ኤንቪዲያ አዲስ የጄኔሬቲቭ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሱፐር ኮምፒዩተር አስተዋወቀ፡፡
ኩባንያው የእጅ መዳፍ መጠን ያላቸው ጄትሰን ኦሪን ናኖ የተባሉ ሱፐር ኮምፒዩተሮችን በ249 ዶላር ዋጋ ለገበያ አቅርቧል፡፡
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቶችን ለማበልፀግ ገበያ ከሚውሉ መሰል ኮምፒዩተሮች አንጻር ጄትሰን ኦሪን ናኖ እጅግ በርካሽ መቅረቡ ተመላክቷል፡፡ ኮምፒዩተሩ ጄኔሬቲቭ ኤ.አይ፣ ሮቦቲክስ እና የኮምፒዩተር ቪዥን ሲስተሞችን ለማበልፀግ ግልጋሎት ላይ እንደሚውል የኩባንያው ድረ-ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡
ጄትሰን ኦሪን ናኖ በአፈጻጸም አቅሙ ከቀደሙት ተመሳሳይ የኩባንያው ምርቶች አንጻር 70 በመቶ እድገት አለው፡፡ በዚህም ጄኔሬቲቭ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኮምፒዩተር ቪዥንን መሰረት ላደረጉ ሞዴሎች የተሻለ አፈጻጸም ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡
ሱፐር ኮምፒዩተሩ በዘርፉ ነጠላ ስራን ከሚከውኑ ሞዴሎች ሀሳብን ወደ እውነታ ገቢራዊ ለማድረግ መሰረት የሆኑ ሞዴሎችን ለማልማት ሽግግር በማድረግ ምቹ መደላድልን ይፈጥራል፡፡
ኤንቪዲያ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ እና ለሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ሲስተሞች ዕውን መሆን ግብዓት የሆኑ የግራፊክስ ማቀነባሪያ ክፍሎችን (ጂ.ፒ.ዩ) በማምረት ይታወቃል