የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha


ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ላይ ግቢ ጉባኤውን በተመለከተ መልእክቶች ፣ መንፈሳዊ ጽሑፎች ፣ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎች መሰል መልእክቶች ይተላለፉበታል፡፡
ያሏችሁን ጥያቄዎችና አስተያየት በዚህ bot ይላኩልን👉 @CommGibiGubae_bot

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


የ2019 ዓ.ም ልዩ የመክፈቻ ጉባኤ
3 ቀን ቀረው!

📆ማክሰኞ መስከረም 26፤ 2019 ዓ.ም ⏰ከ7:30 ሰዓት ጀምሮ
📍በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

እንኳን ለግሸን/ለብዙኃን ማርያም በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ማርያም ድንግል ምክሖን ለደናግል
ይእቲኬ ቤተ ምስአል
ዘአስተዓጸቡ ታቀልል
ለኲሉ ፍጥረት ትተነብል
በአክናፈ መላእክት ትትኬለል
ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል
ወትፈደፍድ እምሱራፌል
መንክር ወመድምም ዕበያ ወክብራ ለድንግል
ጽሕፍት ውስተ ወንጌል
ወዲበ ርእሳኒ አክሊል
በትእምርተ መስቀል።

በዐፄ ዳዊት አማካኝነት ከግብጽ የመጣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል “አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል” እንደተባለ የመስቀል ቅርጽ ባለው በግሸን ተራራ በደብረ ከርቤ የገባው መስከረም 21 ቀን ነው። በዚህች ዕለት ሕዝብ ሁሉ በአንድነት የተሰበሰቡበት ዕለት ስለነበረ ዕለቱ “ብዙኃን ማርያም” እየተባለ ይጠራል።

ከእመቤታችንና ከቅዱስ መስቀሉ በረከት ረድኤት ያካፍለን!

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

ውድ የግቢ ጉባኤያችን አባላት እንኳን ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ

እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ
                                                                   ምሳ 2፥6


እነሆ በጉጉት የጠበቅናት ቀን ደረሰች።
የክረምቱን ወራት አሳልፎ በሰላምና በጤና ጠብቆ ለ2019 በሰላም ያደረሰን የልዑል እግዚአብሔር ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን!

ከእረፍት በኋላ ወደተማርንባትና ወደምንወዳት ግቢ ጉባኤያችን እንኳን ደህና መጣችሁ እያልን ዓመቱ ከመደበኛው የአስኳላ ትምህርታችን ጎን ለጎን መንፈሳዊ ማንነታችን የሚገነባበት ፣ በቅዱስ ቃሉ የምንታነጽበት ፣ በትምህርታችን የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በመንፈሳዊ ህይወታችን ደግሞ በእምነትና በበጎ ምግባር ለመበርታት የምንሠራበት ዘመን እንዲሆን አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር ፈቃዱ ይሁንልን።

የ2019 ዓ.ም ልዩ የመክፈቻ ጉባኤ
📆ማክሰኞ መስከረም 26፤ 2019 ⏰ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ
📍በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን

ለበለጠ መረጃ በ +251 90 977 9252 ወይም
+251 99 118 4116
ይደውሉ

መልካም የትምህርት ዘመን!

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 
Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
         
      🎊 መዝሙር ጥናት 🎊
ወዝክረ ቅዱስ እስጢፋኖስ

ሰላም የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁን? የመጪው ማክሰኞ መስከረም 19 ለመክፈቻ ፕሮግራም ለሚኖረን ልዩ መርሐግብር የመዝሙር ጥናት መርሐግብራችን ይጀምራል።  ስለሆነም ኹላችንም ላልሰሙት ጓደኞቻችንን አሰምተን የመዝሙር ጥናቱን እንካፈል።
  
🗓ማክሰኞ መስከረም 19
⏰7:00 - 10:00⏰

ለበለጠ መረጃ:-
+251907284500

📍 በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 
Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
         
      🎊 መዝሙር ጥናት 🎊
ወዝክረ ቅዱስ እስጢፋኖስ

ሰላም የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁን? የመጪው ማክሰኞ መስከረም 19 ለመክፈቻ ፕሮግራም ለሚኖረን ልዩ መርሐግብር የመዝሙር ጥናት መርሐግብራችን ይጀምራል።  ስለሆነም ኹላችንም ላልሰሙት ጓደኞቻችንን አሰምተን የመዝሙር ጥናቱን እንካፈል።

  
🗓 ማክሰኞ መስከረም 19
⏰7:00 - 10:00 ⏰

ለበለጠ መረጃ:-
+251 907284500

📍በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 
Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

መስከረም 17 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበረ መስቀል ከተሰወረበት ቦታ የተገለጠበትን ታላቅ ክስተት የምናስብበት በዓል ነው። አይሁድ የመስቀሉን ቦታ እንዳይታወቅ ከቤቶች የሚወጣውን አፈርና ጉድፍ በላዩ ላይ እንዲጥሉ በማዘዝ ከ300 ዓመት በላይ ኮረብታውን ከምረውት ነበር። ንግሥት ዕሌኒ ግን ወደ ኢየሩሳሌም በመጣች ጊዜ የጌታችንን መስቀል ለማግኘት ኮረብታውን እንዲቆፍሩና እንዲጠርጉ አደረገች፤ በመጨረሻም የከበረው መስቀል ተገልጦ ተገኘ። ከዚህም በኋላ ለመስቀሉ የሚያምር ቤተ ክርስቲያን አሠራች፣ የመስቀሉም ክብር በታላቅ ሁኔታ በመስከረም 17 ቀን የመስቀል በዓል ተከበረ።

መልካም የመስቀል በዓል ይሁንልን!

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

እንኳን ለመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ዮም በዓለ መስቀሉ በሰማያት በላዕሉ
ወበምድር በታሕቱ ገብረ ሰላመ ለኲሉ

ዛሬ የመስቀሉ በዓል የሚከበረው በላይ በሰማያት ጭምር ነው ለምድር ሁሉ ለአሕዛብ ያበራ ዘንድ በምድር የነገሠ የከበረ ነውና በሰላምና በደስታ ዘወትር በቅዱሳን ይመሰገናል።
                                                     ቅዱስ ያሬድ


መስቀል ለዓለም ሁሉ የሚያበራ የመላእክት የድላቸው ምልክት የቅዱሳን የተጋድሏቸው ዓርማ ነውና በመላእክትና በቅዱሳን ዘንድ ዘወትር ይመሰገናል፡፡

እኛም ኦርቶዶክሳውያን ጌታ በክቡር ደሙ ያከበረው በቅዱስ ሥጋው የቀደሰውና መለኮታዊ ኃይሉ ያረፈበትን የመስቀልን በዓል ደመራ በማብራት በዝማሬና በምስጋና እናከብራለን።

መልካም በዓል!

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

እንኳን ለ2019 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

“በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ” (መዝ 64÷11)


         ማርቆስ ተሻረ ሉቃስ ተሾመ

የሰው ልጅ በዘመናት ዑደት ራሱን እያሻሻለ ፣ የጠመመውን እያቀና ፣ የጎደለውን እየሞላ ለመጓዝ በዐዲሱ ዘመን ያቅዳል፡፡ ከሁሉ በላይ ግን ሥጋዊ ደስታና ምኞት በመላባት በዚህች ዓለም ላይ ለመንፈሳዊ ህይወታችን የምንሰጠው ቦታና ጊዜ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ነው።

መስከረም አንድ በዐዲስ አበባ ሜክሲኮ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ እና በመርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አብያተ ክርስቲያናት ታቦታተ ሕጉ ከመንበረ ክብራቸው ተነስተው ህዝበ ክርስቲያኑን ይባርካሉ በሌሎችም አድባራት በዝማሬና በቅዳሴ ዐዲሱን ዓመት ልንቀበል ይገባናል፡፡

ዐዲሱ ዓመት መልካሙን የምንሰማበት ፣ በጎውን የምናይበት ይልቁንም በልህቀት መንፈሳዊ የምንጎለብትበት ይሆን ዘንድ አምላካችንን በጸሎት መጠየቅ ይጠበቅብናል፡፡

መልካም ዐውደ ዓመት ይሁንልን!

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

እንኳን ለቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ ጳጉሜ 3 የቅዱስ ሩፋኤል መልአክ መታስቢያ ዓመታዊ ክብረ በዓሉ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

ቅዱስ ሩፋኤል የጦቢትን ዓይን ያበራበት ወለተ ራጉኤልን ተቆራኝቷት ከነበረው ጋኔን ያዳነበት እንዲሁም ከእስክንድርያ ውጪ በደሴት ላይ የታነጸች ቤተ ክርስቲያኑ በከበረ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን በውስጧ ተአምርን የተገለጠባት ዕለት ናት።

በልጅነት እድሜያችን በየመንደሩ እየሮጥን የተጠመቅነው ጠበል ስንቶቻችን ትዝ ይለን ይሆን ?

በጳጉሜ ውኃውን ወፍ ሳትቀምሰው በሌሊት ወደ ወንዝ ወርዶ መጠመቅ በአብዛኛው የሀገራችን አካባቢዎች የተለመደ ነው። ይህም እንደ ሰሊሆም በጳጉሜ ውኃው የተባረከ ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው። ዝናሙ ዝናመ ምሕረት ጠበሉ የበረከትና የድኅነት ይሁንልን።

    የቅዱስ ሩፋኤል አማላጅነት አይለየን!

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
"እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ"
እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል አምላካችንም ዝም አይልም በፊቱ እሳት ይነዳል፡፡
                              መዝ 49፡3

እንኳን የዘመን መባቻ ለሆነችው ለወርኅ ጳጉሜን አደረሳችሁ።

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወርኀ ጳጉሜን የዓለም ፍጻሜ መታሰቢያ ተደርጋ ትታሰባለች። የጌታ ዳግም መምጣት በዓመት ለሁለት ጊዜያት ይታሰባል የመጀመርያው በዐቢይ ጾም አጋማሽ በደብረ ዘይት ሲሆን ሁለተኛው በወርኀ ጳጉሜን ዘመነ ክረምት ላይ ነው።

በዘመነ ክረምት ወርኀ ጳጉሜን ከነባሩ ዓመት መጠናቀቅና ከመጪው አዲስ ዘመን ጋር ተያይዞ ቤተ ከርስቲያን የጌታን ዳግም የመምጣት ነገር በስብከቷ በቅዳሴዋና በዝማሬዋ ታስባለች።

እኛም በዚህ ወር ጌታችን ዐዲሱን ዓመት እንዲባርክልን በጾም በጸሎት እንዲሁም ጸበል በመጠመቅ ማሳለፍ ይገባናል።

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

   የነጻ አገልጋዮች (volunteers) ጥሪ
Bete Tselot app is non profit application that aims to help the orthodox community especially those who do not have access to physical prayer books have easy and reliable access. If you are interested in helping please fill this contact information to volunteer

ቤተ ጸሎት ለትርፍ ያልተቋቋመ መተግበሪያ ሲሆን ኦርቶዶክሳዊያን በተለይም የጸሎት መጽሐፍን ማግኘት የማይችሉን ለማገዝ ያልማል። ይህን ዓላማ ለማገዝ የምትፈልጉ ከታች የተቀመጠውን ፎርም በመሙላት ተመዝገቡ።

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeKdXf9og8Xt2n0h3cqncj_WgIjEw5jDLV56STcPqBc_Yzo9g/viewform?usp=dialog)

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

እንኳን ለአባታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖትና ለእናታችን ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የዕረፍት በዓል ‎ አደረሳችሁ!

መድኃኒታችንም እንዲህ አለው ወዳጄ ሆይ አንተ በመከራዬ መሰልከኝ እኔም በመንግሥቴ ከእኔ ጋራ እንድትመስለኝ አደርግሃለሁ። እነሆ የዚህ ዓለም ድካምህ ተፈጸመልህ በእኔ ዘንድም የምቀበለው ሆነ ከእንግዲህስ መንግሥተ ሰማያትን ትወርስ ዘንድ ና። እነሆ ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ገድልህን ለሚጽፍ ለሚያነበውና ለሚሰማውም ቤተ ክርስቲያንህን ለሚሠራ በስምህ መባ ለሚሠጥ ለድሆችም በስምህ ለሚመጸውት በመታሰቢያህም ቀን ለሚቆርብ ስለ አንተ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ እኔ እስከ ዐሥር ትውልድ እምርልሃለሁ።

ከዚህም በኋላ አባታችን በንዳድ በሽታ ታመመ ዕድሜውም ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከስምንት ወር ከአንድ ቀን ሆኖት በለመለመ ዕርጅና አረፈ። በመዘመርና በማመስገን አክብረው ገንዘው በዋሻው ውስጥ ቀበሩት።

ጌታችንም ለእናታችን ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እንዲህ አላት "አንቺን የሚወዱ፤ ስምሽን የሚጠሩ፤ ዝክርሽን የዘከሩና በዓልሽን ያከበሩ እስከ ፲ ፪ ትውልድ እምርልሻለሁ»

በመጨረሻም ተጋድሎዋን ፈጽማ ነሐሴ ፳፬ ቀን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታ መላእክት አሳረጓት።

ከበዓሉ ረድኤት በረከትን ያካፍለን!

