ጊዚያዊው የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ሆነው ከወርሃ ህዳር አንስቶ የሰሩት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።
እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በማህበራዊ ትሥሥር ገጹ ይፋ እንዳደረገው መሳይ ተፈት ለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል እንዲቀጥሉ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔ ላይ ደርሷል።
ከሶስት ወራት በላይ በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት እየሰሩ የሚገኙት መሳይ ተፈሪ በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች የሚያስመዘገቡትን ውጤት መሠረት ተደርጎ ሊታደስ በሚችል የአንድ ዓመት ውል ብሔራዊ ቡድኑን የሚመሩ ይሆናል።
አሰልጣኙ ቋሚ ኮንትራት የተሰጣቸው መሆኑን ተከትሎም አብረዋቸው የሚሰሩ የአሰልጣኝ ቡድን የማዋቀር ኃላፊነትም ተጥሎባቸዋል።
ከአፍሪካ ዋንጫ እና ከቻን ውድድር ውጭ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው መጋቢት በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከግብጽ እና ጅቡቲ አቻው ጋር የሚጫወት ሲሆን አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪም ብሔራዊ ቡድኑን ለእነዚህ ጨዋታዎች የሚያዘጋጁ ይሆናል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews