እንናፍቃለን!
ከሰሞኑ ኦርቶዶክሳውያኑን በዋናነት በገድላት፣ “ማርያም ኀጢአት አለባት ወይስ የለባትም?” እና በሌሎችም ጉዳዮች “እየተፈሳፈሱ” ይመስለኛል፡፡ ቀሲስ ዲበኩሉ በላይ የተባሉት “አባት”፣ “ሐዋርያዊ መልሶች” በሚል ስያሜ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከሚያገለግለው አክሊል ከሚባል “ወጣት” ጋር በተለይ “ገድልን መርምሬ እንጂ በደፈናው አልቀበልም” በማለቱ ብዙዎች ቲክቶዶክሶች ጥርስ ነክሰውበታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፣ “ማርያም ኀጢአት አለባት” ብሎአል በሚል ሌላኛው አባት አስጠንቅቀዋል ተባለ፡፡ ነገሩ እንደ ዘበነ ለማ ያሉ ሰዎችም ፊት ለፊት ስሙን ጠቅሰው ባይናገሩም፣ ነገር ግን “ገድል አልቀበልም የሚል ኦርቶዶክስ አይደለም” በማለት አቋማቸውን አንጸባርቀዋል፡፡
በአጭሩ የገድልና የማርያም “ልዕለ ልዕልትነት” ጉዳይ ይህን ያህል ያጨቃጨቀው እነ ዘበነንም ኾነ ቄስ ዲበ ኩሉን፤ አስጠንቃቂውን አባት ጠቅሞ አይደለም፤ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ ወደ እውነተኛ ወንጌል ፊቷን እንዳትመልስ ተግተው ስለሚሠሩና ስለሚፈልጉ እንጂ፡፡ ጌታ ኢየሱስ ይገስጻቸው!
እንደ በፊቱ በጥቂቱም ቢኾን፣ ኦርቶዶክሳዊ ተሐድሶ አቋምን የያዙ ሰዎች፣ በዚያው መድረክ ብቅ ማለታቸው ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ እኛም አቋማችን ለኦርቶዶክስ ሌላ ሐዳሲ እንዲመጣ አንሻም፤ የራስዋ ልጆች በትክክልና በእውነት፤ በማያመቻምች አቋም ትክክለኛ ሐዳሲ እንዲኾኑ ነው ናፍቆታችን፤ አክሊል የተባለውም ወጣት “ኹሉን አውቃለሁ ባይነቱን” ትቶ፣ በክርስቶስ ባለው መዳንና ጸጋ ተግቶ፣ በቤቱ ውስጥ ያለውን የተነቀፈ ጽድቅና ቅድስና፤ መካከለኛና አስታራቂ በመናገር፤ በመስበክ ቢተጋ በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት ብዙዎች ወደ ወንጌል ይመጣሉ የሚል እምነት አለኝ!
አክሊል፤ ወደ እኛም ኾነ ወደ ወንጌላውያን መምጣት አለበት ብዬ አላምንም፤ ሸክሙ ወገኖቹ፤ ጭንቀቱ ኦርቶዶክሳውያን ሊኾኑ ይገባል፤ ጨርሶ ካልተገፋ በቀር ሊወጣ አይገባውም ከሚሉ አንዱ ነኝ!
ኦርቶዶክሳዊ ተሐድሶ እንደ ቃሉና እንደ መንፈስ ቅዱስ ምሪት ብቻ እንዲኾን እንናፍቃለን!