🇪🇹🛫በኢትዮጵያ አየር ኃይል የተሰራችው ፀሃይ - 2 የስልጠና አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራዋን በስኬት ማከናወን መቻሏን የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ ኮሎኔል መሰረት ጌታቸው ገልፀዋል፡፡
🇪🇹🛫ፀሃይ -2 አውሮፕላን ለበረራ ማሰልጠኛ እና ለሌሎች አገልግሎት መዋል የምትችል መሆኑን ያስታወቁት ኮሎኔሉ የተሰጣትን ግዳጅ በብቃት መፈፀም የሚያስችላትን የዘመኑን የአቭዬሽን ቴክኖሎጂ መታጠቋንም አብራርተዋል፡፡
🇪🇹🛫የአውሮፕላኗ ስኬታማ የሙከራ በረራ አየር ኃይሉ የደረሰበትን የከፍታ ጉዞ ጠቋሚ ነው ያሉት ምክትል አዛዡ በቀጣይነትም ወደ ምርት ሂደት ለመሸጋገር ፋብሪካውን የማደራጀት ፣የመፈተሻ እቃዎችን የማሟላት እና የሙያተኞችን አቅም የማጎልበት ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
🇪🇹🛫የትራንስፖርት አውሮፕላን ስኳድሮን አዛዥና አብራሪ እንዲሁም የፀሃይ -2 የሙከራ በረራን በስኬት ያካሄዱት ሻለቃ ፍቃዱ ደምሴ በበኩላቸው አውሮፕላኗ አለም የደረሰበትን የአውሮፕላን ቴክኖሎጂ የታጠቀች የበረራ አቅሟም አስተማማኝ፤ ተቋሙ ለያዘው ራዕይ ጉልህ አስተዋፅዖ የምታበረክት መሆኗን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመለክታል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews