👯♀️🕺💃ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በመጪው እሁድ የካቲት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ተሳታፊዎች በነፃ የሚታደሙበት የዳንስ ፊትነስ ኮንሰርት ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
👯♀️🕺💃ኮንሰርቱን አስመልክቶ ትላንት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አዲስ አበባ በሚገኘው የአደዋ መታሰቢያ ሙዚየም በሚካሄደው የዳንስ ፊትነስ ኮንሰርት ላይ እስከ 10ሺ ተሳታፊዎች ይኖራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
👯♀️🕺💃ሆም ካሚንግ አዲስ በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀው የዳንስ ፊትነስ ኮንሰርት ላይ በተለይም ሃገራቸውን ለመጎብኘት ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ በርካታ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
👯♀️🕺💃በኮንሰርቱ ላይ የመታደም ፍላጎት ያላችሁ ዜጎችም በኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ዶት ኮም ላይ በነጻ መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን በቪ አይ ፒና ቪቪ አይ ፒ ደረጃ መሳተፍ ለሚፈልጉ ታዳሚዎችም የተዘጋጀ ቲሸርት መኖሩን ሰምተናል፡፡
👯♀️🕺💃ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በዳንስና ጭፈራ እየተዋዙ የሚቀርቡበት የዳንስ ፊትነስ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃና ጭፈራዎች ለአለም ከማስተዋወቅ ባለፈ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን እንዲሁም የሰውነት ክብደት መጨመርን ለመከላከል ትልቅ አስተዋጽዎ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡
👯♀️🕺💃እንደዚ አይነት በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት የጋራ ኮንሰርት መዘጋጀቱም አንድነትና መቻቻልን ለመፍጠር ሚናው የጎላ ነው ተብሏል፡፡
ዜናውን ያደረሰን ሪፖርተራችን ብሩክ አስቀናው ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews