የኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ በጀርመን በርሊን መካሄድ ጀመረ !
እስከ መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ. ም በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ በውጭው ዓለም በተለይ በጀርመን ያሉ የኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት አባላት እናት ቤተ ክርስቲያናቸውን በመደገፍ ረገድ ያላቸውን ሚና አስመልክቶ የየራሳቸውን ተሞክሮ የሚያቀርቡበትና ውይይት የሚደረግበት ነው። በመኾኑም በጉባኤው የአምስት አኀት አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች የተገኙ ሲኾን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትን በመወከል ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተዋል።
ጉባኤውን በጸሎት የከፈቱት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ 3ኛ የህንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የጉባኤውን አስፈላጊነት በማውሳት ፤ ለአዘጋጆቹ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በተመሳሳይም ከሮማ ካቶሊክ፣ ከምሥራቅ ኦርቶዶክስ፣ ከጀርመን ወንጌላዊት አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች በጉባኤው በመገኘት መልእክት አስተላልፈዋል።
©የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚድያ
✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨
መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]
በኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናትና በጀርመን ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በሚል ዓላማ በጀርመን ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው የኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ. ም በህንድ ማላንካራን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የመክፈቻ ጸሎት በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ተጀመረ።