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

✨ዝክረ ቅዱስ እስጢፋኖስ✨
       
📆 ቅዳሜ ነሐሴ 23 ፤ 2018 ዓ.ም 

⏰ ከ7:00-8:00

⛪️ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ

            
በመርሐግብሩ ላይ ተገኝተን ከሰማዕቱ በረከት እንድንሳተፍ በእመቤታችን ስም እናሳስባለን።

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

      ✨ዝክረ ቅዱስ እስጢፋኖስ✨
       
📆 ቅዳሜ ነሐሴ 23 ፤ 2018 ዓ.ም 

⏰ ከ7:00-8:00

⛪️ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ

            
በመርሐግብሩ ላይ ተገኝተን ከሰማዕቱ በረከት እንድንሳተፍ በእመቤታችን ስም እናሳስባለን።

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርኃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ኦ ርኅርኅተ ሕሊና አፍቅሮተ ሰብእ ልማዳ።
ሰአሊተ ምሕረት ይእቲ ማርያም ሐፁረ መስቀል ዘየዓውዳ።
ንትቀበላ ንዑ ለወለተ ዳዊት ዘይሁዳ።
መጽአት ነያ ኅቡረ ምስለ ወልዳ።
ናንፈርዕፅ ቅድመ ሥዕላ እንዘ ንሁብ ጋዳ።
ለለጌሠሙ ትመስል እንግዳ።
                                         መልክአ ሥዕል


ከልብ የምትራራ እመቤታችን ሰውን መውደድ ልማዷ ነው። የመስቀል ጋሻ የሚጋርዳት እመቤታችን ማርያም ምሕረትን የምትለምን ናት። ከይሁዳ ነገድ የተገኘ የዳዊትን ልጅ እንቀበላት ዘንድ ኑ። ከልጇ ጋር አብራ እነሆ መጣች። በየጊዜው እንግዳ ትመስላለችና በሥዕሏ ፊት እጅ መንሻን እየሰጠን ደስ ይበለን።

የፍልሰታዋ መታሰቢያ 3ተኛ ሱባዔ እነሆ ተፈጸመ።

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

እንኳን ለእመቤታችን በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

ሰላም ለሥጋኪ እግዚአብሔር ዘመሠጣ። ከመ ተሀሉ በህየ ለማህደረ ብርሃን በውስጣ። ወለተ ካህናት ማርያም ፈጻሚተ ቃላት የውጣ። አዕዳወ ፍቅርኪ በላዕሌየ ይሡጣ። እፍረተ መዓዛ ቅድወ ዘብዙኅ ሤጣ።


"እግዚአብሔር ወደ ላይ ለነጠቃት/ላረገችው ለሥጋሽ ሰላምታ ይገባል። በብርሃን ማደሪያ ውስጥ ትኖር ዘንድ። የካህናት ልጅ ማርያም ሆይ፥ የብሉይ ኪዳንን ቃላት የምትፈጽሚ ነሽ። የፍቅርሽ እጆች በላዬ ላይ ይዘርጉ። መዓዛው እጅግ ያማረና ዋጋው ብዙ የሆነ ሽቶ ነሽ።"

ሐዋርያት ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ዕረፍት በኋላ ከእነርሱ በመለየቷ ባዘኑበት ወቅት ወንጌላዊ ዮሐንስ በገነት ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ተመልሶ ወደ ምድር ወረደ። ለሐዋርያትም መላእክት በታላቅ ክብር በምስጋና እንዳሳረጓት ነገራቸው፡፡ ሐዋርያትም ይህን በሰሙ ጊዜ  እጅጉን አዝነው በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ ነሐሴ ዐሥራ ስድስትም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው፡፡ በታላቅ ክብር በተወደደ ልጇ ቀኝ ተቀምጣ፣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ፣ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት፡፡ እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን ባረከቻቸው፡፡ ጌታችን ሠራዔ ካሕን ቅዱስ እስጢፋኖስ ዲያቆን ሆነው ቀድሰው ሥጋውንና ደሙን አቀብሏቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ፡፡

ጌታችን አምላካችን በእመቤታችን አማላጅነት ይምረን ዘንድ ከበዓሏም በረከትን እናገኝ ዘንድ ፈቃዱ ይሁንልን! አሜን፡፡

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

✨ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን ለገለጠበት ለበዓለ ደብረ ታቦር እንኳን በሰላም አደረሰን! ✨

ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዕለት እረኞች ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል፡፡ ‹ቡሄ› ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና በበዓሉ ችቦ የሚበራውም ከዚህ ታሪክ በመነሣት ነው፡፡ ለክርስትና ልጅ፣ ለአማች፣ ለምራት፣ ለዘመድ አዝማድ ዅሉ የቡሄ ዳቦ ይሰጣል፡፡ ልጆችም ዳቧቸውን እየገመጡ ጅራፍ ሲገርፉ ይውላሉ፡፡ የጅራፉ መጮኽ የድምፀ መለኮት ምሳሌ ሲኾን፣ ጅራፉ ሲጮኽ ማስደንገጡም ነቢያትና ሐዋርያት በድምፀ መለኮት መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን ያስታውሳል፡፡ ልጆች ‹‹ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና፤ የቡሄው ብርሃን ለእኛ በራልን …›› የሚለውንና ይህን የሚመስሉ መንፈሳውያን መዝሙራትን እየዘመሩ በየቤቱ በመዘዋወር በዓሉን ያውጃሉ። እኛም ሁላችን የደብረታቦር በዓልን ትርጉም በማወቅ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ትውፊቱን በመጠበቅ ልናከብር ይገባል።

መልካም የደብረታቦር በዓል!

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን ለገለጠበት ለበዓለ ደብረ ታቦር ዋዜማ እንኳን በሰላም አደረሰን!


ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡ ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ዘንድ ‹ቡሄ› በመባል ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ‹መላጣ፣ ገላጣ› ማለት ነው፡፡
በአገራችን ክረምቱ፣ ጭጋጉ፣ ደመናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት በዚሁ በዓል አካባቢ ስለ ኾነ በዓሉ ‹ቡሄ› ተብሎ ይጠራል፡፡ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ ‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እንዲሉ፡፡ በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች የቡሄ ዕለት ማታ ምእመናን ችቦ ያበራሉ፡፡ ይህም በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው፡፡ ሕፃናቱ ይህ በዓል ከመድረሱ በፊት ቀደም ብለው ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮኹ (ሲያኖጉ) ይሰነብታሉ፡፡ እናቶችም ለዚህ በዓል የሚኾን ዳቦ ለመጋገር ስንዴያቸውን ሲያጥቡ፣ ሲፈትጉ ይሰነብታሉ፡፡ በበዓሉ ዋዜማ (ነሐሴ ፲፪ ቀን) ሕፃናት በየቤቱ እየዞሩ ‹‹ቡሄ ና በሉ፤ ቡሄ በሉ፡፡ ቡሄ መጣ፤ ያ መላጣ፤ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ …›› እያሉ ይጫወታሉ፡፡ በዚህ ጊዜ እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ እያነሡ ይሰጧቸዋል፡፡ ሕፃናቱ ‹ቡሄ› የሚሉትም ዳቦውን ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

✨ ነሐሴ 7 ጽንሰታ ለእግዝእትነ ማርያም ✨

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

“ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ፣ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ።”

ማርያም ሆይ፣ በኃጢአት ፍትወት የተፀነሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ።

በዚህች ዕለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተጸነሰች። ወላጆቿ ቅዱሳን ኢያቄምና ሐና ልጅ አጥተው በቤተ እግዚአብሔር ጸሎት ይለምኑ ነበር።
ሐና ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ፦ “አቤቱ ጌታዬ፣ ለዚች እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ፣ ምነው ለእኔ ልጅ ነሳኸኝ?” ብላ አለቀሰች፤ ይህን ያየ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ለ40 ቀናት ሱባኤ ያዘ። በ40ኛው ቀንም ሁለቱም ሕልም አዩ።
ኢያቄም ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ነጭ ወፍ በራሱ ላይ ሲቀመጥ እንዳየ ነገራት። ሐናም ነጭ ርግብ በራሷ ላይ ወርዳ በጆሮዋ ገብታ በማህጸኗ ስትተኛ እንዳየች ነገረችው።

ይህንን ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው። በዚያን ዕለት በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እየጠበቁ እስከ ሰባት ቀን ለየብቻቸው ሰነበቱ።
በ7ኛው ቀን (ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ወደ እነርሱ ወርዶ፦ “ዓለም የሚድንባት፣ የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ” ብሎ ተሠወራቸው። እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። በዚህች ቀንም እመ ብርሃን ተጸነሰች።
በፈቃደ እግዚአብሔር እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች።

ምልጃዋና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን! አሜን።

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 
Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ሰላም ውድ የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁን?
በግቢ ጉባኤያችን የሚገኘው የባች እና መርሐግብራት ማስተባበርያ ክፍል ለሚዲያ ክፍል አዳዲስ አባል ስለሚያስፈልግ፤ ማገዝ የምንችል በአቅማችን ለማገዝ፤ ካልቻልን ደግሞ ለምናውቃቸው እህት ወንድሞቻችን እንድናደርስ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScxUvrV2MkCQW37RQ7_gG-2hfuj3blyv9aJZGk-Go0oVYggUA/viewform?usp=publish-editor


የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ 

Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.