‹አፍሪካ ውስጥ ‹ሕዝቡ› እንደሚለው ቃል በመሪዎች የተነገደበት ቃል የለም። አንዳንዱ መሪ ሕዝቡ የሚለው የገዛ ራሱን እሳቤ ነው። ሌላው ደግሞ ቤተሰቦቹንና ዘመዶቹ ብቻ ነው ሕዝቡ ብሎ የሚቆጥረው።››
📕‹‹በህይወት ስትኖር መቼም ቢሆን ኹሉንም ሰው ማስደሰት አትችልም፤ ማወቅና መጠንቀቅ ያለብህ ዋናው ቁም ነገር ማስከፋት የሌለብህን ሰው ለይተህ ማወቁ ላይ ነው።››
📕‹‹ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእምሮ ነው፤ ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍ ነው››
“Dirreen lolaa inni guddaan sammuu namaati, Injifannoo guddaan of mo’uudha
📕የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ መጠኑና ስፋቱ ቢለያይም፣ ራሱ በሠራው አሊያም ሌሎች ባጠሩለት እስር ቤት ይኖራል፡፡ እንደ ራሱ አሳብና አመለካከት ግን ትልቅ እስር ቤት የሚኾንበት አንዳች ነገር የለም፡፡ ለካስ እስር ቤት ቦታ ሳይኾን አስተሳሰብ ነው፡፡ በዚህች ምድር እጅግ ብዙ ሰው በአእምሮው እስር ቤት ውስጥ በአሉታዊ አስተሳሰብ ታስሮ፣ በከንቱና እንቶ ፈንቶ ፍርሀት ተይዞ ማንም እንዳይረዳው ኾኖ የእስር ቤት ቊልፉን ራሱ ደብቆ ይኖራል።
💚ሜሎሪና - ስውር ጥበብ
💛ሜሎሪና - ቴሎስ
❤️ሜሎሪና- ሕይወቴ
መጽሐፉን በኹሉም የመጽሐፍ መደብሮችና ከአዟሪዎች እጅ ይገኛል።