ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ምስጋና ቀረበ፡፡
************
‘የላቀ አገልግሎት፣ ደስተኛ ደንበኛ’ በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ከሚገኘው የደንበኞች የአገልግሎት ወር ጋር በተያያዘ በዛሬው ዕለት የዋናው መሥሪያ ቤት ሠራተኞች የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡
በሁነቱ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የካስተመር ኤክስፔሪያንስ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ ደንበኞቻችን የህልውናችን መሠረት መሆናቸውን ገልፀው፣ ከባንካችን ጋር በታማኝነት ስለሚሠሩም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ባንካችን ሰሞኑን በተለያዩ አካባቢዎች ከደንበኞች ጋር የውይይት መድረክ ማካሄዱን የገለፁት አቶ ኃይለየሱስ፣ የደንበኞች አገልግሎት ወር በዲስትሪክቶች እና በቅርንጫፎች በድምቀት እየተከበረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አቶ ኃይለየሱስ የባንካችን የህልውና መሠረት የሆኑትን ደንበኞች ለሚያገለግሉት መላው የባንኩ ሠራተኞችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