የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምስተኛ ድሉን አስመዘገበ፡፡
**********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀምበርቾን 4 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 9፡00 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው በዚህ ጨዋታ ሴናፍ ዋቁማ አራቱንም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎሎች አስቆጥራለች፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በውድድር ዓመቱ ካደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች አምስቱን ማሸነፍ ሲችል፣ በአንዱ አቻ ተለያይቷል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከታታይ ባስመዘገባቸው ድሎች ቀሪ አራት ጨዋታ እየቀረው ከመሪዎቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ማጥበብ ችሏል፡፡