ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር... dan repost
🟢🟡🔴
ጥር 21 | #እመቤታችን በማይነገር ክብር ዐረፈች።
#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር። ከነገር ሁሉ በፊት እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር።
ከልጇ ዕርገት በኋላ በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትን ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች። በጽርሐ ጽዮንም ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ15 ዓመታት ኖረች።
በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ፣ ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል፣ ሐዋርያትን ስታጽናና፣ ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች።
🌹 አስደናቂው ዕረፍቷ 🌹
ዕድሜዋ 64 በደረሰ ጊዜ ጥር 21 ቀን መድኃኒታችን አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ። ኢየሩሳሌምን ጨነቃት። አካባቢውም በፈውስ ተሞላ። በዓለም ላይም በጎ መዓዛ ወረደ።
እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት ባልተደረገ፣ ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ፣ ክብርና ተአምራት ዐረፈች። ሞቷ ብዙዎችን አስደነቀ።
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ፥
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ" እንዲል።
ከዚህ በኋላ መላእክት እየዘመሩ፣ ሐዋርያቱም እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ፣ በአጎበር ሥጋዋን ጋርደው ወሰዱ።
በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ ቅዱስ ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው) እነርሱን ቀጥቶ፣ ሥጋዋን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ ከዕፅ ሕይወት ሥር አኑሯታል። እንደ ልጇም ከሞት ተነሥታ አርጋለች።
-🌹-
ልደታቸው ከልደቷ፣ ዕረፍታቸው ከዕረፍቷ የተዋደደላቸው #አቡነ_ቀውስጦስ ዐረፉ።
ከቅዱስ ገላውዴዎስና ከቅድስት እምነ ጽዮን በእመቤታችን አማላጅነትና ብሥራት የተወለዱ ናቸው።
ባረፉም ጊዜ እመቤታችን በሰማይ መካከል ነፍሳቸውን በፈገግታ ተቀብላ "መታሰቢያህን ለሚያደርጉ ሁሉ በልጄ በረከት እበርካቸዋለሁ" ብላ ቃል ኪዳን ገባችላቸው።
ከጌታችን የተሰጣቸው ቃልኪዳን 👉 t.me/Ewnet1Nat/9819