2ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው ብልጽግና ፓርቲ ነባሮቹን የፓርቲውን አመራሮች በድጋሚ መርጧል።
ፓርቲው ከዚህ ቀደም ከነበረው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በተለየ መልኩ በዘመናዊ መንገድ አካሂጃለሁ ባለው ምርጫ አቢይ አህመድን የፓርቲው ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል ።
በምክትል ፕሬዝደንትነት እያገለገሉ የሚገኙትን ተመስገን ጥሩነህና አደም ፋራህንም እንዲሁ በድጋሚ መርጧቸዋል ።ብልጽግና ፓርቲ አመራሮቹ በከፍተኛ ድምጽ እንደተመረጡ የጠቀሰ ሲሆን በምን ያህል ድምጽ እንደተመረጡ ግን አልገለጸም ።
አመራሮቹ በጉባኤተኞቹ ፊት ቃለመሃላ መፈጸማቸውንም ፓርቲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል ።
1700 የፓርቲው አባላት በድምጽ እየተሳተፉበት በሚገኘው የብልጽግና ጉባኤ ከአመራር ምርጫ በተጨማሪ የተሻሻለው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ውይይት በማድረግ በሙሉ ድምጽ ስለመጽደቁ ተነግሯል ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በብልጽግና ጉባኤ ላይ በመሳተፍ የአጋርነት መልዕክታቸውን ያስተላለፉ የ15 አገራት ገዥ ፓርቲዎች የተለያዩ መዳረሻዎችን መጎብኘታቸውን ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያሳያል ።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews